ይህን ተመልከቱ፤ የብልጽግና ፓርቲ መሰረታዊ ፍልስፍናው ሃብት ነው ወይም እድገት ነው ። ነገር የፓርቲው አርማ ያንድነት (የህብረት) ወይም የመደመር ምስል ነው። አሁን ደሞ ለምርጫ ምልክትነት ያቀረበው አምፖል ነው። ያ ደሞ የሚያመለክተው ብርሃን ነው ። የብርሃን ትርጉም እውቀት እንጂ መደመርም ሆነ ሃብታምነት አይደለም ።
ስለዚህ ፓርቲው መደመር፣ መበልጸግ ፣ እወቀት (ትምህርት) በሚሉ የተለያዩት ትኩረቶች መሃል ችግር አለበት ። ይህም ማለት ሃሳቡን ዲዛይን ያደረጉት ሰዎች ጥልቅ ህተት ነው።
በሌላ በኩል ኢዜማን ተመልከቱ ። የፓርቲው መሰረታዊ ፍልስፍና ፍትህ ነው ። የፓርቲው አርማ ብዕር (እውቀት) እና ሚዛን (ፍትህ) ነው ። ማለትም የብርሃን ሃሳብና ምልክት ያለው ባኢዜማ አርማ ውስጥ ነው ። አሁን ደግሞ የምርጫ ምልክቱ ያው ሚዛን ነው ። ትክክለኛ ዲዛይን ማለት ይህ ነው።
ይህም ሆነ ያ ብርሃኑ ነጋና አቢይ አህመድ ስለ ብርሃንና አምፖል የሚያደርጉት ስልጡን የምርጫ ፖለሚክስ እጅግ ውብ ነው !!!
እርግጥ ብርሃን የሚመነጨው ከአምፖል ነው ወይስ ከኤሌክትሪክ የሚለው ጉዳይ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል