Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

The best and fitting criticism against Dr. Abey Ahmed’s government- “ የዶር አብይ መንግስት ወንጀለኛ ያደልባል!"

Post by Y3n3g3s3w » 20 May 2021, 19:09

The best and fitting criticism put forward against Dr. Abey Ahmed’s government
“ የዶር አብይ መንግስት ወንጀለኛ ያደልባል”
ከስድስትና ሰባት ወር በፊት (ወያኔ እንደዱቄት ሲቦን ከማየታችን በፊት ማለት ነው) በለዉጡ ኃይል ላይ የነበረኝ ትግስት እየተንገዳገደብኝ በተለይ የዶር አብይ መንግስት በወያኔ ላይ የሚያሳየዉ ትግስት በጣም የተለጠጠ ስለመሰለኝ "do you know the difference between a PM and a pastor?" ብዬ መሞነጫጨሬን አስታዉሳለሁ::

ይሁን እንጂ ያን ማለቴ ፀፅቶኝ አያቅም ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወያኔን የዶጋመድ ካረጉ በሁላ ፓርላማዉ ላይ ብቅ ብለዉ የነበረባቸዉንና ያለፉትን ከባድ ፈተና በዝርዝር ተናግረዉ እጄን አፌ ላይ እስኪያስጭኑኝ ድረስ(ገና ዛሬ ነዉ እጄን ከአፌ ላይ አንስቼ ስለ ጠቅላዩ መናገር የጀመርኩት) መንግሥታቸዉ በቂ ኃይልና ደህንነት እንዳለዉ ነበር የተረዳሁት:: ለዛም ነበር እንዴት ይሄን አያደርጉም: አላደረጉም እንያልኩ ስንጫጫ አጅሬዎቹ ለካ ነፍስ ግቢ ነፍስ ዉጭ ሥራ ላይ ነበር::

አሁን ነገሮች አየተገለጡ መጡ: አንዳንድ ወንጀለኞችንም ለምን እንደሚያደልቡ ከሞላ ጎደል እየገባኝ ነው::

ዞሮ ዞሮ አሁንም የዶር አብይ መንግስት እንደጀመሩት ብልሃት የተሞላበት: ነገር ግን ቆፍጠን ከማለት ሌላ ምርጫ የላቸዉም ::

እነዚህን የጋርዮሽ ስርዓት አስተሳሰብ የያዙ ያዉም ተቀጣሪ ወይም ተላላኪ ካዲ የጎሳ ፖለቲከኞች (ሸኔ); አስመሳይ የድል አጥቢያ ጀግኖችና የጎሳ ፖለቲከኞች (አብን)ና የበግ ለምድ የለበሱ የብልፅግና አመራሮችን አሁን በያዘዉ የሰለጠነ ፖለቲካ ብቻ አደብ ማስያዝ አዳጋች ነው የሚሆንበት:: ሕግ ማስከበሩ በዘገየ ቁጥር የሚከፈለዉም ዋጋ ከፍ ያለ ነው የሚሆነዉ:: የሆነ ቦታ ላይ ወንጀለኞች ሳይጠበድሉ ከስርከስር ባጭሩ መቅጨት የሚያስፈልግ ይመስለኛል( Jawar Mohammed is a living example)::

ይገባኛል; በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ከዉጭ ኃይሎች ጋር እየተገዳደረች ባለበት ሁኔታ ስለልዩነት ሳይሆን ስለአንድነት ነዉ መሰበክ ያለበት ነገር ግን ከዉጭ ኃይሎች ጋር ለሚደረገዉ ትግል ባንዳዉ ሁሉ ተለይቶ መታወቅ አለበት; ከዛ በተጨማሪ በተለይ ከምርጫ በሁላ ሕዝብ ሰላም በማንኛዉም ወጭ የሚፈልግ ይመስለኛል::

ለማንኛዉም ለምርጫዉ በሰላም ያድርሰን; ምርጫዉንም ብልፅግና ያሸንፍ::

ለምን??

1. ወያኔ በ30 ዓመት ያልሰራዉን(ወያኔ ግን 30 ዓመት ሰራ ነዉ ሰረቀ ግራ ያጋባል አደለ? ) በ3 ዓመት ዉስጥ ብልፅግና ያከናወነዉን አጢነህ/ሽ ተመልከት/ቺ !
2. የብሔር ግጭት አላስቆመም??
እሱማ በ30 ዓመት ዉስጥ ትልቁ ወያኔ ያከናወናቸዉ ስኬቶች ናችዉ; የዶር አብይ መንግስት ወያኔ እዛም እዛም የለኮሰዉን እሳት በማጥፋት ግዜዉን ባያጠፋማ ምን ያህል እንደምያስገርመን መገመት ይቻላል !

“ የዶር አብይ መንግስት ወንጀለኛ ያደልባል” (ስዩም ተሾመ ); ቢሆንም ቢሆንም

ኢዜማን በልቤ ብልፅግናን በእጄ


Last edited by Y3n3g3s3w on 21 May 2021, 15:36, edited 1 time in total.


Post Reply