By Tesfaye Gebreab
ወያኔ ተወግዶአል። ማለትም ዳግም ተደራጅቶ ድርጅት ሊሆን አይችልም። በፕላኔታችን የብርጭቆ ታሪክ ውስጥ ወድቆ የደቀቀ ብርጭቆ ስብርባሪው ተለቅሞ፣ ተጠግኖ አገልግሎት ሲሰጥ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። የደቀቀ ብርጭቆ የ50 ቀን እድል ወደ ቆሻሻ በርሜል መወርወር ነው። (የ40 ቀን ያላልኩት የሁሉም ነገር ዋጋ ስለጨመረ ነው።) በዘመናዊው የቆሻሻ እቃ ደንብ የደቀቀው ብርጭቆ ተፈጭቶ ሌላ ብርጭቆ ቢሰራበት እንኩዋ "የቀድሞው ብርጭቆ" ሊሆን አይችልም።
አብይ አህመድ በ18 ቀናት የትግራይ ጦርነት ያገኘው ድል ሊከሽፍ ግን ይችላል። መክሸፉ ወያኔን እስከ መመለስ ባይደርስም የመከፋፈል አደጋ የማስከተል እድል ይኖረዋል።
የOLF አባል የሆነ አንድ ወዳጄ ባንድ ወቅት፣
እንዳለኝ ትዝ ይለኛል። ይች አባባል ዛሬ "ግማሽ ስላቅ - ግማሽ እውነት" ሆናለች።ወያኔን ከቀበርን በሁዋላ ከነፍጠኛ ጋር አንድ ጦርነት አይቀርልንም
የኦሮሞ ታጋዮች ህይወት ከፍለው ያመጡት ለውጥ ላይ ቆመው በጥቃቅን ጉዳዮች ምክንያት ተከፋፍለው ሲሻኮቱ ማየት ያሳቅቃል። አብይ አህመድ ጥርሱን ነክሶ በተሰባበረ ምላጭ ላይ በባዶ እግሩ ሲራመድ ማየትም ሌላው "ሰቆቃወ ኢትዮጵያ" ነው።
ርግጥ ነው፣ ንጉስ ጎበና ዳጪ እና አጤ ምኒልክ የመሰረቱዋት ኢትዮጵያ እንደዚህ ዘመን ጠላት በዝቶባት አያውቅም። ግን ደግሞ አልፈረሰችም። እየተንገዳገደች ታዘግማለች። እንደ COVID-19 ሲፈለፈሉ የሚያድሩ ጥያቄዎች ሲደበድቡዋት ውለው ሲያደባዩዋት ያድራሉ። ኢትዮጵያ "የሚናገር በዝቶ - የሚያዳምጥ ጠፍቶ" ሆናለች። በግልጽ እውነቱን የሚነግራትን እንደ ግመል ቂም ቁዋጥራ ትነክሳለች። የሃሰት የሙገሳ ቅባት የሚቀባትን እንደ ታቦት ትሸከመዋለች። ይህን ባህል ለመለወጥ ጊዜ እና ፋታ አጥታ ታየች።
ኤርትራ እና ሶማሊያ "የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች" የሚል ቅጽል ስም የያዙት በኔው ዘመን ነበር። ይህ አባባል ተገላቢጦሽ የሆነውም በኔው ዘመን ነው። በኔው ዘመን ነገ ምን እሰማ ይሆን?
የደቀቀው ብርጭቆ ተመልሶ ባይጠገንም፣ የብርጭቆው መድቀቅ ለኢትዮጵያ መጪ ዘመን የብሩህ ተስፋ ዋስትና ሊሆን እንደሚችል አንዳችም ማረጋገጫ የለም። አምላክ እንዲህ ባለው ጉዳይ ላይ እጁን ቢያስገባ ኖሮ በ'ውነቱ ጸሎት ያዋጣ ነበር!!
___________________
Ethiopians flooding all over Ethiopia, in support of PM Abiy Ahmed. Watch Benishangul-Gumuz in Asosa town from 0:00 to 33:30 and from 33:30, Kafa people in Bonga town in southern Ethiopia.
TPLF's Heydays: Dance unto Death!