‘ኮፍያቸው እንኳን’
ስታሊነ ትግራይ እንዴነህ ስታሊን፣
ዜናውን ሰማህ ወይ የ ‘ኣቦካ ስብሐትን’፣
‘ኮፍያቸው እንኳን አይገኝም’ ስትል፣
‘ባርኔጣቸው እንኳን አይገኝም’ ስትል፣
‘ከዘራቸው ሳይቀር’፡ ተገኝቷል ምን ልትል?

ወያኔ እንዳልኖረች ኢጦቢያን ቦጥቡጣ፣
ጁንታዋ እንዳልኖረች ኢጦቢያን መጥምጣ፣
‘ስብሐት’ እንዳልኖረች ትግራይን ደፍጥጣ፣
መምህር ነኝ ስትል መምህር የቆረጣ፣
መምህር ነኝ ስትል መምህር የመረጣ፣
ስትኖር ሳትጠረቃ ንጹሓን ጋግጣ፣
ግፉ ተደማምሮ ሰማይ ቤት ሲወጣ፣
መውጫው ጨለመባት ጫንያለው ሲመጣ።

ስትቋምት ልትኖር፡ ጁንታዋ አድፍጣ፣
በጥልቅ ገደል ውስጥ፡ ማይመች ለጦጣ፣

በወርቅ አምባ ዋሻ፡ ስብሐት ተሸጉጣ፣
መግቢያ መውጫው ጠፍቷት፡ በጨለማ አፍጥጣ፣
በቕዘት ስትባንን ጁንቲት ስትንጣጣ፣
እነ አዬዋ አወጧት ጠቅልለው በፎጣ።

‘ተራራ አንቀጠቀጥን’ ሲሉ እንዳልነበረ፣
ትዕቢቱ አልጠቀመም ጉራ ሆኖ ቀረ፣
ይህ ነው ታሪካቸው ሲያልቅም አላማረ፣
"ይውሓጥዋ እምበረ ናበይ ድሕርሕረ!"።


