Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42480
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኢትዮጵያ አጀንዳና የ2013 ብሄራዊ ምርጫ

Post by Horus » 16 Feb 2021, 02:03

በሚቀጥለው ምርጫ ከ50 በላይ ፓርቲዎች ለስልጣን ይወዳደራሉ ። አንድ ሰው፣ አንድ ዜጋ ድምጽ ለመስጠት የያንዳንዱ ፓርቲ ጥሩነትና መጥፎነት መለኪያው ምንድን ነው?

የፓርቲዎች መለኪያ ፍቱን ዘዴ የፓርቲዎች ንግግር፣ ፍልስፍና፣ ድርሰት፣ ጣፋጭ ስብከት ወይም ጉልበት ሳይሆን የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው። እያንዳንዱ ዜጋ ይህን የኢትዮጵያ አጀንዳ በኪሱ መያዝ ያለበት ሚዛን ነው ።

የኢትዮጵያ አጀንዳ ምንድን ነው?

አንድ፣ አገርና መንግሥት፤

የኢትዮጵያን አንድነት፣ ሰላምና ጥንካሬ መጠበቅ፣ መፍጠር፣ ማሳደግ የመጀመሪያው ግዙፍ ተግባር ስለሆነ አንድ ፓርቲ በቅድሚያ የሚለካበት ሚዛን ነው። አንድ ፓርቲ በዚህ ግዙፍ ተግባር ላይ አሳማኝ ራዕይ፣ ፕሮግራም፣ ፖሊሲ ፣ መፍትሄ ከሌለው ውድቅ ማድረግ ግዴታ ነው ።

ሁለት፣ ሕብረተሰብ እና ፖለቲካ፤

ኢትዮጵያን ዴሞክራሳዊ፣ ነጻና፣ ፍትሃዊ ማህበረሰብ ማድረግ ሁለተኛው ግዙፍ ተግባር ስለሆነ አንድ ፓርቲ በሁለተኛ ደረጃ የሚለካበት ሚዛን ነው። አንድ ፓርቲ በዚህ ግዙፍ ተግባር (ዴሞክራሲ፣ ፍሪደም፣ ጀስቲስ) ላይ አሳማኝ ራዕይ፣ ፕሮግራም፣ ፖሊሲ ፣ መፍትሄ ከሌለው ውድቅ ማድረግ ግዴታ ነው ።

ሶስት፣ ሕዝብና ብልጽግና፤

ኢትዮጵያዊያንን የበለጸጉ፣ የተማሩ፣ ጤነኛ ሕዝብ ማድረግ ሶስተኛው ግዙፍ ተግባር ስለሆነ ስለሆነ አንድ ፓርቲ በሶስተኛ ደረጃ የሚለካበት ሚዛን ነው። አንድ ፓርቲ በዚህ ግዙፍ ተግባር ላይ አሳማኝ ራዕይ፣ ፕሮግራም፣ ፖሊሲ ፣ መፍትሄ ከሌለው ውድቅ ማድረግ ግዴታ ነው ።

አራት፣ ካልቸርና ኢኮሎጂ፤

የኢትዮጵያን ባህል የሚፈጥር፣ ሚፈልስፍ፣ ኢኮሎጂው ሚዛናዊ የሆነ እምነትና ስነምግባሩ መንፈሳዊ የሆነ ካልቸር ማድረግ አራተኛው ግዙፍ ተግባር ስለሆነ አንድ ፓርቲ በአራተኛ ደረጃ የሚለካበት ሚዛን ነው። አንድ ፓርቲ በዚህ ግዙፍ ተግባር ላይ አሳማኝ ራዕይ፣ ፕሮግራም፣ ፖሊሲ ፣ መፍትሄ ከሌለው ውድቅ ማድረግ ግዴታ ነው ።

በቃ ማንኛውም ዜጋ፣ በማንኛውም የትምህርትና የፖለቲካ ንቃት ደረጃ ያለ ኢትዮጵያዊ ይህችን አጭር አጀንዳ ባንጎሉና በኪሱ ይዞ እያንዳንዱን ፓርቲ እንደ ስንዴ ማበጠር ይችላል ።

ፓርቲዎችን በስሜትና በቃላት ማማር፣ በስብከትና በፕሮፓጋንዳ ብዛት አትመዝኑ ። እያንዳንዳችሁ ይህን የሚመስል ለኢትዮጵያ የምትመኙት አጀንዳ ያዙ ፤ ያ አጀንዳም እንደ ወርቅ መለኪያ ተጠቀሙበት ።

የ2013 ፖለቲካ ውድድር ታውጇል! እጹብ ድንቅ ነው! ትልቅ የህዝብ መማሪያ ድራማ እንደ ሚሆን አልጠራጠርም! በአገራችን እስቲ አሉ የሚባሉት የፖለቲካ ሃስቦች፣ ጽንሰ ሃሳቦች፣ ንድፈ ሃሳቦች፣ መንገድና እቅዶች፣ ቅኔና ዜማዎች የምንሰማበት የፖለቲካ ወቅት ላይ ነን!

በአንድ ዴሞክራሳዊ ሰርዓት የአንድ ዜጋ ድምጽ የስርዓቱ አልፋና ኦሜጋ፣ መቆሚያውና መፍረሻው ነውና በትልቅ ክብርና ጥንቃቄ ያዙት!

Horus
Senior Member+
Posts: 42480
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የ2013 ብሄራዊ ምርጫ

Post by Horus » 16 Feb 2021, 13:38

ዴሞክራሲና ነጻነት ያለ መስዋዕትነት አይመጣም !

Horus
Senior Member+
Posts: 42480
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የ2013 ብሄራዊ ምርጫ

Post by Horus » 17 Feb 2021, 03:49

በሚቀጥለው ምርጫ አቢይ ማጆሪቲ መያዝ መፈልግ ሳይሆን ማጆሪቲ ካልሆነው እንደ መለስ ዘመን ይሆናል !

ኢዜማ ጠካራ ማይኖሪቲ ፓርቲ ይሆናል እስከ 2018 ድረስ ማለት ነው ።

እኔ አቢይ ብሆን የሆነ ጎሳ ጋር ከመፎካከር ከኢዜማ ጋር መፎካከን እመርጣለሁ !!

ስለዚህ የዜጋ ፖለቲካ ብዙ ወንበር እንዲያገኝ ኢትዮጵያን የምትወዱ ከኢዜማ ጋር ተባበሩ

Post Reply