Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Ejersa
- Member
- Posts: 3978
- Joined: 05 Nov 2019, 10:39
Post
by Ejersa » 10 Nov 2020, 10:27
በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመውን ግፍ በጨረፍታ ነግረውኝ እምባዬን መቆጣጠር እንኳን አልቻልኩም። "ወደ ሰላሳ የሚጠጉ ወታደሮችን ገድለው ልብሳቸውን አውልቀው ሬሳቸን አንድ ላይ ከምረው ሌሊቱን ሙሉ ሲጨፍሩ አደሩ" ሲሉኝ በስመዓብ ብዬ አማተብኩ። በዚህ ላይ "አሁንም ድረስ አስክሬናቸው አልተቀበረም። አሞራና ጅብ እየበላው ነው" ሲለኝ መሸከም ከምችለው በላይ ሆነብኝ። ዝርዝሩን ዛሬ ማታ በቲቪ ይተላለፋል። ለዚህ ግፍ ፍርድ የሚሰጥ አካል በምድር ላይ ያለ አይመስለኝም። በውስጤ የተሰማኝ ሰቀቀን አዕምሮዬ መሸከም ከሚችለው በላይ ነው። የሰው ልጅ በዚህ ልክ ይዘቅጣል ብዬ አስቤ አላውቅም። እንዴት አስክሬን ተከብቦ ይጨፍራል? እንዴት የሰው ልጅ አስክሬን ሜዳ ላይ ተጥሎ አሞራና ጅብ ይበላዋል? ይሄ እኮ የሰው ልጅን ተፈጥሯዊ ባህሪ ይፃረራል። የፈጣሪ ያለህ፡፡
ስዩም ተሾመ
