Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40302
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ናይል የሚለው ስም በአባይ ሊለወጥ ነው! ዬቦ! ኤቦ !!

Post by Horus » 24 Jul 2020, 15:17

Guest1 & Abere

ልብ በሉ አንድ ጽንሰ ሃስብ ወይም ጽንሰ ነገር የምንገልጸው በሚታፎር (በመሰፈር) ነው ። ሌላ ዘዴ የለንም። የዘር ዛፍ እንላለን ። ግን የሰው ዘር ትወልድ ዛፍ አይደለም ። ማንኛውም ሃስብ አስመስለን (በምሳሌና ምስል) የምንወክለው አንድ ምስል ወደ ሌላ ነገር በማሳፈር (በማሸጋገር) ነው ። እጅግ በድሮ ቀምት ቋንቋ 'ሃ/ካሃ' ከፍተኛ ታላቅ ማለት ነበር ። 'ባ' ፍጡር፣ ሀይወት ያለው ብሎም ሰው ነበር ። አባት ሌላ ትርጉሙ ፈጣሪ ማለት ነው፣ (ልጅ ስለሚፈጥር)። አቢ (ሰጪ/ሀይወት የሚሰጥ) እያለ በሚታፎር ሃሳብ ሲስፈፋ ምሳሌዎች ካንዱ ኮኔፕት ወደ ሌላው እየተወሰዱ ነው ይህን ሁሉ እውቀት የገነባነው ። ስለዚህ አባይ የናይል አምላክ መባሉ ሜታፎር ነው ። የህይመት ምንጭ ስለሆነ አባት መባሉ ሜታፎር ነው ። ፈጣሪ ደሞ በትልቅ ነገር መመሰሉ ሜታፎር ነው ። ሰማይ ከኛ በጣም የራቀና ታላቅ ነገር ነው ። መሬም እንዲሁ ። እግዚአብሄር በሰማይ ይኖራል ሁሉም ሜታፎርች ናቸው ። የሰው ልጅ ሃሳብ የምንለውን ነገር ምናብ (ኖሽን) በድምጽም ሆነ በሰዕል ለመግለጽ ከሜታፎር ሌላ መሳሪያ ወይም ዘዴ የለንም ። ይህ ነው የቋንቋና ግንዛቤ (language and cognition) ሳይንሳዊ መሰረት ።

አባይ ታላቅ ወንዝ ነው። አባይ አባት ነው ። አቢይ ታላቅ ነው ። ነገር ግ ን ቃሉ ሲለሰልስ አ ባይ እምቢተኛ የሚለው ሰሩ ሌላ ነው ። አ አፍርራሽ + ባይ = እምቢ ባይ ማለት ነው ። ሃለ/ አለ አደረገ ማለት ነው በሴም ቋንቋ ። ያም ሆነ ይህ አባይ ትክክለኛው የወንዙ ስም ነው ። ናይል ደጋግሜ እንዳልኩት የግሪክ ቃል ሲሆን የወንዝ ሸለቆ ማለት እንጂ ታላቅ ወንዝ ማለት አይደለም ። እውነትኛውን ያባይ ስም ያኖርን እኛ ነን ፣ መቴ አረቦቹ የግሪኩን ስም ነው ይዘው ያሉት ።

Post Reply