Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39769
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Horus » 21 Jul 2020, 02:18

ኢዜማ የኦሮሞ ተስፋፊና ሄጂሞኒስቶች ተላላ አጋር አሁን የመጨረሻውን ትምህርት ወሰደ ። ሌላው፣ ሌላው ቢቀር የኦሮሞ ቴረሪስቶችና ነፍሰ ገዳዮች ሰላማዊውና በኦሮሞ መንግስት ተማምኖ ወደ መኛታ የሄደውን ሕዝብ ከእንቅልፉ የመቀስቀስ እና ነፍሱን የማዳን ዝግጅት እና ኢንተለጀንስ የሌለው ፓርቲ ሆኖ መገኘቱ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ፋይዳ ቢስ፣ የቆመለት ሶሺያል መሰረት ማ እንደ ሆነ የማያቅ የኦሮሞ ሄጂሞኒ እቅድ አጃቢ ሆኖ የቀረ ፓርቲ ሆኖ ከማየት የበለጠ ሚያበሳጭ ነገር የለም ።

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by TGAA » 21 Jul 2020, 02:40

የፈራ ተባው የኢዜማ ፖለቲካ ሆሮስ አንተ እንዳልከው በጣም አቋም የሌለው ፤ መሽልመጥመጥን ደግሞ የአርቆ አስተዋይነት ምልክት አድርጎ የሚያቀርብ ፤ የብልጽግናን ፓርቲ የህልውናው ዋስትና አድርጎ የሚቆንጥር ፤ በልመና የተሰማራ የፖለቲካ ድርጅት ነው፡፡ "የለውጡ አካልን ለመደገፍ የሚሉት ባዶ አባባል ኢዜማ ሳያሳልስ ይለፈልፋል" ፤ እውነት የለውጡ አካላ ወይም ለውጥ የሚፈልግ ከሆነ የኢዜማ ፖሪንሲፕልድ አቋም መያዝ አብይን እንደመደገፍ እንጂ ለለውጡን ማደናቀፍ ሊሆን አይችልም፡ ይህ አይነት ከፍርሀቻ አንዳንዴም የመሽኮርመም ፖለቲካ ነው የዘውግ ፖለቲከኞችን ተዳፍረው የቀን ጭፍጨፋ እንዲያደርጉ ያበረታታቸው ፡፡ ብዙ ተስፋ የተጣለበት ድርጅት እንዲህ ልፍስፍስ እንኳን ሀገር አባሉን መከላከል የማይችል ሁሉንም ነገር ባማላጅ እፈታለሁ ብሎ የተነሳ ድርጅት ሆኖ መገኝቱ በጣን የሚያሳዝን ነው፤ ሁልግዜም የሚረባ ትርጉም የሚኖረው ፓርቲ ሊሆንም አይችልም ፡ ህዝቡ የጊዜ ጉዳይ ነው የራሱን የልቡን የሚወክል የፖለቲካ ድርጅት ይወልዳል ፡

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Guest1 » 21 Jul 2020, 03:16

ክ107 ተቀንሰው ስንት ሆኖ 90? የሚሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖራቸውና ኣብዛኞቹም የብሄር ፓርቲዎች መሆናቸው የመላ አገሪቱን ችግርና መከፋፈል እንጂ የኢዜማን ድክመት ኣያሳይም። እንዲያውም ጸንተው በህብረብሄር ድርጅትነት መቀጠላቸው ጥንካሬን የሚያሳይ ነው። ሌላው ኢዜማ ብቻውን ምንም ማድረግ ኣይችልም። ኣሁን ተመልካች የሆነውም በሽግግሩ መንግስት እምነት ስላጣ ይመስላል። አንድ ዋና አባሉ ታስሮበት የለ?

