-
Abe Abraham
- Senior Member
- Posts: 14414
- Joined: 05 Jun 2013, 13:00
Re: Horus ....በኣዲስ ብቻ ሳይሆን በካሩቱምም ጭምር ...ሱግ ኣል-ኣፍረንጂ on fire !
አቤ
አረብኛ የምታውቅ ይመስለኛል፤ ሱቅ አል አፍረንጂን ያቃጠሉት እነማን ናቸው ነው የሚለው ፖሊሱ? አይሲስ በኢትዮጵያም በሱዳምን ቢከሰት አልደነቅም። በመደምሰሳቸው የተበሳጩ ዎያኔዎች ጀለቢያ ለብሰው ቴረሪዝም ቢጀምሩ ማንም አይደነቅም ።
ይህኮ ነው ያፍሪካ ቀንድን እናሸብራለን፤ ግጭቱን ረጅናል ማድረግ ማለት?
ባንተ ግምት የሱዳኑ እሳት ሞቲቨ ምን ይመስልሃል?
የሱዳን ዲስታብላይዜሽን የሚፈልጉ ሃሎች እነማን ናቸው?

The last man in the video says that it is an electrical accident and that he had tried several times to get help from the electricity authorities ( he recorded the message he sent to them on his mobile and reported the contents to the police after the accident ) but no one came to do the preventive repair work. In Sudan there are lots of people who have been to technical schools and universities but they lack problem solving abilities. The capital city Khartoum for instance is like a big village which keeps growing faster than the services provided by the government .
ሱዳን ብዙ ችግርና ግፍ ያለበት ኣገር ቢሆንም በከተማ ውስጥ " ሳቦታጅ " ( ማቃጠል ፡ ንብረት ማውደም ) የማድረግ ልምድና ታሪክ የለውም ። ኣሳሲነሽን የሚባል ነገርም ባገሪቱ ተሰምቶ ኣያውቅም ። በጥይት መትቶ መግደል ማለቴ ነው ። በየተበላሸች ኣውሮፕላን ኣንተና ጓደኛችህን ልከው እንደምትሞት ያደርጋሉ ። ኣል-በሺር ያገባት ሁለተኛ ሴት በዚ መልክ ነው ባልዋን የገደለው ። ሌላ በእስር-ቤት ውስጥ ኣሰቃይቶ መግደልና ሶዶማዊ ሰቆቃ መፈጸም ባገሪቱ ብዙ የሚታይ ነገር ነው ። በኣል-በሺር ግዜ በሰቆቃ የሚታወቅ ብዙ ሰዎች ያጠፋ የጸጥታ ሃላፊ ሳላሕ ጎሽ ይባላል ። እስካሁን ድረስ ባደረገው ወንጀል የጠየቀው ሰው የለም ። ስለ'ዚ ምእራባውያንና ኣረቦች ካፈቀዱለት ኦፊሽያሊ የሱ ሰዎች ወደ ስልጣን እንደሚመለሱ ለማድረግ ይችላል ።
ሳቦታጅ ካለ ኣገሪትዋን በሙሉ የሚያዳክም የኤኮኖሚና ( ዶላር ከሱቅ ጠርጎ መውሰድ ) የጸጥታ ሳቦታጅ ነው ። ለዚህ ስራ የተደራጁ ሰዎች በኣገሪቱ ሙሉ የሚገኙ ሆነው በተለያዩ መዋቅሮች - ባንኪን ፥ ፖሊስ፡ ሲክረት ሰርቪስ፡ ትምህርት፡ ኣርሚ ... - ተሰማርተው የሚገኙ ናቸው ። እነዚህ ሰዎች የኣል-በሺርና የሓሰን ኣል-ቱራቢ (ሞተዋል) ተከታዮች ናቸው ። ቁጥራቸው በጣም ብዙ ስለሆነና ብዙ ሱዳናውያንን በሃይማኖት ስለ መረዙና ስላሳበዱ ሊያደርሱት የሚችሉ ኣደጋ ቀጣይ ይሆናል ። ስለ'ዚ ነው ደሞ " ኣልደውላ ኣል-ዓሚቓ " / ዲፕ ስተይት ብለው የሚጠርዋቸው ። መንግስት በከፊል ወይም በሙሉ ቢቀየር እነሱ ሁል ግዜ ቁጭ ብለው የብልሽት ስራቸው እያደረጉ ይኖራሉ ። የኒገር ኣስተሳሰብ ስላላቸው ኣገሪትዋ ኋላ ቀር በትሆን ምንም ኣይሰማቸውም ።
