የገና ጀምበር ፣ የንጋት ጨበር
የጽብሃ ኮከብ፣የጠጥበት ኢምር
ያሙነ ራዕይ ፣ የሰማይ የምድር
አስትሮ እሳት፣ የሶባ ጨረር
የሳባ ሃሩር፣ የበጋ አባር
የንጋት ገና፣ የጠዋት ጺዮን
ዬሎሄ ሶራ ፣ የቆሬ ብርሃን
ያዮ አይነቁር፣ የደራቃ አይን
የለሊት ጮራ፣ የቀናት በያን
የሶባ ጾራ፣ራዕይ የዛኘት
የገና ውልደት፣ የገና ፍጥረት
እንሰሳ ከሰው የተለየበት
አዳም ከምኝት የተነሳበት
ኮከብ ጭለማን ያሸነፈ እለት
የብርሃን ገና የብርሃን ልደት
ሆረስ አይነ ኩሉ
በ2021 ገና ዋዜማ