Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11588
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በዓመት ውስጥ ብር ከዩሮ € 34% ከፓውንድ £ ደግሞ 28.6% ተዳክሟል

Post by sarcasm » 20 Jan 2021, 18:28

የብር የምንዛሪ ዋጋ መዳከሙ የዋጋ ግሽበት ያስከትላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ተናገሩ
Ethiopian Reporter

20 January 2021
ሳምሶን ብርሃኔ

በዓመት ውስጥ ብር ከዩሮ €34% ከፓውንድ £ ደግሞ 28.6% ተዳክሟል




መንግሥት ከዶላርና መሰል የውጭ ምንዛሪ መገበያያዎች አንፃር የብር ምንዛሪ ዋጋን እንዲዳከም ማድረጉ፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስከትላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ተናገሩ።

በተለይ በስፋት በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ምርቶች ከውጭ የሚገቡ በመሆናቸው የብር ዋጋ ከውጭ ምንዛሪዎች አኳያ መዳከሙ የዋጋ ጭማሪ ያስከተለ ሲሆን፣ ይህ የሚቀጥል ከሆነ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሊያመጣ እንደሚችል ባለሙያዎች ከወዲሁ እያስጠነቀቁ ነው።

በአንድ ዓመት ውስጥ እስከ ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ብር ከዶላር አኳያ በ24 በመቶ፣ ከዩሮ አኳያ 34 በመቶ፣ እንዲሁም ከፓውንድ አኳያ ደግሞ 28.6 በመቶ ተዳክሞ የመሸጫና የመግዣ ዋጋው ወርዷል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት መንግሥት ፍላጎትና አቅርቦትን መሠረት ያደረገ ተለዋዋጭ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት መተግበሩን ተከትሎ፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የኑሮ ውድነት ሊያባብስ እንደሚችል ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፖሊሲ አውጪዎችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በበኩላቸው ዕርምጃው፣ ‹‹ያለ ቅጥ የጨመረውን የብር ዋጋ›› በመቀነስ የወጪ ንግድ ገቢ ለማሳደግ ያለመ ነው ሲሉ ቆይተዋል።

በሌላ በኩል የብር ዋጋ መዳከሙ የፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃ መግዣ ዋጋ እንዲጨምር በማድረጉ፣ አገር ውስጥ እየተመረቱ ያሉ ምርቶች እንዲወደዱ ምክንያት ሆኗል። ጭማሪው እንደ ዘይት ባሉ ከውጭ ሙሉ ለሙሉ የሚገቡ ምርቶች ላይ የባሰ ሲሆን፣ ይህም የኑሮ ውድነት እያስከተለ መሆኑን ማውቅ ተችሏል።

ብርን ማዳከም ለምን አስፈለገ?

በ2003 ዓ.ም. አንድ ዶላር ከባንኮች ለመግዛት 17 ብር ብቻ በቂ ነበር። ከአሥር ዓመታት በኋላ ግን የብር ዋጋ በ130 በመቶ በመዳከሙ አንድ ዶላር ለመግዛት ከ40 ብር በላይ ያስፈልጋል። በእነዚህ ወቅቶች የብር ዋጋ በመንግሥት ከአምስት ጊዜ በላይ እንዲዳከም ተድርጓል። ታዲያ ይህንን ዓይነት ዕርምጃዎች የተወሰዱት፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ያላትን ተፎካካሪነት ለመጨመር ቢሆንም ውጤቱ አስደሳች አልነበረም።

