Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42464
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አንድ ስንኝ ለፍጻሜ ዘዎያኔ

Post by Horus » 30 Jan 2021, 02:12

የግማሽ ምዕተ አመት ቅብጠት
ግፍ ቅሚያ ወንጀል ትዕቢት
ግራት ጥጋብ ውጥረት ዕብሪት
ጉልበት ንቀት ዉሸት ክህደት
በሰካራም ድንፊያ በድቁርና ኩራት፤
ለምን ብሎ መጫር ክብሪት
ለመጋ'የት በራስ እሳት
አልቦ አንጎል ባዶ ስድስት
የድሮን ምሳ የጅብ እራት
ለመፈ'ጸም ለማሸለብ በደደቢት፤
በተከዜ ምድረ በዳ ጭርታ
በነደደው ሃሩር ፍላታ
ከማይናገሩት ቋጥኝ ተርታ
በተምቤን በረሃ ጸጥታ።

ሆረስ አይነ ብርሃን
January 29, 2021

Horus
Senior Member+
Posts: 42464
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ ስንኝ ለፍጻሜ ዘዎያኔ

Post by Horus » 31 Jan 2021, 13:41

ክፍት አፉ ልደቱ
አንጎለ ቡቱቱ
ያልተባለ አንቱ
ቅሌታም ለፈደድ
ያርጀ በከንቱ!

Post Reply