አፍሪካ እንደ አሜሪካ ለምንድን ነው የነጮች አህጉር ያልሆነችው?
ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝብ ባይኖሩ፣ ምኒልክ የሚባል መሪ ባይኖር ኖሮ የዛሬ አፍሪካ ልክ የዛሬ አሜሪካን ትሆን ነበር።
Re: አፍሪካ እንደ አሜሪካ ለምንድን ነው የነጮች አህጉር ያልሆነችው?
አፍሪካ? ወይ ጉድ!ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝብ ባይኖሩ፣ ምኒልክ የሚባል መሪ ባይኖር ኖሮ የዛሬ አፍሪካ ልክ የዛሬ አሜሪካን ትሆን ነበር።
የአሜሪካ አንዷ ቅኝ ገዢ ብትሆን ኖሮ
የዛሬ አሜሪካ እንዴት ናት? ጥቁሮችን ያገለለች፤ ነጥላ በሁሉም ነገር ተጭና የበታች ያደረገች፤ የጥቁር ፕሬዝዳንትም የሾመችና የጥቁር ቢልየኔርም የፈጠረች አገር ናት። ኢትዮ ይህ ይሆን ነበር? አሜሪካ ከአውሮፓዊያን የተለየች ስለነበረች ምናልባት 59ኛ ክፍለ ሃገር ታደርጋት ነበር?
59ኛ ለማድረግ ብዙ ነጮች ማስፈር ስለማያስፈልጋትና በመሬት በሽበሽ ያለች ስለሆነች በወረራው አልገባችም *የላይቤሪያ* ጉዳይን ረሳሁት ክክክክ። የቬትናም እንዴት ነበር? ገላ ጨርሳ ነው የለቀቀችው። ቀኝ ገዢዎች አፍሪካን ለቀው የወጡበት ምክንያት እንደ አውስትራሊያ ገለው መጨረስ ስላቃታቸው አይደለም? ሁልጊዜ በነጻነት ተዋጊዎች ህዝባቸውን ላለማስጨረስ ብለው የጅ አዙር አገዛዝ መሰረቱ። አሁን እነማን ናቸው 59ኛ የአሜሪካ ጭቁን ስቴቶች?
ሚኒሊክ ባይኖር ምን ይሆን ነበር?
ብሪቲሽ ሶማሌ ልክ እንደ አሁኗ ጂቡቲ፤ በጣሊያን እጅ የቀረችው ኤርትራ፤ በሱዳን በኩል ግብጽ ወይም ሱዳን ደቡብ በከፊል በሱዳንና በኬንያ ይጠቃለሉ ነበር። እነ ጣሊያን፤ ፈረንሳይና እንግሊዝ እንዴት እንደሚከፋፈሉ የወጣ ካርታ ነበር።
እነዝህ የደቡብ አፓርታይድ ሲስተም ብቻ ሳይሆን ጥቁሩን ይጨርሱ ነበር። ሲጨርሱና ሲገሉ እንጂ ሲዋሃዱና ሲያሳድጉ አላየንም? ዘመናዊ ፋብሪካ አስጀመሩ። መንገዶችና ድልድዮች ገነቡ ኋላ ቀር የነበረውን የአፍሪካ አገር ወደ ዘመናዊ ስርኣት አሸጋገሩ።
ምን ለማለት ነው? አንድን ነገር ሙሉ በሙሉ ጨለማ ብቻ አድርገን ካየን ብዙ የምንስተው ነገር ይኖራል። ብርሃን ብቻ ካየንም ችግር ነው። ሁለቱንም ለማየት እንሞክር።
ትዝ ያለኝ ፑቲን አፍሪካን ሊወሯትና ሊያጠፋችሁ ያለውን እንደገና ማየት ይጠይቃል። በተጨማሪም ታሪክን ማገላበጥ ከአሁኑ የአፍሪካ ሁኔታ ጋር ማያያዝ የሚጠይቅ ቆንጆ አርእስት ነበር።
Re: አፍሪካ እንደ አሜሪካ ለምንድን ነው የነጮች አህጉር ያልሆነችው?
እነሱ በራሳቸው ድክመትና አላዋቂነት ካልተሳሳቱና ካልወደቁ በተቀር ብልጽግ ናና ኢዜማ ኢትዮጵያን ያፍሪካ መሪ ሃያል አገር የማድረግ እድሉ ውለል ብሎ ተከፍቶላቸዋል ። ለምን በሉ?
