Please wait, video is loading...
(አባሪ አንድ፣)
ከሁለት ወር በፊት፣
የአደባባይ ሚዲያ ጋዜጠኛ( ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ) :-
" የኤርትራ ጦር ትግራይ ገብቷል? ጦርነቱን እየተሳተፈ ነው?"
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት(መልስ)፡-
"አሃሃ! ቅድም ብዬሃለሁ። ሰዎቹ ኢትዮጵያን አያውቋትም። ኢትዮጵያ እኮ ከ10ሺህ በላይ ጦር ደቡብ ሱዳን ያሰማራች አገር ናት። ከቸገራት እሱን ታመጣለች።ለምን ከኤርትራ ትወስዳለች?ለምን? የኢትዮጵያ ጦር እኮ ሶማሊያ አለ። የኢትዮጵያ ጦር እኮ ማሰልጠኛ ውስጥ አላት። ኢትዮጵያ እኮ ህዳሴ ግድቡን የሚጠብቅ አንድ ትልቅ ክፍለጦር ያላት አገር ናት። ይሄን ማንቀሳቀስ ትችላለች። እንደው ይችን ሀገር እንዴት አድርገው ቢገምቷት ነው?ሁሉንም በጥቅምት 24 የጨረሱት መሰላቸው እኮ!...ከዛም በላይ እኮ ኢትዮጵያ ግፉ ሞልቶ በእግዚአብሔር ዘንድ ሲፈስ የማይታይም ጦር አላት። የሚታይ ብቻ አይደለም። እናም ከሚታየው እና ከማይታየው ጦሯ አቅም በላይ የሆነ ነገር የለም። ብድር አትሄድም። ኢትዮጵያ ሳይቸግር ጨው ብድር አትሄድም!።"
***
(አባሪ ሁለት)
ከሁለት ወር በኋላ፣
የEthiotube ጋዜጠኛ፣
" የኤርትራ ጦር አልገባም የሚለው ሚዲያ ላይ የተናገርከው ነገር ነው። የኤርትራ ጦር መግባቱን ደግሞ አለም ያየው ነው። የዛን ግዜ ያልክበት ምክንያት ምንድነው?"
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣
"እኔ የኤርትራ ጦር አልገባም አላልኩም። ሰው የሚፈልገውን ስለሚሰማ እንጂ በወቅቱም የተጠየቀው ጥያቄ <<የኢትዮጵያ ጦርና የኤርትራ ጦር ግንባር ፈጥረው ነው እያጠቁ ያሉት፤ የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ጦር ሊያግዝ ነው የገባው?>> የሚል ጥያቄ ነው የተነሳው። ወደ ኃላ ሄደህ ማዳመጥ ትችላለህ። እኔ ያልኩት የኢትዮጵያ ጦር የራሱን ስራ ለመስራት ይበቃል። የኤርትራን ጦር እገዛ አልፈለግንም። ስለዚህ ሁለቱ ግንባር ቀድመው አልታገሉም። ወይንም ደግሞ የኤርትራ ጦር እኛን ለማገዝ አልገባም።"
ጋዜጠኛ፣
"ለማገዝ ካልሆነ የኤርትራ ጦር እስከ አድዋና አክሱም እንዴት ደረሰ?"
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣
"እኛን ለማገዝ አይደለም! ራሱን ለመከላከል ነው የገባው"
ጋዜጠኛ፣
" እስከ አድዋ? አክሱም?"
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣
" አዎ! አክሱም፣ አድዋ ከኤርትራ ድንበር ስንት ኪሜ ነው? ይሄን በመድፍ፣ ታንክ፣ ሮኬት ርቀት አስበው! እንደ ሲቪል ሳይሆን እንደ ወታደር። በአንድ የመድፍ ርቀት የሚሸፈን እኮ ነው።"
