Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"እኔ የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር እንጂ በጠላት ኣልተከበበም ብዬ ነበር። ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስበው ግን ተከቦ እንደነበር አየሁ እና ቆጨኝ ተፀፀትኩኝ" ይሳቅ ወልዳይ የፈንቅል አመራር

Post by sarcasm » 26 Apr 2021, 09:13

የትግራይ ህዝብ በጠላት ተከቦ ኖሯልን፧ እኔ ይሳቅ የፈንቅል አመራር የትግራይ ህዝብ የተከበበው በኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር እንጂ በጣላት አይደለም ብዬ አምን ነበር፤ አምን ነበር ብቻ አይደለም እውነት ነው ብዬ በሚድያም ተናግርያለሁ። ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስበው ግን ተከቦ እንደነበር የሚያሳዩ ፍንጮች አየሁ እና ቆጨኝ ተፀፀትኩኝ።

ተፃፈ በ isaac welday የፈንቅል አመራር
የመቐለ ቆይታዬ ክፍል ሁለት


ይህንን እውነት ስፅፍ የሚከፋችሁ ካላችሁ ይህ መራራ እውነት ስለሆነ ምንም ማድረግ አልችልም።
መቐለ መቐለ ብቻ ለምን አበዛህ የሚል ጥያቄ ይነሳ ይሆናል በትግራይ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር በመነሳት ተዘዋውረህ ማየት የሚያስችል እድል ባለመኖሩ



¤ በትግራይ ህግ የማስከበሩ ተግባር ከተጠናቀቀ በኋላ ያለው ነባራዊ ሁኔታ


~ ጦርነት ሊያስከትለው የሚችል ችግር እና ጠባሳ ምን እንደሆነ ይታወቃል ። ይሁን እንጂ ከጦርነቱ ማግስት ሁሉም ወደነበረው መመለስ ሲገባው የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ(ህግ የማስከበሩ ተግባር) ከተጠናቀቀ በኋላ የደረሠበት ግፍ እና እንግልት እስከ ሊባል የሚችል አይደለም መገለጫውም እናቶች ተገድለዋል ሴቶች ተደፍረዋል ህዝባዊ ተቋማት ወድመዋል እነዚህ ህግ የማስከበሩ ተግባር ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑን መዘንጋት የለበትም። አንተ መቐለ ከተቀመጥክ ይህንን መረጃ ኬት አመጣሀው የሚል ጥያቄ ይነሳ ይሆናል ? መልሱ ቀላል ነው በመቐለ አብዛኛው ት/ቤት ግቢ ውስጥ በተፈናቃይ ተጥለቅለቀዋል እነዚህ ተፈናቃዮች ቀን ጥሏቸው እንጂ በነበሩበት ሃብት አፍርተው ጎጆ ቀልሰው ሲኖሩ የነበሩ ብርቱ ተጋሩ ነበሩ አሁን ቀን ጥሏቸው የሲቃ እንባ ሲያነቡ ያማል ለዚህ የዳረጋቸው ጁንታው ነው የሚል ጥያቄ ከተነሳ መነሻው አዎ ብልም የኋላ ኋላ ግን ለዘመናት የትግራይ ህዝብ ለመውረር እና አንገት ለማስደፋት ሲዘጋጅ የነበረ ተስፋፊ ሃይል እንደነበር ተረዳሁ።

የሰሜን እዝ ስቃይ ሞት እና ሰቆቃ የትግራይ ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ ከቀንበር ነፃ ለማውጣት ነው። ይሁን እንጂ ይህንን በሚፃረር መልኩ በትግራይ የነበሩት የፀጥታ መዋቅር ከፈረሱ በኋላ የትግራይ ህዝብ ወደ ባርነት የሚያስገባ ተግባር ሲከወን አየሁ ሰማሁ ጎበዝ ወዴት እያመራን ነው በአፋችን እማማ ኢትዮጵያ እያልነሰ በተግባር የኢተትዮጵያ ምሶሶ የሆነውን የትግራይ ህዝብ እንዲሰቃይ እንዲራብ እንዲፈናቀል ወዘተ ማድረግ ይህ ከሆነ ኢትዮጵያዊነት እኔ ኢትዮጵያዊነትን ጠላሁት እኔ ስመካበት የነበረው የአባቶቼ ኢትዮጵያዊነት ስሜት ከወዴት ጠፋ አልኩኝ ትግራዋይ በኢትዮጵያውያን ተገደለ ተዘረፈ እህቶች ተደፈሩ አራሶች ከነደማቸው ከቀዮቸው ተሰደዱ በመንግስት በተጠናው ጥናት በቢልዮን የሚቆጠር የትግራይ ሀዝዝብ ሃብት ወድመዋል ተዘርፈዋል በማን የሚለው ባይገለፀም እኔ ግን በማን እንደሆነ እገልፃለሁ በተስፋፊ ሃይል እና በኤርትራ ወታደር ተዘረፈ ይህ ብቻ አይደለም አንዳንድ ስንምግባር የሌለው የሃገር መከላከያ ሠራዊት ተሳትፎም እንዳለው መዘንጋት የለበትም።

ይህንን ተከትሎ ታታሪው እና ሰራተኛው የትግራይ ህዝብ ለርሃብ ተጋለጠ ለስደት ተጋለጠ አንገት እንዲደፋ ተሞከረ አንገት ለመድፋት የሚያስችል ቁመናና ስነልቦና ባይኖረውም

¤ የእውነት የትግራይ ህዝብ በጣላት ተከቦ ንሮዋልን !!!!!!!


