Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
temari
Member
Posts: 3904
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

1 of the 4 Ethiopia's Geothermal energy projects

Post by temari » 17 Mar 2021, 07:57


Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: 1 of the 4 Ethiopia's Geothermal energy projects

Post by Ethoash » 18 Mar 2021, 07:04

ሁለት ነገር ስጮህ ነበር ። አንደኛ አሜሪካ አጋር አይሆነንም ብዬ። ወድ ፷ ዓመት የፈጀ ፕሮጀክት ይዘው ሲያንደባልሉት ሲያንደባልሉት ፯፭ ሜጋ ዋት ብቻ ለማምረት ብቅቶዋል ። በዚህ ላይ ቢሊዬኖች ዶላር የፈጀ ፕሮጀክት ነበር ። አሜሪካ ፣ ካናዳ ምንም ፕሮጀክት አይስሩልንም እርማችንን እንቁረጥ ብዬ ነበር ።

ታድያ በአሜሪካኖች ምትክ ቻይናዎች በአጭር ግዜ የኬን ያን የጂሆተርማንን ፕሮጀክት አስጨርሳ እንዳስረከበችም ተናግሬ ነበር ። የቻይናዎች ጥራታቸው ደግሞ ኬን ያኖችን ማስልጠናቸው ነው። አሁን ኢትዬዽያ ውስጥ ኬን ያኖችን ሳይ በጣም ነው ደስ ያለኝ። እንዲህ ነው እንጂ አፍሪካ አንደነት። በነካ እጃቸው ደግሞ የጎማ ተክልን ከላይቤሪያ እንዲህ ማስመጣት ከተቻለ እደገታችን ተፋጠነ ማለት ነው።

ቻይኖች የኬን ያን ፕሮጀክት ሲስሩ ወሃው አንዴ ኤሌትሪክ ካመነጨ በኋላ ወደ መሬት ውስጥ እንደገና ውሃውን በመክተት እንደገና ሙቀት አግኝቶ እንደገና ኤሌትሪክ እንዲያመነኝ ያረገዋል።

የጂዎተርማን ቴክኖለጂ ያለምንም ጥፋት አይደለም ጥቅም የሚስጠው። በዙ ስልፈር ወደ አየር ስለሚበትን በአካባቢ ያሉት ዛፎች በሙሉ ይሞታሉ ሽታውም ደግሞ አያስቀርብህም የበስበስ የበስበስ ሽታ ነው የሚሽት ህ ። ታድያ ቻይናዎች ይህንን ለመቆጣጠር ውሃውን ዝም ብለው አይለቁትም ወድ ምድር እንደገና ስለሚልኩት ችግሩ ተቃሎዋል ። የኢትዬዽያ ፕሮጀክት አሜሪካና አዲት አገር አለች በጂዎተርማል የታወቀች እሱዋም ሆነው በፖሮጀክታችን እየተጫወቱ ነው። ፖሮጀክቱ በሐይሌ ስላሴ ግዜ የተጀመረ ነው። ከእንግሊዝ አንዲት ጥርብ ሴት አምጥተው ፒሄሽ ዲ አጠናለሁ ብላ እንዴት የጂሆተርማል ፕሮጀክታችን በስልፌር አካባቢውን እንደሚጎዳ ታጠናለች መፍትሔውን ሳታስቀምጥ ። ማለት የሚፈልጉት እኮ አካባቢውን ስለሚጎዳ ፕሮጀክቱን ዝጉት ነው።

ሌላ ትንሽ ቅሬታዬ በተራ በተራ ጉድጎድ መቆፈራቸው ነው። ይህም አምስት አመት ይፈጃል በለዋል ። ኢትዬዽያ አስር ሺህ ሜጋ ዋት ካለን በዚህ ሙቀት ብቻ ለምን መቆፈሪያውን አንጀታችንን አስረን ገዝተን ወይ ደግሞ አቅም ላላቸው ስዎች ስጥተን ለምን በፍጥነት አናስቆፍርም አምስት መቆፈሪያ ካመጣን አስሩንም ጉድጎድ በሁለት ወር ስለምንጨርስው በሁለት አመት መቶ አምሳ ሜጋ ዋት ሀይል ይኖረናል ። ይህንን ስንሽጥ ለሶስት አመት የመቆፈሪያውን ዋጋ እንመልስና ብዙ ትርፍ እናገኛለን ። ይህ ቁፋሮ መቆም የለበትም ባይ ነኝ። እየታሽገ መቀመጥ ከቻለ ቁፋሮው ለአንድ ቀን መቋረጥ የለበትም ባይ ነኝ።

ወተትንም ፓስተራይዝድ ማረግ ይቻላል በዚህ ውሃ ሲል በጣም ነው ደስ ያለኝ እንግዲህ ውሃው ከወተቱ ጋራ ስለማይገኛኝ ውሃው ወተቱን ፓስትራይዝድ አርጎ ወድ መሬት ሲመለስ ደጋግመን ደጋግመን በውሃው መጠቀም በነፃ ስንችል ምን ያህል ጠቀሜታ አለው ዋጋውንም ማርከስ እንችላለን። ይህ ማለት ደግሞ የብርቱካን ጫማቂዎች እና የብዙ አታክልቶች ጭማቂዎችን ማሽግ እንችላለን። አንድ ቴክኖለጂ አለ ለዓመት ጭማቂው ወይም ወተት ሳይበላሽ የሚያስቀምጥ ማሽግያ ቴክኖለጂ እሱን ብንጠቀም ደግሞ ያለፍርጅ ጭማቂያችንና ወተታችን ፍሪጅ ሳይስፈልገው ለአመት ካስቀመጥነው አፍሪካ በሙሉ መላክ እንችላለን ማለት ነው። እትፍ እትፍ ቡዳ እንዳይበላው

ሌላው ደስ ያለኝ ደግሞ እንድሶላር ሳይሆን ፪፬ ስዓት ሀይል መስጠቱ ነው ። ሳይቆራረጥ። ከሀይድሮም ይሻላል ዝናብ መጠበቅ የለ። ወይ ግደብ መገንባት የለ በትንሽ ቦታ ላይ ብዙ ሀይል ማምረት ይቻላል። የግድባችን ውሃ ያለው መሬት ውስጥ ነው ያለው ። እያወጡ መጠቀም ብቻ ነው።

Post Reply