አንደኛ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንካራ አገር፣ ጠንካራ መንግስት ይፈልጋል ። የዘር ፖለቲካ እንደ ካካ አጸያፊ ቃል እየሆነ ነው ። ስለዚህ መላ ኢትዮጵያዊ ብሄራዊ አንድነት እየጠየቅ ነው ። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንካራ ጦር፣ ጠንካራ መንግስት እንዲኖር እየጠየቀ ነው።
ሁለትኛ፣ በተልይ በተለይ የኢትዮጵያ ሕዝብ የማንም አገር ጣልቃ ገብነት አምርሮ ሊዋጋ ተነስቷል። አሜሪካ ተቻኩሎ በሰራው ስህተት በግድ ወደ ኋላ ያፈገፍጋል። ይህ ግዴታ ነው። ያፍሪካ አንድነት፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ቱርክ፣ ኢራን ፣ኢምሬት፣ ኩባ፣ ወዘተ ኢትዮጵያን መደገፋቸው ያለውን ያለም ትግል ቁልጭ አድርጎታል !
ኢትዮጵያ የምትፈልገው ነገር ሚሸጡላት አገሮች እኒህ ናቸው ።
እጅግ ግዙፉ ያሜሪካ ስህተት፣ አሜርካ እንዴት ካፍሪካ ተባረረቸ የሚለው ግዙፉ የደፊት የታሪክ ክርክር የጀመረው አሜሪካ ላባይ ግድብ ብድር ከልክላ ኢትዮጵያ በራሷ ሕዝብ መዋጮ ህዳሴን የገነባች ቀን ነው። ያኔ ነው አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ሊኖራት የሚችለው ተጽዕኖ አፈር ተድሜ የበላው! አሁን ያሜርካ ባዶ ጥርስ አልባ ማስፈራራት ነው ።
የምዕራብ ኩርፊያ እድገታችንን በትንሹ ቀስ እንዲል ከማድረግ ባለፈ ሌላ ፋይዳ የለውም ።
ሱዳን ካላረፈች ሌላ ሱማሌ ትሆናለች ! ፈጣሪ ካለና ጥቂት ረጅም ተጓዥ ሚሳይሎች ከገዛን ወይም ከሰራን ግብጽ ጭራዋን ትጠቀልላለች !
ጠንካራ መንግስት፣ ጠምካራ ጦር ይህ ነው የዛሬ አጀንዳችን !!

Last edited by Horus on 02 Jun 2021, 10:17, edited 1 time in total.
Re: አፍሪካ እንደ አሜሪካ ለምንድን ነው የነጮች አህጉር ያልሆነችው?
አሜርካ በዚህ ከቀጠለች ያፍሪካ ፖለቲካዋ ሁሉ ገደል ነው የሚገባው !! አሜሪካ ቻይናን የምትታገለው ኢትዮጵያ በመጉዳት ከሆነ ካፍሪቃ ቀንድ እናባርራታለን !
Re: አፍሪካ እንደ አሜሪካ ለምንድን ነው የነጮች አህጉር ያልሆነችው?
በኢምፒሪያሊዝም ወደ ግሎባላይዜሺን ተሸጋግረናል እኮ! ክክክክክክአሜርካ በዚህ ከቀጠለች ያፍሪካ ፖለቲካዋ ሁሉ ገደል ነው የሚገባው !! አሜሪካ ቻይናን የምትታገለው ኢትዮጵያ በመጉዳት ከሆነ ካፍሪቃ ቀንድ እናባርራታለን !
