Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"የኤርትራ ወታደሮች የአክሱም ቤተ ክርስትያን ጳጳስ አቡነ መቃርዮስ ንብረት የሆነች ቶዮታ መኪና ዘርፈዋል" የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን

Post by sarcasm » 23 Mar 2021, 21:11

Excerpts from the report ...

የኤርትራ ወታደሮች ከወሰዱዋቸው ንብረቶች ውስጥ የአክሱም ቤተ ክርስትያን ጳጳስ አቡነ መቃርዮስ ንብረት የሆነች ቶዮታ መኪና ወታደሮቹ ኅዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ ሃገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ድረስ በመሄድ የወሰድዋት እና “የሃገረ ስብከቱ ንብረት የሆነች ኮድ 5 (ታርጋ ቁጥር 02223) መኪና 4 ጎማዎችንና አንድ የመኪናዋ ኮምፒተር በመፍታት እንደወሰዱ የቤተክርስትያኗ አገልጋዮች ለኮሚሽኑ ገልጸዋል። ሁኔታውን ለመከላከያ ሠራዊት አካላት ብናሳውቅም እስካሁን ምላሽ አላገኘንም” ብለዋል።

በሲቪል ሰዎች ላይ ከደረሰው የሞት እና የአካል ጉዳት በተጨማሪ የሃይማኖት ተቋማትና የግለሰብ መኖርያ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች የንብረት ጉዳቶች ደርሰዋል። ኅዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ገደማ እስከ ረፋዱ 11፡00 ሰዓት ቁጥራቸው ያልታወቁ የኤርትራ ወታደሮች በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ውስጥ ባለው የመቃብር አከባቢ ሆነው የቤተክርስትያኑን ሕንፃ ለማፍረስ በትግርኛ “ህረሞ ... ህረሞ ... “ (በለው... በለው)እያሉ በጥይት ሲደበድቡት እንደዋሉ ቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ተጠልለው የነበሩ የዓይን እማኞች ለኮሚሽኑ ገልጸዋል። (የተመታው የቤተክርስትያኑን ሕንፃ ስእል በረፖርቱ ተካትቷል)

ኅዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. በአክሱም ከተማ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ነዋሪዎች ለኮሚሽኑ ሲያስረዱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባሎችና ኃላፊዎች በከተማው ውስጥ እያሉ ጥቃቱን ባለመከላከላቸው ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል በማለት ገልጸዋል። በሌላ በኩል ከዚህ ክስተት በኋላ ታኅሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. የኤርትራ ወታደሮች ወደ አክሱም ቅድስት ማርያም ፅዮን ቤተ ክርስትያን ገብተው ለመዝረፍ ያደረጉትን ሙከራ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ህዝቡ ተባብሮ እንደተከላከለው ምስክርነታቸው የሰጡ ነዋሪዎች እና የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች አሉ።

https://www.facebook.com/permalink.php? ... 4253551816