በሥልጣን ላይ እያሉ ሕይወታቸው ካለፈው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አሁን ሥልጣን ላይ እስካሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ድረስ፣ የብርን ዋጋ ማዳከም ወጪ ንግድን ለመጨመር መፍትሔ ተደርጎ ቢወሰድም የተገኘው ውጤት እንደተጠበቀው አልነበረም። ባለፉት አሥር ዓመታት ዓመታዊ የወጪ ንግድ ገቢ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ፈቅ ያላለ ሲሆን፣ ከውጭ የሚገባው ምርት በአማካይ 15 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል። ከአራት ዓመታት በፊት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ብር በ15 በመቶ እንዲዳከም ሲደረግ ይስተካከል ተብሎ ቢሆንም፣ በወጪ ንግድ ገቢ ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ ሳይታይ የዋጋ ግሽበትን አባብሶት አልፏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስተዳደር ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ብር የሚዳከምበትን መጠን ይቀንሳል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፣ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓቱ ተለዋዋጭ እንዲሆን በመደረጉ ይበልጥ ሊጨምር ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልክ እንደ ቀዳሚ የኢትዮጵያ መሪዎች ይህ የወጭ ንግድ ገቢ ይጨምራል ብለው ቢያቅዱም ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ንቅንቅ አላለም።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ወሰንሰገድ አሰፋ መንግሥት ይህን ዓይነት ዕርምጃ የሚወስደው ብር ሲዳከም በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ምርት ይረክስና ከውጭ የሚገባ ምርት ዋጋ ይጨምራል ይላሉ፡፡ ይህም የወጪ ንግድ ገቢን ያሳድጋል በሚል ዕሳቤ ቢሆንም፣ ነገር ግን የአገሪቱን አቅም ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ሲሉ ይሞግታሉ። ‹‹በተለይ ኢትዮጵያ ከውጭ ከምታስገባቸው ምርቶች ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የሚይዙት በአገር ውስጥ መመረት ስለማይችሉ፣ ብር ከዶላርና ከሌሎች የውጭ ምንዛሪዎች አንፃር ሲዳከም የዋጋ ግሽበት ማስከተሉ አይቀሬ ነው፤›› ይላሉ።

በእርግጥ ያለፈው በጀት ዓመት የብሔራዊ ባንክ መረጃ ሲታይ ወደ አገር ውስጥ ከገቡ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች ውስጥ 15 በመቶ የሚሆነው ነዳጅ ሲሆን፣ ወደ 30 በመቶ የሚሆኑት አገር ውስጥ በስፋት በሕዝቡ ፍላጎት መጠን የማይመረቱት እንደ ዘይትና ስንዴ ያሉ የፍጆታ ምርቶች ናቸው። በተመሳሳይ ለፋብሪካዎች የሚውሉ ማሽነሪዎችን ጨምሮ የካፒታል ዕቃዎች ወደ 29 በመቶ ድርሻ ያላቸው ሲሆን፣ ወደ 22.4 በመቶ ድርሻ ያላቸው ደግሞ በከፊል ያለቁ ምርቶች ናቸው።

እነዚህ ምርቶች በአገር ውስጥ ሳይመረቱ ብርን ማዳከም የሚጠቅሙ ምርታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ለሚልኩ አገሮች እንደሆነ የሚያወሱት አቶ ወሰንሰገድ፣ ‹‹ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች በእነዚህ አገሮች በጥሬ ዕቃነት የሚውሉ በመሆናቸው ዕሴት በመጨመር መልሰው ወደ ኢትዮጵያ በመላክ የበለጠ ትርፋማ እንደሚሆኑና ኢትዮጵያ ደግሞ ኪሳራ ላይ እየወደቀች እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ብር ሲዳከም የኢትዮጵያ ምርት ይረክርስላቸዋል፣ የሚልኩት ምርት ዋጋ ደግሞ ይጨምርላቸዋል፤›› የሚሉት ባለሙያው፣ ‹‹ከዚህም ማን አተራፊ፣ ማን እየከሰረ እንደሆነ መረዳት ቀላል ነው፤›› ሲሉ አስተያየታቸውን አጋርተዋል።

