በትግራይ ህዝብ ላይ በአለም ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ አይነት አለምን ያስደነገጠና ጉድ ያሰኘ ግፍ የፈፀሙትን የጠላት ወታደሮችን ማርኮ የሚንከባከበው የትግራይ መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ህዝብ ለመርዳት፦ ለመመገብና ለማከም የመጡትን የረድኤት ሰራተኞችን ይገድላል ማለት አንድም መሰረተ ቢስ ውሸት ሁለትም እጅግ አስቂኝ ቀልድ ነው።
የረድኤት ሰራተኞቹን የገደለው የረድኤት ድርጅቶችን "ለህወሀት የጦር መሳርያ ያቀርባሉ" በማለት የሚከሰውና ከትግራይ ጠቅልለው እንዲወጡለት የሚፈልገው የብልፅግና መንግስት እኔጂ TDF አይደለም፤አይሆንምም።
የTDF ሰራዊትማ ህዝቡን የሚያክሙለትንና የሚመግቡለትን የረድኤት ድርጅት ሰራተኞችን ምን ልሁን ብሎ ይገድላል?
ሀሰት በመንዛት የአለም ህብረተሰብን ማደናገር የሚቻልበት ምእራፍ ተዘግቷል።
የፒፒ መሪዎች ለሚፈፅሟት እያንዳንዱዋ ወንጀል ነገ በአለም አቀፍ ህግ ይጠየቁበታል።

Please wait, video is loading...