የተለያዩ ከባድ የጭነት መኪኖች ሲወጡ ለአንድ መኪና 60 ሺህ ብር ጉቦ እያስከፈለ የተገኘው አቶ ፋሲል በርሀ ብሩ ለዶ/ር ሙሉ እንደሚያካፍል ለመርማሪ ፓሊስ ቃል ሰጥቷል። ይሄ ጉድ እንዳይወጣ ይሄ ጉዳይ የያዘው መርማሪ ፖሊስ በማስፈራራት አንዴም ከስራ በማባረር አቶ ፋሲል ከእስር እንዲፈታም ትልቅ ግፊት ሲያደርግ የነበረው የዶ/ር ሙሉ የድህንነት አማካሪ አቶ መኮነን መሆኑ ማጋለጣችን ይታወሳል። ይሄ ከባድ ወንጀል ተድበስብሶ እንዲሄድ አቶ መኮነን ጫና ሲፈጥር ቆይቷል።
ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሾሙት የድህንነት አማካሪ ሁለት የአባት ስም በመጠቀም ማለትም አቶ መኮነን ገ/ዮሃንስ / አቶ መኮነን ገ/ሊባኖስ በሚል ሁለት ፔሮል ላይ ሲበላ የከረመ ሰው ነው።
አ/ቶ መኮነን ትላንት ማምሻው በቁጥጥር ስር ውሏል። ወንጀሎኞች እና የጁንታ ርዝራዦች ማጋለጡ ይቀጥላል ሴረኞች የጊዜ ጉዳይ እንጂ ከህግ በላይ መሆን አይችሉም።
በጀግና የሃገር መከላከያ የተገኘ ለውጥ ሊቀለበስ አይገባውም!