በዚህ ሐሳብ የሚስማሙት የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ብር በመዳከሙ ምክንያት አምራቾች እየተጎዱ መሆኑን ይገልጻሉ። ‹‹አምራቾች ጥሬ ዕቃዎችን በብዛት ከውጪ የሚያስገቡ ስለሆነ፣ ዓለም አቀፍ መገበያያዎች ከብር አንፃር ዋጋቸው መጨመሩ የምርት ወጪያቸው እንዲያድግ ምክንያት ሆኗል፤›› ይላሉ፡፡ ችግሩ በዚህ አያበቃም። በተለይ ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚያመርቱ አምራቾች የምርት ወጪ ሲጨምር የሚሸጡት ዕቃ ላይ ዋጋ እንዲጨምሩ እንደተገደዱ ይነገራል። ይህም የዋጋ ግሽበት እንዳባበሰ ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል ለብር መዳከም እንደ ምክንያት የሚነሳው ባለፉት አሥር ዓመታት ከፍተኛ መጠን ያለው ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲገባ መደረጉ ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዓለማየሁ ገዳ (ፕሮፌሰር) እንደሚሉት፣ መንግሥት የበጀት ጉድለትን ለመሙላት ገንዘብ ማተምን እንደ አማራጭ ለዓመታት በመውሰዱ ምክንያት፣ የብር የመግዛት አቅም እንደተሸረሸረና ከሌሎች ገንዘብ አንፃር ያለው ዋጋ እንዲዳከም ምክንያት ሆኗል። ይህ መንግሥት መር ከሆነው የብር ዋጋ ቅነሳ ጋር ተዳምሮ የበለጠ የዋጋ ግሽበት ሊያመጣ እንደሚችል ሊታወቅ ይገባል ብለዋል፡፡

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው ብር የተዳከመበት መጠን ከፍ ባለባቸው ዓመታት የዋጋ ግሽበት ከፍ ሊል ችሏል። ለምሳሌ በ2012 ዓ.ም. ዓመታዊ የብር ምንዛሪ መቀነስ (Depreciation) ከ20 በመቶ በላይ በነበረበት ወቅት ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት ከ12.6 በመቶ ወደ 19.9 በመቶ ከፍ ብሏል። የምግብ ዋጋ ግሽበት የበለጠ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ ከ13.1 በመቶ ወደ 23.1 በመቶ ጨምሯል።

የመፍትሔ ሐሳብ

መዋቅራዊና የአቅርቦት ችግሮች ሳይፈቱ ብርን ማዳከም አይበጅም የሚሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ፣ እስካሁን በተገኘው ውጤት የወጪ ንግድ ገቢን መጨመርና የገቢ ንግድ ወጪን መቀነስ የሚቻለው እነዚህ ተግዳሮቶችን በመፍታት እንደሆነ ገልጸዋል። የሎጂስቲክስ፣ የኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ እጥረት፣ ቢሮክራሲና ሌሎች መዋቅራዊ ችግሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ዋሲሁን፣ ብርን የበለጠ ማዳከም ለኢትዮጵያ ዓይነት ኢኮኖሚ የማይበጅ ነው ይላሉ።

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በየወቅቱ በሚያወጣቸው ሪፖርቶች፣ ‹‹የብር ዋጋ ከሌሎች ዓለም አቀፍ መገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለ ቅጥ ከፍ ያለ ነው፤›› በማለት፣ መንግሥት በየጊዜው ተለዋዋጭ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ሊተገብር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ይሞግታል።

በዚህም ሳያበቃ ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ባወጣው ሪፖርት ሥርዓቱ ከመንግሥት መር ወደ ገበያ መር ሊቀየር እንደሚገባ በማውሳት፣ ኢትዮጵያ ፍላጎትና አቅርቦትን መሠረት ያደረገ ተንሳፋፊ የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት ካልተገበረች፣ በ2020 በፈንዱ የፀደቀላትን የሦስት ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ፓኬጅ እንደማታገኝ ግልጽ አድርጓል። መንግሥት በበኩሉ ከሁለት ዓመታት በኋላ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ እንዳቀደ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ አቅርቦት መር የሆነ የምጣኔ ሀብት ሥርዓት ለመከተል ማሰቡን አስታውቋል፡፡

ይህንን የተረዱት አቶ ወሰንሰገድ፣ ‹‹አይኤምኤፍ ብድር ለመስጠት የመዋቅራዊ ለውጥ ፕሮግራሞችን መተግበር እንደ ቅደመ ሁኔታ ማስቀመጡ ለማን እንደሚቆም ማሳያ ነው፤›› በማለት፣ መንግሥት ውሳኔውን በድጋሚ ሊያጤነው እንደሚገባ ይናገራሉ። በተለይ የአይኤምኤፍ የገንዘብ ምንጮች ትልልቅ የውጭ ድርጅቶችና ሀብታም አገሮች በመሆናቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች በፕሮግራሙ በሚያስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ እንደማይጨነቅላቸው ማሳያ ነው በማለት ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።


