Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42474
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጥንታዊውና ቱባው የክስታኔ ገና ባህል በአማውቴ (ሰሜን ጉራጌ)

Post by Horus » 13 Feb 2021, 03:12

እዚህ የምታዩት የገና ሜዳ እኔ ሳድግበት ክረምት ክረምት ረግረግ ይሆን ነበር ። ከመስከረም በኋላ ከብት እናግድበት ነበር። አክራሚ ወይም ቅዱስ ዮሃንስ መጠመቂያ ነበር። ሞጆ አራጆ የዝላይ ጨዋታ ፣ ፈርስ መጋለቢያችን፣ ገና መጫወቻችን፣ ጥምቀት ማክበርያችን ነበር። ሜዳው ዎተደር፣ እንጀሪ፣ እንዶዴ ፣ ጎቤኒ በሚባሉ ቀበሌዎች ይከበብ ነበር። ተራራው ላይ ያለው አማውቴ ባልወልድ ነው ። በሰሜን በኩል ገገራ ሚካኤል እና ማሪያም አለች፤ በምስራቅ እንዶዴ ገርጊስ አለ ። በእንጀሪ ወደ ደቡብ ተራራው ስር ጢያ ማሪያም አለች ። ከዚያም የጢያ ሃውልቶች አሉ።