Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42343
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የመቀሌ ጦርነት ወደ መቀሌ ረሃብ ይለወጣል

Post by Horus » 24 Nov 2020, 17:38

ለምን በሉኝ?

ይህ ወሮበላ ጁንታ እጁን ካልሰጠ ጦርነቱ ብዙ ግዜ ይወሳዳል ከተማው ራሱ ሊፈርስ ይችላል ። ለምን?

የመቀሌ ሕዝብ ቁጥር ከ320 ሺ አይበልጥም። አሁን ሸሽቶ መቀሌ የተከማቸው ልዩ ሃይል ምናምን እስከ 100 ሺ ይደርሳል ብንል የከተማው 1/3 ወይም 1/4 ናቸው ማለት ነው ። ይህ ላንድ ከተማ ብዙ ነው ።

ጦርነቱን አጭር፣ ሰርጂካል ኦፐሬሽን ከመሆን ወደ ከተማ የመንገድ ዉጊያ ከተለወጠ የከተማው መፍረስ ብቻ ሳይሆን ...

በዉሃ፣ ምግብ፣ ጽዳት እጦት ረሃብ፣ በሽታ፣ ወረርሽኝ ይነሳል ። ኮቪድ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

ለዚህ ሁሉ መፍትሄው ባስቸኳይ የከተማው ነዋሪ ሕዝብ ግዙፍ ሰልፍ ጠርቶ እነዚህ ከተማ ውስጥ ተደብቀው የሚያስጨርሷቸውን ሌቦች ከተማ ለቀው ወደ ሚሄዱበት እንዲሄዱ መጠየቅ ላለም ማሳየት ።

ከቻሉ ደሞ ከኢትዮዮጵያ ሰራዊት ጋር ኮሚኒኬሽን ሰርግተው ሌቦቹ ያሉበትን ቦታ መንገር ነው ።

አለዚያ እነሱም ከጁንታው ጋር ያልቃሉ ማለት ነው።

ኢትዮጵያ በምንም አይነት ይህን የግብጽ አምስተኛ ረድፍ ጁንታ ሳትደመስስ ወይ ሳታስር ጦርነቱ አይቆምም


Last edited by Horus on 24 Nov 2020, 17:56, edited 1 time in total.



Post Reply