Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42383
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 24 Dec 2020, 18:25
ዎያኔ ኢትዮጵያ ተከፋፍላ ስለተዳከመች አገር አፍርሰን ስልጣን እን ይዛለን ብለው ግዙፍ የስሌት ስህተት አድረገው በ30 ቀን ከምደር ገጽ ጠፉ !!
አሁን ደሞ ሱዳን እንዲሁ የኢትዮጵያ ወታደር ከዎያኔ ጋር ስለተወጠረ በዚህ እድል መሬት እንውሰድ ብለው ግዙፍ የስሌት ስህተት እየሰሩ ነው ።
ለምን በሉኝ?
አቢይና የኢትዮጵያ ሰራዊት በዚህ ሰአት ከፈተኛ የሕዝብና አገር ድጋፍ አላቸው ። ወታደሩ ከፍ ተኛ የዉጊያ ሞራል ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ ጎሳዎች ከምን ግዜም የበለጠ አንድ እየሆኑ የጎሳ ፖለቲካ ሁሉ እንዲሻር በመጠየቅ ላይ ናቸው። ልክ እንደ አድዋ ግዜ ሕዝቡ ባርበኝነት ላይ ባለበት ሰአት ነው ሱዳን የተሳሳተ ሂሳብ ውስጥ ያለችው ።
አቢይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ አድርጎ የጎሳ ፖለቲካን እስካዳከመ ድረስ ኢትዮጵያ የሰሞኑን ችግሮች ሁሉ በድል ታልፋለች ። አንድ የሆነ ሕዝብ ማንም አይበግረውም ።
-
Guest1
- Member
- Posts: 1926
- Joined: 28 Dec 2006, 01:02
Post
by Guest1 » 25 Dec 2020, 01:02
ኢትዮ ጦርነቱን እንደምንም ትወጣዋለች። ዛሬ የያዙትን መሬት ይለቃሉ። ዋናው ችግር ያለው ፓለቲከኞቹጋ ነው። ሶማሌ ስትወር ተሰሚነት የነበረው ኢህአፓ ደርግን ተቃውሞ ነበር። በመንግስት ስልጣን ላይ የነበረው መኢሶንም እንደዝሁ ተቃውሞ በማሰማቱና ደርግንም ለመተካት ሲሞክር ተባሮ እንዲፈረጥጥ ተደረገ።
ቲየሪው ምን ይላል? ሁለት አገሮች ወደ ጦርነት ሲገቡ፤ የሁለቱ አገር ህዝቦች አፈሙዛቸውን ወደ ጨቋኙ መንግስት ያዙሩና የራሳቸውን ህዝባዊ መንግስት ያቋቁሙ። በህይወት ሳይሆን በቲየሪ ተመርተው የኢትዮና የሶማሊያ ህዝብ መሃከል ምንም አይነት ስምምነት ሳይኖርና የሁለቱ አገሮች ፓለቲከኞቹም ሳይነጋግሩ፤ እንደ ጠላት የሚተያዩ የኛዎቹ ፓለቲከኞች አንድ አቁም ይዘው ከአገር ወራሪ ጎን ተሰልፈው የህዝባቸውንና የወታደሩን ሞራል ገለው፤ በራሺያ ታንኮች ትንሿ ሶማሊያ ታግዛ አዋሽ ደረሰች።
አሁን የፓለቲካ ክፍፍሉ የከፋ በሆነበት ሁኔታ አንድነት አለ ማለት ይከብዳል። አንድነት የተፈጠረው በአንድ ምክንያት ነው። የአማራው ሃይል ሲጎለብት አንድነት ይፈጠራል። የአማራው ሃይል ሲዳከም የአንድነት ስሜት ይጠፋል። አሁን የደረስኩበት አዲስ ቲየሪ ነው።
