Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15332
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ጽድቅ እንደ አብርሃም አገር ፍቅር እና ዐርበኝነት እንደ እስክንድር ነጋ

Post by Abere » 28 Mar 2021, 12:14

ጽድቅ እንደ አብርሃም አገር ፍቅር እና ዐርበኝነት እንደ እስክንድር ነጋ። ለብዙዎቻችን ኢትዮጵያን ለምናፈቅራት አገራችን በድህነት ዐቅሟ ብዙ ስላደረገችልን ይሆናል ምናልባትም በተለይ ውጭ ለመንኖር ከ፩ኛ ድግሪ እስከ ሁለተኛ ድግሪ አስተምራን: ደግሳ ድራ :ልጅ ወልደን ስመን ክርስትና እና ልደት አክብረን ይሆናል። እስክንድር ግን ከዚህ የተለየ ነው። የተማረው ውጭ: ልጁን በእስር ቤት ብዙ ኑሮውን በባዕድ አገር ነበር። በዘመነ ትህነግ ሃብት በሙስና ተዝርፎ ጭምልቅልቅ ያለ ሃብታም በሚኮንበት ዘመን በንጽህና ለአገሩ እንደ ማንደላ የታገለ ዐርበኛ ነው። ለወያኔ ከስልጣን መባረር እና ለዛሬው የወያኔ ውድቀት ዋናው ኃይል እስክንድር ነበር። ከወያኔ ውድቀት በኋላ የ 6ወር ዕረፍት ሳያገኝ ተረኞች ጥርስ ገባ። ምክንያቱም ቀጣይ የግፍ ሴራ በመጋፈጡ። አንድ ጥሩ ንጹህ ሰው ስንት የጥፋት ማዕበል ማቆም እንደሚችል ከእስክንድር መረዳት ይቻላል እግዚአብሄርስ ስለአንድ ጻድቅ ሲል ብቻ ብዙ ኃጥያተኞችን ከጥፈት ይታገስ የለ። እስክንድር ለመስዋዕትነት እራሱን ባይሰጥ ኑሮ ይህን ጊዘ አዲስ አበባ ሌላዋ አሳዛኝ የማይካድራ ከተማ ነበርች። የሚያሳዝነው ግን እስክንድር በእስር ቤት ተዘግቶ በአገራችን ምህረት እና ሰላም ይወርዳል ብሎ ሰው ይገምታል። የንፁህ ዕንባ በግፍ በእስር ቤት ሲፈስ ሲያይ ውሎ ሲያይ የሚያድር እግዚአብሄር እንደት ሰላም ያመጣል። ለመበልፀግ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው። ይህ ዘመነ ጉግ ማንጉግ ነው እንደት እስክንድር ከአሳሪዎቹ እነ ስብሃት ነጋ ይታሰራል።

እስክንድርን በእስር ቤት ለማስገባት ዐብይ አህመድ የሞራል ብቃት የለውም። ዐብይ እወነተኛ ስብዕና ካለው እስክንድርን መፍታት አለበት። ኢትዮጵያዊ ወገኖቸ ለምን ወረተኛ እንሆናልን ከማይካድራ አይነት እልቂት እኮ ነው ቀድሞ ነቅቶ አዲስ አበባን የታደጋት። ዐብይ አህመድ መስራት የሚገባውን ስራ ሰለ ሰራ ነው የታስረው። ለመሆኑ ዐብይ አህመድ በእንዝ ህላልነት ወይም ዳተኝነት የወያኔን እና ኣኦነግን መቀመጫ ሲያስሽ ባይከርም ኑሮ እኮ በማይካድራ እና በለሎች ቦታዎች የተፈፀመው ግድያ ኣይኖርም ነበር። ዕውነት እንነጋግር እንጅ። ጄግና ለመደገፍ ባለመቻላችን ለወደፊቱ ክፉ ቀን ጀግና እናጣለን። እስክንድር ኢትዮዽያዊነት ብቻ ነው የእርሱ ጎሳ ፡ ብዙውን ወገናችንን ያጠቃው በሽታ ጎሳ አያውቅም።የዐብይ አህመድ ችሎታ የሚለካው የወደቀን ውየኔ ጥሎ መሞካሸት ሳይሆን የእወነት ዐርበኞችን በመምሰል ነው።