ይሁን እንጂ የምጣኔ ሀብት ፕሮፌሰሩ ዓለማየሁ ገዳ መንግሥት በአገር ውስጥ መመረት የሚችሉ ምርቶችን በመለየት፣ ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን የመተካትና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ላይ እሴት የመጨመር ሥራዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባው ጠቁመዋል። ተንሳፋፊ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ለኢትዮጵያ እንደማይበጅ የገለጹት ፕሮፌሰሩ፣ የገንዘብ ፖሊሲ ወጪ ንግድን ለማሳደግ መዋል እንደሌለበት ተናግረዋል።

ኢኮኖሚስቱ አቶ ዋሲሁን በበኩላቸው፣ ‹‹ኢትዮጵያ ተንሳፋፊ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ልትከተል የሚገባት የውጭ ምንዛሪ ክምችቷን ካሳደግችና ሌሎች ለወጪ ንግድ አለማደግ ምክንያት የሆኑ ማነቆዎችን (ማለትም መዋቅራዊ ችግሮችና የአቅርቦት ክፍተቶችን) ከፈታች ነው፤›› ብለው፣ ብርን በከፍተኛ መጠን ማዳከም ለጊዜው በረድ ሊደረግ እንደሚገባ ምክራቸውን ለግሰዋል።

https://www.ethiopianreporter.com/article/21053

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: በዓመት ውስጥ ብር ከዩሮ € 34% ከፓውንድ £ ደግሞ 28.6% ተዳክሟል

Post by Ethoash » 21 Jan 2021, 07:45

dear sarcasm

This is Ethoash, the economist expert answering your dilemma ....

አንዳንድ የምጣኔ ሀብት ምሁር የምትላቸው ነገሩ ለራሳቸው ስለማይገባቸው ። ትልቅልቅ ቃላትን በመጠቀም ሊያወናብዱህ ይፈልጋሉ እኔ ግን በቀላል አማርኛ ኢኮኖሚ እንዴት እንደሚስራ አሳይሀለው ። በጣም ሳቀልብህ ደግሞ ቀላል እንዳይመስልህ ። የኢክኖሚ ረቂቅ በዓለም ላይ ወደር የለሌኝ ኢኮኖሚስት ስለሆንኩ ነው። ሳልማር እንደው ከጌታ ከፈጣሪያችን የተስጠኝ ትልቅ ስጦታ ስለሆነ በደንብ አድምጠኝ አልደግመውም። ብዙ ግዜ ይህንን መልስ ደጋግሜዋለሁ ስልችቶኛል ለምክሬ ስለማላስከፍል ሁሉም ቀላል ይመስለዋል።

አንድ ግዜ ወያኔዎች ለምን የኢትዬዽያ ቡና ደረጃው ወረድ ብለው ጠይቁና ኤክስፕርት ከብራዚል አመጡ ። ታድያ ያ ኤክስፕርት አንድ ሚሊዬን ዶላር ለኤክስፕርት ምክር ጠየቀ ። እሺ ተባባሉ ኤክስፕርት መጣ ሁሉ ነገር አየና ። እናንተ ምንም ችግር የለባችሁም ቡናውን ስታስጡ ብቻ ከመሬት ከፍ አርጉት ጠረፔዛ ነገር ስርታችሁ በጠረፔዛው ላይ አድርቁት ብሎ አንድ ሚሊዬን ዶላሩን ውስዶ ሄደ ። ዛሬ ኢትዬዽያ የቡና ገበሬ በመሬት ላይ የሚያስጣ የለም አንድ ሚሊዬን ዶላሩ ቆጭቶት ይሆናል።

አሁን ወድ ጥያቄ ስመለስ ኢትዬዽያ ፫ ቢሊዬን ዶላር አግኝታ ፩፭ ቢሊዬን ዶላር ገቢ ታረጋለች ነው ያልከው ። ታድያ ይህንን ለማተካከል በጣም ቀላል ነው።

