ENSET: THE MOTHER OF ETHIOPIAN ECOLOGY & SUPER FOOD
Enset is the pillar of Green Ethiopia revolution. Enset will be the 2nd largest food export next to Teff.
Re: ENSET: THE MOTHER OF ETHIOPIAN ECOLOGY & SUPER FOOD
ኢትዮጵያ ሱዳኖች እንደ ሚሉት የዉሃ ቦምብ የታጠቀች አገር ነው ። ይህ ደሞ አረንጓዴ ምድር ባሰፋን ቁጥር የዝናብ መጠን እየላቀ ይሄዳል ። ዛሬ በታወጀው መሰረት በሚቀጥለው የበጀት ዘመን 100 ትናንሽና መካከለኝ ግድቦችን ኢትዮጵያ ጸራለች ። እነዚህ የመስኖም ሌላም አይነት የትናንሽ (diversified small scale) ግድቦች ማለት ነው።
ይህን መሰል አገር አቀፍ የመስኖና አረንጓዴ ምድር ንቅናቄ ዛፍ ብቻ ሳይሆን እንሰትን በደጋ፣ ወይና ደጋ እና ከፊል ቆላ በሆኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉ ይለማል ማለት ነው። በቅርብ ግዜ እስከ 50% የኢትዮጵያ ሕዝብ መደበኛ ምግብ ቆጮ ይሆናል ። የቆጮ ዳቦ፣ እንጀራ፣ ኬክ፣ ገንፎ፣ የቆጮ ብስኩት፣ እና የቆጮ ጭማቂና መጠጥ በቅርብ የምናያቸው እድገቶች ናቸው !
በሁልገብ ጥቅሙ በኢትዮጵያ የሰብልና እጸዋት አለም እንሰትን (ኧሰት) የሚያክል እጽ የለም !
ብዙ ተአምር ለማየት እንዘጋጅ !!
ይህን መሰል አገር አቀፍ የመስኖና አረንጓዴ ምድር ንቅናቄ ዛፍ ብቻ ሳይሆን እንሰትን በደጋ፣ ወይና ደጋ እና ከፊል ቆላ በሆኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉ ይለማል ማለት ነው። በቅርብ ግዜ እስከ 50% የኢትዮጵያ ሕዝብ መደበኛ ምግብ ቆጮ ይሆናል ። የቆጮ ዳቦ፣ እንጀራ፣ ኬክ፣ ገንፎ፣ የቆጮ ብስኩት፣ እና የቆጮ ጭማቂና መጠጥ በቅርብ የምናያቸው እድገቶች ናቸው !
በሁልገብ ጥቅሙ በኢትዮጵያ የሰብልና እጸዋት አለም እንሰትን (ኧሰት) የሚያክል እጽ የለም !
ብዙ ተአምር ለማየት እንዘጋጅ !!
Re: ENSET: THE MOTHER OF ETHIOPIAN ECOLOGY & SUPER FOOD
የእንሰት ክፍሎች ስም በክስታኔ ጉራጌኛ፡
1 ኧሰት = እንሰት
2 ኧኩሳ = ቆጮ
3 አጥሚጥ = የቆጮ አጥሚት፣ ከእንሰት እምቡጥ ተጨምቆ የሚወጣ ክሪም ኦፍ እንሰት (cream of Enset)
4 ቡላ = የቆጮ ዱቄት
5 ጉንስ = የቆቾ ቂጣ (እንጀራ)
6 አልበበጫት = በጣም ስስና ለስላሳ የቆጮ እንጀራ
7 እርግፎን = የተቆላ ቆጮ (roasted kotcho)
8 ተጋን = የእንሰት ተክል ማሳ፣ ተጋን ማለት በሴም ቋንቋ ጋርደን (garden) ማለት ነው
9 ማራ = በረድፍ የተተከሉ እንሰቶች መስመር
10 ችግኝ = ትናንሽ ችግኞች
11 ሱማ = ተለያይተው በተርታ የሚተከሉ ታዳጊ የእንሰት እጽዋት
12 ቅጠል = ቅጠል
13 ጥረት = የእንሰት ቅጠል በእሳት በማለስለስ የሚሰራ የክትፎ ማቅረቢያ
14 ትምቦሽላ = የቅጠሉ ጀርባ አጥንት፣ ለቃጫ ምርትና ለማገዶ የሚውል ። እርጥብ ትምቦሽላ ልጆች እንደ ነፍጥ ሰርተው የዉጊያ ጨዋታ መሳሪያ
15 ቀስላ = የሚፋቀው የእሰት ልጣጭ
16 ኮባ = የደረቀ ቀስላ፣ ለጂበ፣ ቅጭቀጨ፣ ወደረ መስሪያ የሚውል
17 ኧዉታ = የእንሰት ስር (አሚቾ) ወይም የእንሰት ድንች
18 ሙካ = አንድ የዉታ ጉማጅ እንደ ድንች ተቀቅሎ የሚበላ
19 ሰንዳ = ሳንጃ፣ ባለሁለት ስለት የእንሰት መቁረጫና ቆጮ መክተፊያ
20 አጋት = የቆጮ መቀጥቀጫ ሹል የአጥንት መዶሻ
21 ዎለት = ባለሁለት ማረሻ መደቅደቂያ መሳሪያ
22 ዋታ = እንሰት መፋቂያ ጠፍጣፋ እንጨት (ቦርድ)
23 ጂበ = ከኮባ የሚሰራ የእልፍኝ ምንጣፍ
24 ቅጭቀጨ = ከኮባ የሚሰራ የለት ተለት ምንጣፍ
25 አንጮት = ከቃጫ የሚሰራ ምርጥ ምንጣፍ (ለበአል ቀን ብቻ የሚነጠፍ)
24 ድድቅ = የእንሰት ቁፋሮ (የወንዶች ስራ)
25 ዎኔቦ = የድድቅ ደቦ
26 ዉሳቻ = የሴቶች የእንሰት መፋቅ ደቦ
እያለ ይቀጥላል ..።