Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42713
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ገና በአማውቴና ጢያ፣ ክስታኔ፣ ሰሜን ጉራጌ

Post by Horus » 24 Jun 2021, 21:28

Last edited by Horus on 25 Jun 2021, 14:26, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42713
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ገና በአማውቴና ጢያ፣ ክስታኔ፣ ሰሜን፣ ጉራጌ

Post by Horus » 24 Jun 2021, 22:24

እንዳጋጣሚ ይህን አካባቢ ለምታውቁ፣

ያ ልጆቹ ገና (አንቃት) የሚጫወቱበት ሰፊ ሜዳ ጨፋ ወይም ሶሶቱ ይባላል፣ በአራት ቀበሌዎች መሃል ነው ያለው ።

ከሚዳው ሰሜን ያለው ቀበሌ ዎተደር ወይም ወተደር ይባላል። በቀኙ በኩል ገገራ ሚካኤል አለ።

ከሜዳው በሰሜን መዕራብ ያለው ተራራ የባለወልድ (ባሎልድ ገገራ) ይባላል። ትልቁ የአማውቴ ደብር ባለወልድ ቤ/ክ ነው። የገና ቀን ይከበራል ፣ የልጆች ገና ግጥሚያ የሚደረገው ከቤተስኪያን መልስ ነው።

ከሜዳው ምዕራብ ያለው ቀበሌ ጉሎ ይባላል። ባልሳሳት እዚያ ጉሎ ኪደነ ምህረት አለች

ከሜዳው ምስራቅ ያለው ቀበሌ እንዶዴ ይባላል። ጫፉ ላይ ገርጊስ (ጎርጊስ) ቤተ/ክ አለ።

ከሜዳው ደቡብ ያለው ቀበሌ እንጀሪ ይባላል። እንጆሪ በብዛት ያለበት ቦታ ነው ። በእግር ለሚሄድ ወደ ጢያ ማሪያምና የጢያ እማየ (የጢያ ትክል ድንጋይ) መሄጃው ነው።

በነገራችን ላይ የጢያ ሃውልት ላይ ያለው ሳንጃ በክስታኔ ቋንቋ ሰንዳ ይባላል። አሁን ሴቶችም ወንዶችም እንሰት የሚቆርጡበት ባለ ሁለት ስለት እጅም ሳንጃ ወይም ጎራዴ ነው።

በሜዳውና በእንዶዴ መሃል ክረምት ክረምት ወንዝ የሚሆን ገደል ስለሆነ ያንቃት ገና ግጥሚያ ብዙውን ግዜ በእንጀሪና ወተደር ቀበሌዎች መሃል ነው ፤ አሸናፊው ቡድን ኳሷን (ቀርጠማው) ወደ ራሱ ቀበሌ ያስገባው ነው ።
Last edited by Horus on 25 Jun 2021, 19:07, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42713
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ገና በአማውቴና ጢያ፣ ክስታኔ፣ ሰሜን፣ ጉራጌ

Post by Horus » 25 Jun 2021, 14:25

ብዙዎቻችሁ አርቲስት አቦነሽ አድነውን (የባላገሩ ዘፋኝ) ታቋታላችሁ ። ተወልዳ ያደገችው ቡኢ ነው ። ቡኢ የክስታኔ ጉራጌ (ሰሜን ጉራጌ) ዋና ከተማ ነው ። ባልሳሳት ከምድረ ከብድ በምዕራብ 20 ደቂቃ ያለ ከተማ ነው። አሁን በትንሹ የሚያበረታታ እንስቃሴ እያደረገ ነው ። ይህ አካባቢ ደቡብ ሶዶ ነው። ከላይ በገና ጨዋታ ምታዩት አማውቴ ሰሜን ሶዶ ነው ።


Horus
Senior Member+
Posts: 42713
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ገና በአማውቴና ጢያ፣ ክስታኔ፣ ሰሜን ጉራጌ

Post by Horus » 25 Jun 2021, 20:33

በክስታኔኛ ምድረ ከብድ ማለት ክቡር ምድር፣ ቅዱስ ምድር (Holy Land) ማለት ነው ። ይህን ገዳም መጀመሪያ ያቆሙት ቅዱስ አቦ በ1460 ዓ/ም ነው። በግራኝ መሃመድ ተቃጥሎ ነበር ። ለመጨረሻ ግዜ በዚህ መልክ ያሰሩት አጼ ምኒልክ እና ፊ/ሪ ሃብተ ጎርጊስ ዲነግዴ ናቸው ። ቅዱስ አቦ ምድረ ከብድ አቦን፣ ዝቋላ አቦን፣ አዳዲ ማሪያምን ያሰሩት በዚያው ዘመን ነው ። ያረፉበትና መቃብራቸው እዚህ ምድረ ከብድ በር ላይ ነው ያለው ። የሚከበረውም በመጋቢት 5 ነው


Horus
Senior Member+
Posts: 42713
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ገና በአማውቴና ጢያ፣ ክስታኔ፣ ሰሜን ጉራጌ

Post by Horus » 26 Jun 2021, 01:17

ኢዮ እንዞሪቴ ገና ነበቦ !! (እነሆ ሆያሆዬ ገና አበበ) !!

Selam123
Member
Posts: 4
Joined: 21 Jun 2021, 14:45

Re: ገና በአማውቴና ጢያ፣ ክስታኔ፣ ሰሜን ጉራጌ

Post by Selam123 » 26 Jun 2021, 04:48

'ክስታኔ' ትርጉሙ 'ክርስቲየን' ማለት ነው። የሃይማኖት ተከታይነትን እንጂ ብሔርን/ማሕበረሰብን አይወክልም። የብሔሩ/ማሕበረሰቡ መጠሪያ 'ሶዶ ጉራጌ' በሚለው ይስተካከል።

Horus
Senior Member+
Posts: 42713
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ገና በአማውቴና ጢያ፣ ክስታኔ፣ ሰሜን ጉራጌ

Post by Horus » 26 Jun 2021, 12:04

ነጆ አራጆ (በጸጋዬ ስሜ)፣ እኛ ልጆች ሆነን ባጭሩ ኩስ (ኳስ) ወይም ዝላለ (ዝላይ) እንለው ነበር ። ይህ የዝላይ ጨዋታ የክስታኔ ጎረምሶች ብቸኛ ባህል ይመስለኛል ። ሌላ ቦታ አላየሁትም ። ሾላ እርግፍ እርግፍ ሳይሆን ዝላዩን ማለቴ ነው ።

ይህ ለማታቁ ጸጋዬ ስለ እንጀሪ የሚለው ነገር አሁን የጎርደና ሴራ የሚባለው ድሮ ጉባኤ በሚደረግበት ቦታ ስም ይጠቀስ ነበር ። ለምሳሌ የጎርጢ ሴራ፣ የእንጀሪ ሴራ ማለት ሁለቱም ይህ ያገር ጉባኤ የተደረገባቸው ሲሆን ለምሳሌ አንድ ህግ በጎርጢ ስብሰባ ላይ ተወስኖ ከነበረ ያ ሕግ የጎርጢ ሴር ወይም የጎርጢ ውሳኔ ተብሎ ይታወቅ ነበር ። የእንጀሪ ሴራም እንዲሁ የታወቀ ነው ። ዛሬ ይህ የጎርደና ጉባኤ (ኮንግሬስ ማለት ነው) የሚደረገው የት እንደ ሆነ አላቅም ።



Post Reply