ያልተይዙት ባለስልጣናት ያሉበት ቦታ የታወቀ ሲሆን መንግስት አሉበት በተባሉት አካባቢዎች የቤት ለቤት አሰሳውን ቀጥሏል:: በጥይት ተመተው ከተያዙት ከፍተኛ የህወሃት ባለስልጣናት ውስጥ አክቲቪስቶች፣ ከአሜሪካና አውሮፓ የገቡ የህወሃት አፈቀላጤና ገንዘብ አዘዋዋሪዎች እንደሚገኙበትም ተረጋግጧል:: የቆሰሉት የህወሃት አመራሮችን ህይወት ለማትረፍ ርብርብ እየተደረገም ነው:: የሞቱትና የቆሰሉትን ከፍተኛ የህወሃት ባለስልጣናት በስም ለማጣራት የተደረገው ጥረት አልተሳካም:: መንግስት ዛሬ ወይንም ነገ በጉዳዩ ላይ እና እነማን እደተያዙ እነማን እንደቀሩ መግለጫ ይሰጣል::
ከተያዙት የጁንታው ካድሬዎች ውስጥ "እንደ መንግስቱ ሀይለማርያም አብይን የማምለጥ እድል እንኳ አንሰጠውም" ሲል የነበረ አለበት ተብሏል:: "ከዛ ሁሉ የተንበሸበሸ ኑሮ ከዛ ያማረ አልጋ ቤት መኪና ወርቅ ምግብ መጠጥ በብርሀን ፍጥነት ከነዚህ ሁሉ ነገሮች ወርደህ ልብስህ ጫማህ ተቀዳዶ ቆሽሸህ ገርጥተህ እንደ ልጅ እያለቀስክ ቦሀቃ ስር ከአብሲት ጋር ከመያዝ ሞት ይሻላል"
አንዳንድ የጁንታው አባላት አመራሮች ጫማቸው ልብሳቸው ተቀዳዶ ቆሽሸውና ገርጥተው የምስኪን ገበሬ ቤት ማድቤት ውስጥ ቦሀቃ ስር የተገኙ ሁሉ አሉ
እንፈጫቹሃለን ሲል የነበረው፣ ዱቄት ኩሽና እየፈጨ ሲያዝ ..... ኢማጂን ...... አለ ዶክሌ .....