መጀመሪያ አንተ ከስራ ስትባረር የምታረገው ምንድነው ውጪህን መቀነስ ነው። ለምሳሌ ውጭ የምትበላ ክሆነ እሱን ታቆማለህ ። ፀጉርህን ወጭ የምታስተካክል ከሆነ ቤት ህ ውስጥ ፀጉርህን ማስተካከል ተጀምራለህ ። በአጠቃላይ ውጭህና ገቢህን በስንጠረዥ ላይ ፀፈህ የቱን ብትቀንስ ምንም በሒወት ህ ላይ ለወጥ የማያመጣውን እያየህ ት ዘርዝና በጣም ጠቃሚ የምትላቸውን ታስቀራለህ ። ለምሳሌ ኬብል ካለህ ኬብልህን ታስቆርጣለህ ፣ ስልክህንም ቢዚክ ታረገዋለህ ። አይተሀል እንዴት ቀላል እንደሆነ። በአጭሩ የወገብህን መቀነት ታጠብቅና ይህንን ክፉ ግዜ ታሳልፋለህ።

ይህ ከገባህ ወድ ትልቁ ኢኮኖሚ እንሂድ። ለምሳሌ ኢትዬዽያ በዓመት ፫መቶ ሚሊዬን ዶላር ቤንዚን ታስገባለች። ይህ ሊቀር ይችላል ያሉትና የሚገቡትን መኪናዎች በፍጥነት ወድ ኤሌትሪክ መኪና ከቀየርን ። አሁን እንዲህ ስል ጠማማ ልብ ያላቸው እንኳን ለመኪና ለኛም ኤሌትሪክ የለንም ብለው ችግር ይጠራሉ ። እነዚህን ስዎች መልስ መመልስ አያስፈልግም ዳምጠሀቸው ማለፍ ብቻ ነው። ቤንዚህ የማናስገባ ከሆነና ፫መቶ ቢሊዬን ዶላር የምናተርፍ ከሆነ እኮ የኤሌትሪክ ማስተላለፊ ገመዶችን ቀይረን ዘመናዊ እናረገዋለን ። ለምን ብትል ብዙ መኪናዎች ኤሌትሪክ ሲቀዱ (ህ ህ ህ ህ) ብዙ ገንዘብ ሐይድሮ ስለሚያገኝ ገንዘቡን መልሶ ኢንቨስት አርግ የኤሌትሪክ ሽግሩን ይቀርፋል።

ሁለተኛ የምንልካቸውን የግብርና ወጤቶች ማየት አለብን ። እንዴት ተደርጎ ነው ብርቱካን በጥሬው ለሳውዲ ልከን ። ከስውዲ ደግሞ የብርቱካን ጭማቂ ለዛውም ኤክስፓየር የሆነ የምናመጣው። ለምንድነው ስሊጣችንን በጥሬው ሽጠን በምን ሂሳብ ነው የስሊጥ ዘይት የምናስመጣው። እንዳልኩት ጠማማ ልቦች የስሊጥ ዘይት ፋብሪካ ፫መቶ ሚሊዬን ዶላር ያስፈልጋል እኛ ደግሞ ይህ የለንም ብድር በዝቶብናል ብለው የለፈልፋሉ ከእድገታችን ሊያቆሙን ። ታድያ እራሳቸው ናቸው በጥቁር ገበያ ገንዘብ ቀይረው የሶስት መቶ ሚሊዬን ዶላር ዘይት የሚያስገቡት ለዛውም ያልተመረመረ።

እንዲህ እያረግን ሁሉንም የምናስመጣውን እቃና ፍጆታ እቃ አገር ውስጥ ማስራት እንችላለን ብለን መጠየቅ አለብን ። አዲስ ለሚጀምሩ ደግሞ የአያ ዓመት የታክስ ከለላ፣ የነፃ መሬት መስጠት አለብት ለምን ብትል ኪሳራውን ሳይፈሩ ስለገቡበት ።

