ያሜርካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰክረተሪ ብሊንከን በነገው እለት ሹመቱ ይጸድቅለታል። ሰውዬ ለ25 አመት የሰራው ስራ ስለሆነ ሁሉንም ነገር በዝርዝር ያውቃል ።
የአፍሪካ ቀንድ በሚመለከት በጥቁቱ የተነሱት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው ።
ኢትዮጵያ በሚመለከት ወደ ዲሞክራሲ ተጀምሮ የነበረው ጉዞ ወደ ኋላ የሚመለስበት አደጋ አለ ይላል። ዎያኔን በዘር ፌዴሬሽን ስልጣን ላይ ያወጡት አሜርካኖች ኢትዮጵያ ከጎሳ ፖለቲካ እንዳትላቀቅ ቢሰሩ አያስገርምም ። ስለዚህ ነቅተን መጠበቅ አለብን ።
የትግሬ ጉዳይ በሚመለከት የእርዳታና ሁማኒታሪያ ቀውስ ሊነሳ ይችላል ብሏል ፣ ስለዚህ በአቢይ መንግስት ላይ ግፊት የሚፈጥሩ ይመስለኛ።
ሱዳን በሚመለከት የሱዳን መንግስት ፍራጃይል እስቴት ወይን ለመውደቅ የሚንገዳገድ መንግስት ነው። ሽግግሩም ፍራጃይል ነው ብሏል።
በትግሬና ሱዳን ያሉት ቀውሶች ያፍሪካ ቀንድ አጠቃልይ ብጥብጥ ሊሆን ይችላል ብሎአል ።
የዩጋንዳን ምርጫ አምርሮ ተቃውሟል።
የመን በሚመለከት ሁቲዎች ቴረሪስት ተብለው መፈረጃቸውን ይቃወማል ። ይህን ፍረጃ በቅርብ እንዲነሳ ያደርጋል ።
የሳዉዲዎች በየመን ጦርነት ይቃወማል ፣ ያሜሪካ ትብብርና እርዳታ ይቋረጣል
ሰውዬው ጠንካራ ይሁዲ ስለሆነ ፖሊሲው እስራኤል ተኮር ነው ።
አሜርካ ከቱርክ ጋራ ከባድ ቅራኔ ስላላት ግብጽና ቱርክ ሊቢያ በሚያደርጉት ሽኩቻ ወደ ግብጽ የሚያዳሉ ይመስለኛል።
ሌላው ትልቁ ነገር አሜሪካ የቻይናን ያለም ልዕለ ሃያልነት ፊት ለፊት ለመታገል ስለወሰነች ባፍሪካ ቀንድ አሜሪካና ቻይና ትልቅ ፉክክር ስለሚጀመሩ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሰዎች ተዘጋጁ እንላለን ።