የአሜሪካ ካልቸር እንግሊዝኛን እንደ አሜሪካኖች መናገር (አህኑ በኢትዮ እንደሚታየው ነበርርርርርርር ማለት። የአሜሪካን ባህል መስፋፋት ስነ ልቦናስ አሜሪካን ለመምሰል መሞከር ወዘተ....።
ነባር አሜሪካኖች ከ7 እስከ18 ሚልየንን በግምት ነበር ይባላል (ወደ 12 ሚሊየን እንደማለት ነው) 90% ገለው እንደ ጨረሱ አፍሪካን መጨረስ አይችሉም። አንድ ቢሊየን ህዝብ የደረሰውን በረሃብና በብሽታ መጨረስ ኤድስ ኢቦላ ቢሞክሩም አልቻሉም። የህዝብ ብዛት መቀነስ መሃን ማድረግ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው። እርስ በርስ ማፋጅትም አልረዳቸውም። ስለዝህ እቀባ ይጠቀማሉ።
የአሁኗ እቀባ ቀላል ናት። ዋናው እቀባ አገር የሚጎዳው ስንዴ መከልከል አይደለም። ዋና መሳሪያቸው የውጭ አገር ምንዛሬ የሚባለው ነው። 1 ዶላር 50 ብር ደርሷል። በውጭ ምንዛሬ እጦት ፋብሪካ የቆመ እለት ያኔ ነው መተራመስ። በገንዘብ እቀባ የመጣ እለት ነው እየየው።
ግን ይህ ሁሉ አይሆንም። ፕሮፓጋንዳ ነው!!! የቪዛ እቀባ አጄንዳ ለማስቀየር ነው። አሜሪካ ቴሌን ተረክባለች። ሌሎች ዋና ፕሮጄክቶች የሚባሉትም ከቻይና ጋር ሆነው ተቀራምተዋል ለውደፊቱም እንደዝሁ። በሃይለ ስላሴ ነበር የኢትዮ አየር መንገድ ከአሜሪካኖች ናሽናላይዚድ የሆነው። አሁን የማን እንደሆን በግልጽ ባይነገርም (የቻይናና የአሜሪካና ተላላኪዎቻቸው ነው) የባቡር መንገዶችና ሌሎችም የቻያናን (የአሜሪካም) ኢንቨስትሜንት ሳይኖርበት አይቀርም። ለምንድነው የሚሸፋፈነው?
ኢትዮ እድለኛ ሆና ለጊዜያዊ እንቭስትመንት ቦታነት ተመርጣ ይሆናል። ልክ እንደ ኤዢያ አገሮች ... ባንግላዴሽ ኢንቨስትመንት ጦፉ ነበር። ሁሉም ፋብሪካዎች ተነቀለው ባዶ ሆናለች። የዘመኑ የግሎባላይዜሽን ካፒታል ተንቀሳቃሽ ነው። ትክለውት አገር ውስጥ የሚቀር አይደለም!! የኢትዮም የተለየ አይሆንም። ቋሚ የሆነው የነዳጅና የማእድን ሃብቶች በነዝሁ ተይዟል አረቦች ሳይቀሩ ወርቅ አምራቾች ናቸው። እድሜ ለባሪያ ፈንጋዮች ክክክክክ
ኢኮሚውን ማነው የያዘው፤ምን እየተሰራ ነው፤ ወዘተ.... ለማወቅ ጥረት ስለማይደረግ ሙሉ በሙሉ ጥላቻ ወይም ሙሉ በሙሉ ድጋፍ አይገባም። ክሪቲካል መሆን ያስፈልጋል ለማለት ነው።
Re: አፍሪካ እንደ አሜሪካ ለምንድን ነው የነጮች አህጉር ያልሆነችው?
በግሎባላይዜሽንና ብድር ሱስ አይዲሎጂ የተጠመቀ ሰው ሌላ ሪያሊቲ ያለው አይመስለውም ። ካፒታሊዝም ገበያና ጥሬ እቃ ነው የሚፈልገው ። ያን ለማግኘት ከቀሩት ጋር ተፎካክሮ ሊመዘብረን ይችላል ። ግን በፖለቲካችን ግብቶ ሲፈተፍት ይባረራል ። ኢትዮጵያ ያለ አሜርካ ብድር ለሺ አመት ኖራልቸው። ታዲያ ምን ያረጋል ሰርቶ ማይበላ ለማኝ አገር አልሚው ሰራተኛን ህዝብ ሲሰድብ ሲረግጥ ኖረ ። አሁን ያ ባንዳ መቃብር ሲገባ ያሜሪካ እዬዬ ባያውቁን ነው ። አሜርካ ፋይዳቢስ የሆነችን ለኛ ያባይ ብድር የከለከለች ቀን ነው ። ኢትዮጵያ ዲያስፖራ 6 ቢሊዮን ዶላር ባመት ይልካል ! ደሞ ሌላም መላክ ይችላል፣ የራሱ ዴቬሎፕመንት ባንክ አቁሞ ለኢትዮጵያ ማበደር ይችላል ። ግ ን በነጭ የተገረፈ ጥገኛ አንጎል ሌላል ነገር ማየት ከቶም አይችልም ።
Re: አፍሪካ እንደ አሜሪካ ለምንድን ነው የነጮች አህጉር ያልሆነችው?
