የምርጫ 2013 የዕጩ ምዝገባ ሂደት እና በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ
የ #ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ)
በሱማሌ በኦሮሚያና በቤንሻንጉል በምርጫ ክልል ቢሮዎች በአግባቡ ያለመከፈት ችግር እና ከፀጥታ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ያዘጋጀናቸውን እጩዎች በከፊል ማስመዝገብ አልቻልንም። በጋምቤላ አኮቦ እና በአፋር አባላ የሚባሉ ምርጫ ክልሎች ምርጫ ቦርድ ቢሮ እንደከፈተ ሪፓርት ቢያደርግም በክልሉ ያለን መዋቅር አመራር፣ አባላት እንዲሁም እጩዎች የምርጫ ክልል ቢሮዎቹን ሊያገኙዋቸው አልቻሉም። በሲዳማ ክልል በሦስት ምርጫ ክልሎች በመዝጋቢ በተፈጠረ ችግር አባላት ሊመዘገቡ አልቻሉም፤ በኦሮሚያ ክልል በበርካታ የምርጫ ክልሎች ቢሮ ባለመከፈት፤ በፀጥታ ችግር፤ በመዝጋቢ ተባባሪ አለመሆን ምክኒያት በርካታ ዕጩዎቻችንን ማስመዝገብ አልቻልንም፡፡ በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በፀጥታ ችግር ምክኒያት በርካታ ዕጩዎቻችንን ማስመዝገብ አልቻልንም፡፡
ከምርጫ ክልል ቢሮዎች ጋር በተያያዘ የገጠሙንን ችግሮች ካዘጋጀናቸው እጩዎች ስም ዝርዝር እና የምርጫ ክልል ስም ጋር በማያያዝ ለምርጫ ቦርድ የምናሳውቅ ሲሆን በፀጥታ ችግር ምክንያት እጩዎችን ለማስመዝገብ ያልቻልንባቸው ቦታዎች ላይ በአጃቢ እጩዎችን ለማስመዝገብ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
