አጣሁት ፈልጌ!
ስመኘው በቀለ አሳምነው ጽጌ፡
በነ አምባቸው ሞት በርግጌ በርግጌ፡
በነ ሰዓረ ሞት በርግጌ በርግጌ፡
በነ ሓጫሉ ሞት በርግጌ በርግጌ፡
አመራር ልጠይቅ ቁጭ ብዬ በግርጌ፡
ፋሲካ አሳልፌ ልጋብዘው ሰርጌ፡
ያዳሙን አበረን አጣሁት ፈልጌ፡
እንግዲህ ምን ትዪ ኡራ ሆንሽ ዘጌ!
[ዝክረ ባህርዳር - ኤርትራዊ ግጥም]
Re: አጣሁት ፈልጌ! [ዝክረ ባህርዳር - ኤርትራዊ ግጥም]
Meleket wrote: ↑16 Oct 2018, 11:22ዱለቷን መረጠ
አዲስአቤ ሁሉ ፍቅር ቢለግሰው፣
ያስመራ ሰው ሁሉ ፍቅር ቢለግሰው፣
እንዲም እንዲያም ብለን ብናንቆለጳጵሰው፣
ያያ አሕመድ ልጅ ምንም አልመሰለው።
እኛ በቦንብ ቆስለን ክብርን ብንሰጠው፣
ትልቁን ፍሪዳ አጋድመን ጋብዘነው፣
የዝናሽ ባልተቤት ጠቅላዩ ቆፍጣናው፣
በያይነቱ ምግብ አቅርበን ብንሰጠው፣
ይችንም ያችንም ሁሏን የቀመሰው፣
በኮልታፋ ምላስ እየተቅበጠበጠ፣
ያያ አሕመድ ልጅ ዱለቷን መረጠ።
አፋጣኝ ፍትሕ ለአዲስ አበቤዎች!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
Re: አጣሁት ፈልጌ! [ዝክረ ባህርዳር - ኤርትራዊ ግጥም]
Meleket wrote: ↑17 Oct 2018, 12:18ያያ ኣሕመድ ልጅ “ዱለቷን” መረጠ
ትርጉም አንድ - ያያ ኣሕመድ ልጅ ምርጥ ሆና የተሰራችውን ዱለት መረጠ። ከወጡ ሁሉ እጅግ ጣዕም የነበራትን “ዱለት”ን ለራሱ መረጠ። ምርጥ ምርጡን ላያ ኣሕመድ ልጅ።
ትርጉም ሁለት - ያያ ኣሕመድ ልጅ “ዱለታዋን” መረጠ - መዶለት መረጠ- ዶለተ። በተለይ ሃገሬን ኤርትራን በተመለከተ ጉዳይ በሃገሬ በኤርትራ የነበሩ ማናቸውም ኢትዮጵያዊያን የታጠቁ ሃይሎች (እነ አርበኞች ግንቦት 7፣ ኦነግ ፣ የትግራዩ ደምህት ወዘተ) አንድ ባንድ ወደ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ትጥቃቸውን እየፈቱ ሲገቡ፣ በ “ያያ ኣሕመድ ልጅ” የሚታዘዘው ሰራዊት ማለትም ኢትዮጵያዊ ሰራዊት ግን እስከ ዛሬ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ከሃገሬ ከኤርትራ አልወጣም፣ ለፍትሕ አልታዘዘም። ጭራሹኑ “ያያ ኣሕመድ ልጅ” ዱለታ መርጧል። አሜሪካ ላይ ስለ አሰብ ሲጠየቅም “ዶማዉን ዶማ አላለም”። በአፉ እተገብረዋለው ያለውን ውልም እስከ ዛሬ አልተገበረም። የራሱን አገር የሚመለከት ጉዳይ “ፈጠን ፈጠን” እያለ ሲተገብር፣ የኛዋን ኤርትራ የሚመለከት ትልቁን የቤት ስራዉን ግን ገና አልተገበረም፣ እንደ ቃሉ ሆኖ አልተገኘም። ዱለታ መረጠ።
ጦቢያን በተመለከተ ደግሞ፣ ያያ ኣሕመድ ልጅ “ዶልቶ”፣
አዲስአበቤዎችን ወደ ጦላይ፣
ምክትል ጠቅላዩን “በተቀነባበረ ዱለታ” በወታደር ማስደንገጥ፣
በስልጣን ክፍፍሉም አዲስ አበቤዎችን በማግለል መወሰን፣
