(ደንቆኛል!)
"ጮክ ብለው 'እጅ ስጡ' እያሉ ይጣሩ ነበር፣ እኔና ጓደኞቼ ፈርተን ድንጋይ ስር ተደብቀን ነበር፣ ከዛ አንዱ መቶ አለቃ የሚባል ልዩ ሃይል መጣና እኔን 'አይዞሽ እጅ ሽጪ አልገድልሽም፣ ልጄ ማለት'ኮ ነሽ ለምን እገድልሻለሁ፣ አይዞሽ' አለኝ፣ እኛም እጃችን ሰጠን። ወደ ተሰበሰቡት ብዙዎቹ ወሰዱን።
እጃችን ከሰጠን እንደሚገድሉን ነበር የተነገረን። የተማርነውም እንደዛ ነው። ግን እጃችን የሰጠን በህይወት አለን፣ እጃቸው ያልሰጡ ግን ብዙ ሲሞቱ አይቻለሁ።
የማስተላልፈው መልእክት: ይህ መዓት እ/ሄር ያመጣው ከሆነ እሱ እንዲያነሳው ህዝቡ ፀሎት እንድያደርግ ነው። ለመንግስታቱም ስለሚጠፋው የህዝባቸው ህይወትና የሚወድመው የሃገራቸው ንብረት ብለው ተወያይተው እርቅ እንዲያወርዱ ነው የምጠይቀው። ከዚህ በተጨማሪ ግን ህዝቡም ሆነ ወታደሩ ይሄ አስከፊ የወንድማማቾች የእርሰበርስ ጦርነት እንዲቆም አዛዦቹም መንግስታቶቹም እንዲጠይቅ፣ ለፓለቲከኞች ስልጣን ሲባል እርሰበርስ መተላለቅ የለብንም እንዲል ነው የማስተላልፈው መልእክት!"
መልእክቱ: ከከፋ ዞን "የ10ኛ ውጤት ሳይመጣልን ሲቀር ስራም ስላልነበረን፣ ጥሩ ደመወዝ አልው ብለን ከጓደኞቼ ጋር ወደ ውትድርና ተቀላቀልን" ያለችው ልጅ መልእክት ነው።
~~~~
እህቴ እንኳን እ/ሄር አተረፈሽ፣ "የወንድማማቾች የእርሰበርስ ጦርነት" በምትይው አጥፊ ጦርነት ምክንያት እንኳንም ህይወትሽ አልተቀጠፈ።
"ልጄ ማለት ነሽ ለምን እገድልሻለሁ" ብሎ ያተረፈሽ ባለንጋራሽም ክብርና ምስጋና ይድረሰው።
እንግዲህ ህዝቡም ወታደሩም እርቅና ድርድር እየጠየቀ ነው። ጠላቴ ከሚለው ጋር ክላሽ ይዞ ፊትለፊት የተገናኘ ወታደር እንኳን "እጅ ስጥ ልጄ ነህ፣ ወንድሜ ነህ፣ እህቴ ነሽ" እየተባባለ ምህረት እየተደራረገ ነው። ታድያ መሪዎቹም እንዲህ የማይሆኑበት ምክንያት ምንድነው? ማን ነው "እምቢ!" የማለት ስልጣን የሰጣቸው??? 100% ችግሩ መሳርያ ካነገተው ላይ ሳይሆን ፓለቲካው ከሚዘውረው አካል ነው። ይበቃሃል ወደ ጠረጴዛ ቅረብ እንበለው። ይህ እልቂት ይቆም ዘንድ ከሁሉም ወገን እንጠይቅ!!!
"እጅ ስጪ ልጄ ነሽ አልገድልሽም!"
Please wait, video is loading...