ኣሁን በየሱዳን መንግስት ያለ ሲቪላዊ ክንፍ " ዲፕ ስተይቱን " ለማፈራረስና በሃይማኖት የተመረዘ ህብረተ-ሰቡን ለመቀየር ሙከራ እያደረገ ነው ። ስራው ግን ቀላል ኣይደለም ። ባለኣግባብ ሃብት ያክማቹ ሰዎች እየተመረመሩ ናቸው ግን ፍጥነት የለም ። በየትምህርት ካሪክለሙ ኣልገራይ የተባለ ሰው ቼርማን ሆኖ ብዙ ለውጥ - ከኣንደኛ ክፍል ጀምሮ- እያመጣ ነበር ሆኖ ግን " ከሃይማኖታችን ጋር የሚጻረር ነገር እያደረገ ነው ተብሎ ስራውን ሊቀጥል ኣልቻለም ። ከሃይማኖታችን በስተቀር ሃይማኖት የሚባል ነገር የለም ። ልጆቻችን ከህጻንነታቸው ጀምሮ ብረይንዎሽ ለማድረግ እየፈለገ ነው ። '" የሚል ክስ ስለገጠመው ከስልጣኑ ሊወርድ ተገደደ ።
ኣልገራይ ለየት ያለ የሃይማኖት ኣስተያየት ያለው የሪፓብሊካን ብራዘርሁድ ኣባል ነው ። የሪፓብሊካን ብራዘርሁድ መስራች ማሕሙድ መሓመድ ጣሃ ከሃይማኖት ወጥተሃል ተብሎ በጃዕፈር ኑመይሪ በሞት የተቀጣ ነው ። ስለዚ ነው የሱዳን ኢስላሚስቶች ኣልገራይን ከብዙ ሙከራ ቡሃላ ስራውን ለቆ እንዲሄድ ያደረጉት ።
ኣልገራይ ኣንድ ግዜ " ኣላህ ቁርኣንን በኣረብኛ ቋንቋ ላከው ልንል ኣንችልም ...መንግስተ-ሰማይ ልትገባ ሙስሊም ልትሆን ኣስፈላጊ ኣይደለም ...ኣምላክ በህሊናህን ነው የሚፈርድህ .. according to your conscience. " ብሎ ሲናገር ብዙ ሱዳናውያኖችን ኣናደደ ። በሱ መሪነት የካሪክለም ኤክስፐርቶች የ " religious tolerance " ( በኣለም ከእስላም በስተቀር ሌሎች ሃይማኖቶች እንዳሉ የሚያሳይ ) ይዞታ ያለው የኣንደኛ ደረጃ ትምህርት-ቤት መጽሓፍ ካዘጋጁ ቡሃላ በኢስላሚስቶች በተደረገ ጫና ስራው ቆሞ ኢንቨስቲጌሽን ተጠራ ። ከዛ ቡሃል ኣል-ገራይ ስራውን ለቆ ሄደ ። ይህ የጠቀስኩት የሱዳን የለውጥ ጉዞ ብዙ ችግሮች እያጋጠመው እንዳለ ለማብራራት ነው ። ጉዳዩ ለሱዳኖች ብቻ ሳይሆን ለኛም የሚመለከት ስለሆነ ።
.
Re: Horus ....በኣዲስ ብቻ ሳይሆን በካሩቱምም ጭምር ...ሱግ ኣል-ኣፍረንጂ on fire !
አቤ አብርሃም፤
በጣም አመሰግናለሁ ! ግሩም ትንተና ነው፣ የሱዳን እውቀትህ ጥልቅ ነው ። አል ቱራቢን ደርሼበታለሁ ። እኔ ያለኝ ሃሳብ ከላይ የጻፍከውን የሱዳን ጉዳይ እንዴት ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደ ሚነካ ጨምረህበት እንደ ኢሳት እና አባይ ሚዲያ ብትልክላቸው የዜናቸው ባክግራዉንድ ያደጉታል ።
በዚንህ ዘመን እውቀት ከቦታ ቦታ የሚጓዘው በከፍተኛ ፍጥነት ነው ። ማንኛውም ጠቃሚ እውቀት አሁን በቀላሉ ማግኘት ሲቻል እውቀትም የሚያድገውና የሚጠቅመው በሰፊው ሲሰራጭ ነው።
ለምሳሌ ተመስገን ደሳለኝ እንደዚህ ያለ መረጀዎች (ፋክትስ ) ቢያገኝ ደስታውን አይችለውም ።
ሱዳን ከፍራጃይል ሲስተም ወደ ፌይድ እስቴት እየሄደች ነው ?? ኬር !