በግሎባላይዜሽንና ብድር ሱስ አይዲሎጂ የተጠመቀ ሰው ሌላ ሪያሊቲ ያለው አይመስለውም ። ካፒታሊዝም ገበያና ጥሬ እቃ ነው የሚፈልገው ። ያን ለማግኘት ከቀሩት ጋር ተፎካክሮ ሊመዘብረን ይችላል ። ግን በፖለቲካችን ግብቶ ሲፈተፍት ይባረራል ።
ኢሜሪያሊዝም ፡) የድሮ ካፒታሊዝም ገበያና ጥሬ ሃብት የነበረው ርካሽ ጉልበት ፍለጋ ወደ ፋብሪካ መገንባት ተሸጋገረ። ከድሮው ታሪክ ወደ አዲሱ እንሸጋገር። አሁን ካፒታል ኤክስፓርት ማድረግ ተጠናክሮ በኣውት ሶርስንግ... ቋንቋ ተተካ። አንቀሳቃሹ ማን ነው? ገንዘብ። ግሎባላይዜሽን ይባል እንጂ አዲሱ ኢምፔሪያሊዝም ፡) የገንዘብ ካፒታል አለም የሚያሽከረክርብት ጊዜ ውስጥ ከገባን ቆይተናል። በፓለቲካም በቀጥታ ቅኝ ገዢ የነበረው ለቆ በእጅ አዙር አገዛዝ በድሮው ስማቸው በአጎብጅ ወይም አቀባባይ ከበርቴ በዘመኑ አነጋገር በተላላኪዎች መተካት ማለት ነው። በፓለቲካችን አይግቡ? ሰውዬ ምን ነካህ?
የኔ በጨለማው ዘመን ነው? ክክክክ ስርቶ ማይበላው ፓለቲከኛው ነው? ክክክክ አሜሪካ ትህነግ መርጣ መልሳ ልታነግስ ነው? ክክክክክክ ያለፈውን በመሳደብ ያሁኑን በማሽሞንሞን እውነትን መደበቅ አይቻልም። ያው አብረን ነን። ክክክክክኢትዮጵያ ያለ አሜርካ ብድር ለሺ አመት ኖራልቸው። ...
ታዲያ ምን ያረጋል ሰርቶ ማይበላ ለማኝ አገር አልሚው ሰራተኛን ህዝብ ሲሰድብ ሲረግጥ ኖረ ። ... አሁን ያ ባንዳ መቃብር ሲገባ ያሜሪካ እዬዬ ባያውቁን ነው ። አሜርካ ፋይዳቢስ የሆነችን ለኛ ያባይ ብድር የከለከለች ቀን ነው ።
እንዲህ አዲስ ሃሳብ ማፍለቅ ጥሩ ነው። የዲያስፓራ ባንክ ከውጭ አገር ባንኮች በምን ይለያል? ለመሆኑ በኢትዮ የሚገኙ የውጭ አገር ባንኮች ስንት ናቸው? ከአገሪቱ የሚያገኙትን ትርፍ እንዴት ነው ወደ አገራቸው የሚያዛውሩት? ለፓለቲካ ይጠቀሙበት ይሆን? መልስ አዎ። የዲያስፓራ ባንክ ፓለቲካውን እንደሚፈልገው ለማዞር ይረዳዋል። ገንዘብና ፓለቲካን ማገናዘብ እንዴት ያቅተን? ፋይናንስ ካፒታል አገሩ ዬት ነው? ክክክክየራሱ ዴቬሎፕመንት ባንክ አቁሞ ለኢትዮጵያ ማበደር ይችላል ።
Re: አፍሪካ እንደ አሜሪካ ለምንድን ነው የነጮች አህጉር ያልሆነችው?
https://en.wikipedia.org/wiki/File:Ongo ... _world.svg
ማኙና ሊስቱን ይመልከቱ።
በአንድ አገር ውስጥ የርስ በርስ ጦርነት፤ በአገሮች መሃከል፤ ኢምፒሪያሊስቶች በአፍጋኒስታን ወዘተ ብለን መከፋፈል እንችላለን። አፍሪካ፤መካከለኛው ምስራቅ፤ ደቡብ አሜሪካ ኤዥያ ...ሁሉም 3ተኛ አለም የሚባሉ አገሮች። ለምን? የጦር መሳሪያ ገበያና ጥቁርና ኋላቀር በመሆናቸው ...
ማኙና ሊስቱን ይመልከቱ።
በአንድ አገር ውስጥ የርስ በርስ ጦርነት፤ በአገሮች መሃከል፤ ኢምፒሪያሊስቶች በአፍጋኒስታን ወዘተ ብለን መከፋፈል እንችላለን። አፍሪካ፤መካከለኛው ምስራቅ፤ ደቡብ አሜሪካ ኤዥያ ...ሁሉም 3ተኛ አለም የሚባሉ አገሮች። ለምን? የጦር መሳሪያ ገበያና ጥቁርና ኋላቀር በመሆናቸው ...