ግዜ መስተዋት ነው ያሳል መልሶ
ማንነት ለይቶ ምስላችን ቀልብሶ፣
ያበራል አጉልቶ መልካችን ለይቶ
ይወስዳል መልሶ እንዳይቀ ተረስቶ
በትላንት ፈረስ በዝክረ ፍካሬ
ይሻገራል ግዜ ነገ ሆኖ ዛሬ፤
ግዜ ራዕይ ነው ያሳየናል በርቶ
ውጥሩ ተንፍሶ እስሩ ተፈትቶ፣
ህያው ነው ህላዌ የዘመን ቀስተኛ
ግዜ ምስጢረኛ የፈጠርነው እኛ፣
መንገዱን አጉልቶ የተጓዝነው ጎዞ
ያሳየናል ግዜ በትዝታ መዝዞ
በጸጥታ ፈረሰ መልሶ መላልሶ
ያሳየናል ግዜ የዚም የዚያ ጉዞ።
ሆረስ ዐይነ ኩሉ
March 22, 32021
አንዲት ህገወጥ ስንኝ ለዛሬው ወያኔ
Last edited by Horus on 23 Mar 2021, 10:29, edited 2 times in total.
Re: አንዲት ህገወጥ ስንኝ ለዛሬው ወያኔ
የትግሬ ነጻ አውጪ ለምን? ምን ላይ ለመድረስ? ግዜ ግን ሁሉን ነገር መልሶ ያሳያል !! እውነትም ውሸትም፣ ትክክልም ስህተትም
Re: አንዲት ህገወጥ ስንኝ ለዛሬው ወያኔ
በሕይወትህ ውስጥ የሠራሃቸውን ስህተቶች ከመሞትህ በፊት ታስታውሳቸዋለህ ! በዚህ የእውቀት ዘመን ድንቁርና ምርጫ ነው !!!
Re: አንዲት ህገወጥ ስንኝ ለዛሬው ወያኔ
የትግሬ ነጻ አውጭ ምን ለማምጣት? ግዜ መስተዋት ነው !!!