Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ከቀይባህር ጋር አንድ ኢንች የማትዋሰነዋን ሀገር፥ ቀይባህርን የችግሮቿ ሁሉ መፈልፈያ ምክንያት አድርጎ የሳለ መግለጫ የሚሰጥ መንግስት ስታይ፥ ያቺ ሀገር ላታገግም መታመሟን ትታዘባለህ።"

Post by sarcasm » 29 May 2021, 10:04

========== "የምጣዱ እያለ፥ የእንቅቡ ተንጣጣ" ==========

ከቀይባህር ጋር አንድ ኢንች የማትዋሰነዋን ሀገር፥ ቀይባህርን የችግሮቿ ሁሉ መፈልፈያ ምክንያት አድርጎ የሳለ መግለጫ የሚሰጥ መንግስት ስታይ፥ ያቺ ሀገር ላታገግም መታመሟን ትታዘባለህ።

የቀይባህር ባለቤት የሆኑ ጎረቤት ሀገራት እንኳ፥ ቀይባህር የሀገራቸውን ከሌላው ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት ቅርፅ በማስያዝ ረገድ በዚህ የኦሮሙማው መንግስት በገለፀበት መንገድ አልገለፁትም።

"አልሰማሁም፣አልሰማሁም" ነበር ያለችው ሙሾ አውራጇ። "ቀይባህር ኬኛ" መሆኑን አልሰማንም ነበር አልሰማንም.....😪😥😥

ዴቭ ዳዊት።
Please wait, video is loading...