Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

አቶ ጃዋር መሃመድ በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶችና ከውጭ በድብቅ የገቡ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አማካኝነት የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሚስጥራዊ ጉዳዮችን ሲያዳምጡ እንደነበር ...

Post by Za-Ilmaknun » 29 Jul 2020, 14:22

(ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር መሃመድ ቤት በድጋሚ ባደረገው ፍተሻ በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶችና ከውጭ በድብቅ የገቡ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ማግኘቱን ገለጸ።

አቶ ጃዋር መሃመድ በዛሬው እለት በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ልደታ አዳራሽ ቀርበዋል፡፡
መርማሪ ፖሊስም ባለፉት ቀናት ያከናወናቸውን ስራዎች በጠቀሰበት ሪፖርቱ በአቶ ጃዋር መኖሪያ ቤት በድጋሚ ባደረገው ፍተሻ መሳሪያዎቹን ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በመሳሪያው አማካኝነትም የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሚስጥራዊ ጉዳዮችን ሲያዳምጡ እንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በርካታ ተጨማሪ አዳዲስ ግኝቶችን በምርመራ ማግኘቱን ለችሎቱ ይፋ አድርጓል።

አቶ ጃዋር በበኩላቸው የፖሊስ ምርመራ እኔን አይመለከትም ይህ የፖለቲካ ጉዳይ ነው ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።