"ወልደያ ከተማ ወደ ባህር ዳር መውጫ ዋናው መንገድ ከአስፋልቱ ትንሽ ገባ ብሎ እየተሰራ ያለና ያላለቀ ትልቅ እስር ቤት አለ፡፡ በትግራይ ውስጥ ሲዋጉ ከነበሩት ቁጥራቸው ከ300 እስከ 400 የሚደርሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማሰረያ ቦታ ስልጠፋ ለግዜው በዚህ ባላለቀና አጥር እንኳን በለለው እስር ቤት ውስጥ ታስረው ይገኛሉ፡፡ በተለያየት ቦታዎችም በርካታ የታሰሩ የመከላከያ ሰራዊት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ታስረው የሚገኙት ወታደሮች በአብይ አህመድ እና በመከላከያ ሰራዊት አዛዦች እየተሰራባቸው ያለው ሴራ እጅግ መናደዳቸውን ይገለፃሉ፡፡ አብይ አህመድ እና የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በጦሩ ላይ እየሰሩት ካለው በርካታ ሴራዎች አንዱ መከላከያ ሰራዊቱ የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆነው ጌታቸውን ረዳን ለመያዝ ወይም ለመግድሉ በርካታ ግዚያት በቀለበት ውስጥ ካስገቡት በኋላ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ከወያኔ ጋር በመሳጠር እየሰሩት ባለው ሴራ ምክንያት 'ጌታቸው ረዳን ለመረጃ ስለምንፈልገው በህይወት መያዝ እንጅ መገደል የለበት' የሚል ቀጭን ትዕዛዝ እየሰጡ ለበርካታ ግዚያ ከታተረበት ቀለበት ሾልኮ እንዲወጣ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በዚህም የጦር ሰራዊት አባላት እጅግ ይናደዱ ነበር፡፡" በአጠቃላይ በትግራይ ውስጥ በነበረው እና አሁን ወደ አዲስ አበባ እየሸሸ በሚገኘው የመከላከያ አባላት ላይ በጦሩ አዛዥች እና በአብይ አህመድ እየተሰራው ያለ ሴራ እጅግ የሚያም የሚያበሳጭ፣ እንዲሁን ከፍተኛ የሀገር እና የህዝብ ክህደት ነው፡፡ "
ብለዋል!!
