(ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)
==========================
የአብይ አስተዳደር አይነተኛ መገለጫው ፍጥጥ ያለ አይነ ደረቅነት እየሆነ ነው! ይህ ህሊና ቢስነት ነው!
በእርግጥ ስህተቶቹም ሆነ የባለስልጣናቱ አይነ ደረቅነት ከግብረ ገብ ችግር የመነጩ አይደሉም፤ በሁሉም ልብ ውስጥ የተቀበረ #ኦሮሙማ የሚባል ለአንድ ብሄር የመቆም ዝንባሌ ስላለ እንጂ።
ህሊና ቢስ መሆናቸው የሚገለጥባቸው የሄዱበትን ዘረኛ አካሄድ ከተሰጣቸው ሃላፊነት ጋር ለማስማማት የሞከሩ ጊዜ ነው። ኦሮሙማ ሁሌም ወንጀል ሲሰሩ በህሊናቸው ምትክ መንፈሳቸውን የሚያስታምሙበት ሚዛናቸው ነው!
ለአንድ ቡድን ተጠቃሚነት ሲሉ የሰሩትን ወንጀል በዚህ መልኩ ትክክለኛና የሚያኮራ ስራ አድርገው ማውራት ይጀምራሉ። ነገር ግን ይህ ህገ ወጥነት ነው፤ አደራን መብላት ነው፤ እምነትን ማጉደል ነው፤ ህዝብን መስደብና መናቅ ነው።
~~
እየሆነ ያለው ነገር አስቂኝም አስደናቂም ነው። ህወሃትን "የቀን ጅብ" ብሎ ሲሳደብ የነበረው የአብይ አስተዳደር "የተራበ ጅብ" ሲሆን ማዬት ያሳፍራል። በአይናችን እያዬን የሚፈፀመውን በደል እንኳን እንደሚኮራበት የሚናገር አይነ ደረቅ ሆኖ አረፈው።
የአብይ አስተዳደር አይነተኛ መገለጫው ፍጥጥ ያለ አይነ ደረቅነት እየሆነ ነው። ለምሳሌ፦ አማራንና አማርኛን የሚያጥላላ ንግግር ይናገርና "አማራና ኦሮሞ ደም ቅዳ ደም መልስ ነው" ይላል። "አማርኛ እንዲዳከም እየሰራን ነው" ባለበት አፉ "አማራና ኦሮሞን ለመነጣጠል የሚደረገው ሙከራ አይሳካም" ሲል እንሰማዋለን። "ነፍጠኛን ሰብረነዋል" ካለ በኋላ "የአማራ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው" ይላል።
ሌላው ቀርቶ በቅርቡ የተጋለጠውን የቤትና የመሬት ህገወጥ ወረራ የቀድሞው ከንቲባ እንደሚኮራበት በግልፅ የተናገረውን አንረሳውም። የሰራው የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እንኳን "ወረራው ትክክል ነው፣ ህገ ወጥ ስራ በመስራቴ እኮራለሁ፤ እንዳውም ብዙ ወንጀል ባለመስራቴ ይቆጨኛል" ሲል ተናገረ። ተቋማቱ በሙሉ ስለ ፍትህ አይጠይቁም፤ በፊት የነበሩ ተቋማት ሳይቀሩ በልምሻ የተመቱ ይመስል እንዳለ ሽባ ሆኑ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀር በህግ እንዲጠየቅ ወይም ሌላ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ ሲገባው ጭራሽ የሌላ ዘርፍ ሚኒስትር አድርጎ ሾመው። አስተዳደሩ "ብዙ ያጠፋ ብዙ ይሾማል" በሚል ብልሹ የማፊያ መርህ የተቃኘ ሆኗል።
የአብይ አስተዳደር ወጣ ወረዱ በዚህ ህሊና ቢስነት የተጠመቀ በመሆኑ እንጂ በኦሮምያ ክልል የዘር ፍጅት ጥሪን "ሀ" ብሎ የጀመረውና። በቅርቡ ግልፅ የጥላቻ ንግግር የተናገረው ሽመልስ አብዲሳ እና አዲስ አበባ ላይ ያን ያህል በደል የፈፀመው ታከለ ኡማ ለህግ መቅረብ ነበረባቸው። ዳሩ ግን አስተዳደሩ ከህግ በላይ፣ አመራሮቹም ህገ ወጥ ናቸውና ጥፋታቸውን እንደያሳፍራል የሚናገሩ ህሊና ቢሶች ሆኑ።
ያሳፍራል!
ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
