Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37111
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር: በውቅሮ አል-ነጃሺ መስጂድ በጎኑ በኩል ነው የተመታው:--የጁንታው ተግባር ነው!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 02 Jan 2021, 10:59

ሰበር መረጃ!
የጁንታው ተግባር ነው!!!
በውቅሮ አል-ነጃሺ መስጂድ በጎኑ በኩል ነው የተመታው ። ይህ ታሪካዊና ታላቅ የህዝበ ሙስሊም የእምነት መስጊድ መመታቱ በጣም አዝነናል። ለዚህም አዝንነናል ብቻ ብለን መግለጫ በማውጣትና በከንፈር መምጠጥ ብቻ ሳይሆን የምንገልፀው ያለምንም ግዜ ማባከን ጥገና እንጀምራለን።
በቅርቡም ጥገናውን ጨርሰን ህዝባችን እንዲገለገልበት እንዳርጋለን።
አል ነጃሺ ለትግራይ ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥንታዊ የእምነትና ታሪካዊ ቅርሳችን ነው። ይህንን ታሪካዊ ቅርሳችን መጠገን የዜግነት ግዴታችን ነው።
ከተለያዩ አለማትም የእምነቱ ተከታዬችና ታሪኩን ለመጎብኘት በመምጣት እንደ ሀገር ትልቅ ስምና ክብር የምናገኝበት ቅርሳችን ነው። ለዘላለም በክብር ከትውልድ ትውልድ እየተቀባበልን እናስተላልፈዋለን።
ከውስጥ የነበሩ ቅርሶች ተዘርፈዋል የሚባሉ ፈፅሞ የተሳሳተ ነው። ይህን የሚያራግቡት ማን እንደሆነ ግልፅ ነው የጁንታው ቅጥረኞች ናቸው።
በዚህ ሰአት ለምን እንደሚያራግቡት ላረጋግጥልህ እችላለሁ የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊና የህወሓት ባለስልጣናት ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ማመን በሚከብድ ስለደመሰሳቸው ነው።
ይህ ተስፋ የቆረጠ ጁንታ ህወሓት በስተመጨረሻ ብዙ መሰረታዊ ልማቶችን አውድሞ ነው የሸሸው አል ነጃሺ ከዚሁ አንዱ እንደሆነ ነው ከህዝቡ ያረጋገጥነው።
ለዚህም የሞተ ስርዓት ላይ መውቀሱ ትርጉም የለዉም ይልቅ ያለምንም ግዜ ማባከን አል ነጃሺ በቅርቡ ሙሉ ጥገና እናደርግለታለን።
ዶር አብርሃም በላይ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር።

tarik
Senior Member+
Posts: 37111
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Re: የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር: በውቅሮ አል-ነጃሺ መስጂድ በጎኑ በኩል ነው የተመታው:--የጁንታው ተግባር ነው!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 02 Jan 2021, 15:35

Please wait, video is loading...
https://www.facebook.com/10000248356150 ... 139070734/

Post Reply