እኔ ይሳቅ የፈንቅል አመራር የትግራይ ህዝብ የተከበበው በኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር እንጂ በጣላት አይደለም ብዬ አምን ነበር አምን ነበር ብቻ አይደለም እውነት ነው ብዬ ለታሪክ በተቀመጠው በሚድያም ተናግርያለሁ። ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስበው ግን ተከቦ እንደነበር የሚያሳዩ ፍንጮች አየሁ እና ቆጨኝ ተፀፀትኩኝ ይሁን እንጂ ወዳጆች እንዳሉት ግን ቀጥዬ በምፅፈው ፅሁፍ እገልፀዋለሁ።

¤ የማይካድራው ጨፍጫፍ

በመጀመርያው የማይካድራው ጨፍጫፍ በንፁሃን የተፈፀመ ስለሆነ እኔ እንደ ዜጋ አወገዝኩት አወገዝኩት ብቻ አይደለም በሚድያም ገለፅኩት በሚድያ ገለፅኩት ብቻ አይደለም በፌስቡክ ገፄ ለጠፍኩት ይህንን ይሳቅ ብቻ ሳይሆን ሚድያዎቹ ተቀባበሉት ከዛስ ምን ተፈጠረ?

ከዛማ ለዚህ ምላሽ ይሆን ዘንድ በአማራ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ በንፁሁ ትግራዋይ የተፈፀመው ግድያ ለቁጥር አዳጋች ነው ትግራዋይ በአከባቢው እስኪፀዳ ድረስ ተፈፅመዋል። ይህ የማይካድራ ንፋስ ምስክሬ ነው ይህ የማይካድራ አድባር ምስክሬ ይሁን በማለት ልዝጋው።

¤ የቁርጥ ቀን የትግራይ ህዝብ ወዳጅ

በዚህም የእውነት ኑዛዜየን ላስቀምጥ የአማራ ህዝብ የትግራይ ህዝብ ጎረቤት ብቻ አይደለም ብዬ አምናለሁ። ይህንን በተግባር ማየት ግን ተቸገርኩኝ ይህንን በሚፃር መልኩ ግን የትግራይ ህዝብ ሲዘርፉት ሲያሳዱድት አየሁ ግን ይህንን ከህዝቡ እንዳይነካካ እኔ ከሙሁራኑ እና ከአማራ ብልፅግና መራሹ ልዩ ሃይል ነው ያልኩት ትናንትና ያሞገስኩት የአማራ ልዩ ሃይል ዛሬ ላይ ባስተማረኝ እና ባሳደገኝ ህዝብ ላይ በደል ሲፈፅም አፈርኩኝ አፈርኩኝ ብቻ አይደለም ፀፀተኝ ይህ ስል ግን ኢትዮጵያውያን ትግራዋይ ሲራብ አልደረሡም ማለቴ አይደለም እነማን ደረሡ ካልን ግን የአንበሳው ድርሻ የሚወስዱ መግለፅ ተገቢ ነው።

¤ የአባ ገዳ ልጆች

ትግራዋይ በተቸገረ ጊዜ በተራበ ጊዜ ቀድሞ የደረሠው አባገዳ እና እና ሃደ ስንቄ የመራው የኦሮሞ ህዝብ የአንበሳው ድርሻ ይወስዳል gelettommaa ya guddaa waqqeyyo si ebessuu እላለሁ። ቀጥሎም ብሄር ብሄረሰቦች ሁሉንም የቻሉት አድርገዋል ከአማራ መንግስት በስተተቀር።

¤ የፈንቅል ትግራይ የወጣቶች እንቅስቃሴ አባላት ከህግ ማስከበሩ ማግስት

የፈንቅል አላማ ጨቋኝን እና ዘራፊ አስወግዶ ፍትህ ማስፈን እንጂ ሌላ ዘራፊ መተካት አልነበረም ውዶች የፈንቅል ትርጉም ለማስታወስ ተገደድኩኝ
~ እምቢ ለባርነት እምቢ ለሌቤነት ነበር ታድያ ይህንን ለማስታረቅ የሚችል ሃሳብ ሲያጣ አማራጭ ሲያጣ አመራሮቹ ሳያማክር ወደ በርሃ ወርደዋል


¤ አሁን ያለው ጦርነት በጁንታው እና በመከላከያ ወይስ በትግራይ ህዝብና በመከላከያ ??????? ቀጣይ ፅሁፌ እና ክፍል ሦስት እመለስበታለሁ

ቸር ያቆየን


Please wait, video is loading...