“ለጣናና ለላሊበላ እንዲሁም ሌሎች ቅርሶችና እሴቶች የሚቆረቆሩትን በማግለልና ከጨዋታ ውጭ በማድረግ" እሱ ብቻ ብልጥ ለመምሰል ሞከረ፣ ነገርም “ዶለተ” ማለት ይቻላል።
እርካብና መንበር ከሚለው “ያያ ኣሕመድ ልጅ” ጻፈው ከተባለ መጣፍ የተወሰደ ጥሑፍ እስቲ እንጥቀስ
“እንደ ውሻ፣ ጠላት ላይ በመጮህ ማምለጫን ማመቻቸት ዘላቂ መፍትሄ ባይሆንም ለጊዜው ይጠቅማል። ምክንያቱም እንዳይመለስ ሆኖ ያልተሸኘ ጠላት ጊዜ ጠብቆ ዳግም ለማጥቃት እንደሚመጣ ጥርጥር የለውምና። ታዲያ ጊዜው ሲደርስ ልክ እንደ ነብር ኮቴን ሳያሰሙ ከጀርባ ቀብ ማድረግና ህልሙን ባንድ ጀንበር ማምከን መረሳት የለበትም፤ ወይም ስውር የሆነ ወጥመድ ማዘጋጀት ይበጃል። ሰዎች ራስ ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው። የሚፈልጉትን ነገር እያሳየህ ወደ ምትፈልገው ስፍራ ውሰዳቸውና ጣላቸው። ከዚያም “በሬ ሆይ! ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” የሚለውን ተረት ተርትባቸው። ይህን መሰሉ ለዘብተኛ የኃይል አጠቃቀም ዘዴ ሠላም ሳይበጠበጥ ህዝብም ሳያጉረመርም የተደላደለ ስልጣን ባለቤት ለመሆን ያግዛል።”
እኛ ኤርትራዉያን የደንበሩ ብይን፣ “እንዳይመለስ ሆኖ እንዲሸኝ እንፈልጋለን”። ለምን ቢባል ጊዜ ጠብቆ ዳግም ለማጥቃት እንዳይመጣብን፣ ድንበራችን በፍቅር አሁኑኑ እንዲሰመር በጨዋ ደንብ ህሊና አለኝ የሚለውን የጠቅላዩን መንግስት እንጠይቃለን።
እኛ ኤርትራዉያን “በሬ ሆይ! ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” ተብሎ እንዲተረትብን አንፈቅድም። በምንምም አንደለልም።
ሰላም ሳይበጠበጥ ህዝብ ሳያጉረመርም ስልጣንን ማደላደል የሚለው መርህ፣ ኤርትራዊን በሆዱ በመደለል ተግባራዊ አይሆንም። ሕሊና ያለው ኤርትራዊ በጤፍና በበርበሬ አይደለልም። ጠቅላይ ኣብይ “ዱለታው” ኣያስኬድምና ደንበራችንን አሁኑኑ መሬት ወርደው ያስምሩ፣ ሰራዊትዎንም ከኤርትራ ምድር ልክ እንደነ ኦነግና ደምህት ከኤርትራችን ምድር ያውጡ።
ክቡር ጠቅላይ “ይቅርታ ያድርጉልንና” ሰራዊትዎን ከሃገራችን ምድር እስኪያወጡ፣ እኛ ኤርትራዉያን “ትንሽ እንቅልፍ እንነሳዎታለን” ምክንያቱም ሰራዊትዎ በአሁኑ ወቅት ለአንዲት ቅጽበትም ትሁን በኤርትራ ምድር ሊቀመጥበት የሚችል ምንም ዓይነት ምኽንያት የለምና። ማንኛውም የባዕድ ሰራዊት በሀገራችን እስካለ ድረስ ለህሊናችን የምንገዛ ኤርትራዉያን ድምጣችንን አጉልተን በማሰማት ከኅሊናዎና ከቃልዎ ጋር እስኪታረቁ ድረስ እንቅልፍና ሰላምዎንም እንነሳወታለን።
አሁንም አፋጣኝ ፍትሕ ለአዲስ አበቤዎች!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!