እንደሚታውቀው ኢትዬዽያ ውስጥ አንተ የመጀመሪያውን ኪሳራ እንድትውስድ ዳር ላይ ሆነው ይጠብቁሀል ። ካዋጣህ ዘለው ገብተው ትርፍህን ይጋሩብሀል። ለዚህ መዳኒቱ እንዳልኩት የመጀመሪያ ኪሳራ ሳይፈሩ ለገቡት የማርያም መንገድ ት ስጣቸውና ። ሌላው ሁለተኛ ዙር ኢንቨስተር ታክስ እና የመሬት እንዲከፍል ታረገዋለህ ስለዚህ የመጀመሪያው ኢንቨስተር ሁሌ ተጥቃሚ ስለሚሆን ኪሳራ መፍራታቸው ያቆማሉ መንግስት የሚላቸውን ስምተው መንግስት በሚስጣቸው አስተያየት ኢንቨስትመታቸውን አርገው አገር ጠቅመው እነሱም ይጠቀማሉ።

እስቲ አስበው በምን ሂሳብ ነው ቲማቲም በሞላበት አገር የቲማቲም ሳልሳ የምናስገባው ። በምን ሂስብ ነው ከውጭ የድንች ጥብስ የምናስገባው።

ብዙ ብዙ ባልኩኝ ግን ለዛሬው እዚህ ላይ አበቃለሁ። ሌላው ደግሞ ለምን አስመጭዎች ለምን አገር ውስጥ ማምረት አይፈልጉም የሚል ጥያቄ ያስነሳል ። ይህም በጣም ቀላል መልስ አለው ። አስመጭዎች አየር በአየር ነው መስራት የሚፈልጉት ። ከስራተኛ ጋራ መዳረቅ አይፈልጉም ለምሳሌ የዘይት ፋብሪካ ቢከፍቱ ። እዛው ተላትመው ይቀራሉ ። የአሜሪካ እርዳታ ስጪ መጥቶ ከተማውን በነፃ ዘይት ቢሞላው አንተ ዘይት ህን ታቅፈህ ቀረህ ማለት ነው። ግን የዘይት አስመጪ ከሆንክ ። ነፃ ዘይት ከተማው ሲወረር በሁለተኛው ዙር ሌላ ነገር ማምጣት ትችላለህ። ለዚህም ብዙ ዘዴዎች አሉ እንዴ የአሜሪካን ሽር ሽውደን እንደምንበለፅግ።

አሜሪካኖች ረጂ ድርጅቶች ሳያውቁ የሚያረጉት እንዳይመስላቹሁ ። አንዴ ጃማይካ ቡዙ የወተት ምርት ታወጣ ነበር ። አሜሪካኖቹ ይህንን ኢንዲስትሪ ለመግደል ነፃ የወተት ዱቄት ሀገሪቱን አጥለቀለቁት ። የጃማይካኖች ወተት የሚገዛ ጠፋ ። ገበሬዎቹ ደግሞ ላሙዋን መቀለብ ብቻ ሳይሆን በየቀኑ አልበው መድፋት ነበረባቸው ። የዘይቱን ፋብሪካ ደግሞ ኤርሚያስ አማልጋን ጠይቁት እንዴት አሜሪካ እርዳት ከንግድ እንዳስወጣው ። ኤርሚያስ አመልጋ አሜሪካንን ሻጥር ካልቻለው እንዴት ያልተማረ አምጪና ላኪ የአሜሪካን ሽር ይችለዋል።

እኔ ታድያ ኤክስፕርት የሚያረገኝ የአሜሪካን ሽርን እንዴት አርጌ በእፍጢሙ ደፍቼ ። እነሱ ላይ ተጫውቼ ከንዘቤን እንደምስራ ስለማውቅ ነው። ይህንን በሌላ ግዜ ። ብቻ ይሄንንም ደጋግሜ ፅፌዋለሁ እዚህ ፎረም ላይ።

የብረት ዋጋ ተወደደ ያልከውም ብዙ ካላስገባን እራሳችን ቡዙውን ነገር አገራችን ውስጥ የምንስራ ከሆነ ። ገንዘብ ስለሚተርፈን ብረቱን ለመግዛት እንችላለን ። በዚህ ላይ ለምን የብረት ማቅለጫ ፋብሪካ አይኖረንም ። ምኑ ነው የሚያቅተን ። ግፋ ካለ አፃ ቴድሮስን ታሪክ ማማከር ነው።

Post Reply