Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12910
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

"Yes, I left, but never abandoned my job" Engineer Takele Uma

Post by DefendTheTruth » 13 Oct 2020, 07:36

ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 178 ሚሊዮን ዶላር ከማዕድናት ገቢ መገኘቱ ተገለጸ!
የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትሮ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ባለፉት ሶስት ወራት በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው እንዳሉት ባለፉት ሶስት ወራት በኢትይጵያ ተመርተው ወደ ውጭ አገራት ከተላኩ ማዕድናት 178 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩ ባለፉት ሶስት ወራት 750 ኪሎግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ አቅዶ 2241 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ውጭ አገራት መላኩ ተገልጿል።
ለአገር ውስጥ ከቀረቡ የኢንዱስትሪ እና የኮንስራክሽን ማዕድናት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል።
የስራ እድልን ከመፍጠር አንጻር ደግሞ በሶስት ወራት ውስጥ ለ30 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ ተገልጿል።
የኦፓል ምርትን በተመለከተ ደግሞ በባህላዊ ምርት 675 ኪሎ ግራም ተመርቶ ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን 21 ኪሎ ግራም ኦፓል ደግሞ እሴት ተጨምሮበት ለውጭ ገበያ ቀርቧል ተብሏል።
(ኢትዮ ኤፍኤም 107.8)
በጣም በጣም ዝቅተኛ ነው። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ህገወጥ የማዕድን ሥራዎች ብሎም ወረራ ሥርዓት ብታሥዩዝት ከቢሊየን ዶላር በላይ ማግኘት ይቻል ነበር።

From the following FB page:

https://www.facebook.com/Dagnebeyene