* ከጥቅምት 24 በፊት የህወሃት ሰዎች መቀሌ ፕላኔት ሆቴል ያለምንም ከልካይ ይንፈላሰሱ ነበር።
* ጥጋብና ዕብሪት ሆዳቸውን ነፋቸውና ሰሜን ዕዝን አጠቁ። የሀገሪቱን 80% ከባባድ የጦር መሳሪያ ዘረፉ ፣ ከ 15 ሺ በላይ ወታደሮችን ( ከ አንድሺ በላይ መኮንኖችን ይጨምራል) ከስራ ቦታቸውና መኖሪያ ቦታቸው በውድቅት ሌሊት አፍነው ወደ እስር አጋዙ።
* በጦርነቱ የመጀመሪያ ፍጻሜ ህወሃት እጄ ገባ ያለውን ከባድ መሳሪያዎች አጣ። ይተማመንባቸው የነበሩ ብዙ ሺህ የጦር ሰራዊት አባላቱ ድባቅ ተመቱ።
* ህወሃት ከሀገሪቱ የመከላከያና የጸጥታ ሀይል ተነቅሎ ተጣለ። በዝርፊያ ያቋቃመው ኤፈርት የተባለ ድርጅቱ ንብረቶች ፣ በኢትዮጵያ ባንኮች ያሉ ሀብቶች ሁሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ወደቁ።
* የህወሃት አንጋፋ መሪዎች ከፊሎቹ እነ ስዩም መስፍን ፣ አባይ ጸሀዬ ፣ አስመላሽ ፣ ዘርአይ አስገዶም ህይወታቸውን በጦርነት አጡ። የህወሃት መስራች ስብሀት ነጋ ፣ የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ አባይ ወልዱ ወዘተ ተማረኩ።
* ዛሬ ህወሃት ከጦርነቱ በፊት አረቄ ይጠጣበት የነበረው ፕላኔት ሆቴል በመግባቱ ጮቤ እየረገጠ ነው። ከላይ ያለውን ኪሳራ ለመክፈል ጦርነት መክፈት አስፈላጊ ነበርን ?
አቶ ስዩም መስፍን ከጦርነቱ በፊት " አቢይ አህመድ ጅል ነው " ብለው ነግረውን ነበር። በህይወት ቢኖሩ ኖሮ አሁንስ ማነው ጅሉ ማን ነው?