በመጀመርያ ደረጃ እዚህ አገር በጣም ተቀባይነትን ካገኘ ሰው መካከል አንዱ መስጠፌ( ተሳስቼ ይሆን?) ነው:: ጠቅላይ ሚንስትር ቢሆን የሚለው ሕዝብ ቁጥር የትየለሌ ነው:: ስለአማራ በመቆርቆር የሚናገራቸው ነገሮች በሕዝቡ ዘንድ ትልቅ ቦታን እንዲያገኝ አስችሎታል:: አብይ እና እሱ ቢወዳደሩ የሚያሸንፍ ይመስለኛል:: ብቻ የዚህ ሰው አጨራረሱን ማየት ነው:: አደጋ ላይ እንዳይወድቅ እሰጋለሁ::
ከሁሉም በላይ ያ የሲኦል ምድር የነበረውን የሶማሊ ክልል የተረጋጋ ማረጉ በጣም አሳገራሚው ነው:: ለምን ኦሮምያ እንዲህ አልሆነም? የአብይ ስህተት ይመስለኛል:: መሪው አመራረጡ አለ ወይም ከራሱ አብይ ችግር አለ::
ወደ ዋናው ጉዳይ ስገባ :
የሚናገራቸውና የሚሰራቸው ነገሮች የተመታታ ሆነብኝ:: በጣም ለሚርቀው አማራ ሲቆርወቆር የሚቀርበውን አፋርን ግን መግደልና ማዋረድ ለምን ፈለገ?
እኔ እሱ በብሄረሰብ የሚያምን አልመሰለኝም ነበር: እና በማይረባ መሬት ለምን በመቶ የሚቆጠር ሕዝብ ያልቃል?