ለምን ሌላ ድርጅት ኣይቋቋምም ለሚለው መልሱ ያሉትም መሰብሰብ እያቃታቸው ሌላ ድርጅት ምን ሊፈይድ? እነዝሁ ተቃዋሚ ፓርቲ ነን የሚሉት አንድነት ከፈጥሩ ወይም ሲበተኑ ወይም ሲከስሙ ኢዜማ ይጀግን ይሆናል። ጊዜው የመደንፋት ሳይሆን የስራ ጊዜ ነው። ለመደንፋት ጊዜው እሰከሚፈቀድ ድረስ ድርጅታዊ ስራቸውን ከመቀጠል ሌላ ምርጫ የላቸውም።

Wedi
Member+
Posts: 8598
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Wedi » 21 Jul 2020, 03:17

በጣም የሚገርም ትንታኔ። ትላልክ እና የስንት አመት እድሜ ልምድ አለኝ የሚለው ልማታዊ ጋዜጠኛ ሁሉ የምታስንቁ ወጣት አናሊስት ናችሁ!! በርቱ!!

Genesis
Member
Posts: 161
Joined: 29 Jul 2018, 15:13

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Genesis » 21 Jul 2020, 04:00

Hello Horus,

I hope you remember me. Thank god you come to your senses
You didn’t like it when I told you ginbot 7 was a sell out and it’s leader Birhanu was a hired spy working for the west. But you didn’t listen. Ginbot 7 the now ezema was an opportunist organization then and still is. Forget the request for intelligence, Birhanu has no principle at all. Who was massacred now in Oromo land, Amara and Gurage mostly. Let alone Ethiopia, can Birhanu speak for his relatives the hard working gurages when they are killed? Not at all. This is what happened when you support charlatans like Birhanu, he disappointed you. Better late than never now you understand. The only solution for all of this is when the Gurage, Amaras and other Ethiopian victims stand up together and defend themselves. I was visiting the Amara region a few months ago, I have seen too many Gurages living and as usual working hard running their business. When I talk to them they are happy and feel at home in Amara provinces. My advice to you is never ever support people like Birhanu as they call him bir amtu Nega. You thought then I was insulting him because he is from Gurage ethnic but you were wrong. He is a different breed very shrewd man who can sell his mom for a dime like he did to Ethiopia. Stay focused one day judgment will be served for people like him. Sorry if I am harsh on you and I am glad you are back to the fold. I know you are wise but sometimes standing for a kin is normal and sometimes it is better to investigate when others stand against your kin. This is how truth guides all of us. You stand for Birhanu before when most people are against him because of his opportunist behavior and now you realize the truth on his stand. That makes you wiser, welcome to the club.

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Guest1 » 21 Jul 2020, 04:21

ኢዜማ የሚወቀሰው በምን ምክንያት እንደሆን በግልጽ እውነቱን የሚናገር የለም። ከጥላቻ በስተቀር። ኢዜማን የሚጠሉት እነማን ናቸው? የብሄር ፌድራሊስቶችና የብሄር ፓርቲዎች እና .... በዝርዝር እነማን?

ልማታዊ ጋዜጠኛ ኣድርባይ ጋዜጠኛ ለማለት ነው? ቀልዱ ተመችቶኛል።

Lovetarik
Member
Posts: 357
Joined: 10 Apr 2018, 00:39

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Lovetarik » 21 Jul 2020, 07:14

አዜማ ሽብርተኞችን ከማውገዝ ይልቅ አስክንድርን በመኮነን ስራ ላይ ተጠምዷል። የአዜማ ነገር "የት ይደርሳል የተባለውን ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው" ነው

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Guest1 » 21 Jul 2020, 07:57

የእስክንድር ችግር ያለ ኣቅሙ በመንጠራራቱ ብቻ ሳይሆን ዋናው አጄንዳ በማስቀየሩ እነ ኢዜማ ኣልተደሰቱም። በተለይ ከመንግስትና ከስም ኣይጠሬዎች ጋር ፊት ለፊት ግብግብ መፍጠሩ መስመር የሚያስለቅቅና የሚጎዳም ስለነበር በጣም አልፈለጉትም። ለምን ያለ ... ለማን ይተርፋል ይባላል።

በግሌ ከሁሉም ከሁሉም ኣስገራሚ ሆኖ ያገኘሁት ሲነገረው የማይሰማ ሰው መሆኑ ነው (የሃበሻ ባህሪይ ነው፤ አይደል?)።

Bashu
Member
Posts: 808
Joined: 19 Mar 2009, 22:24

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Bashu » 21 Jul 2020, 08:25

What do you expect from a party headed by Qes Mogesse. Awdma is my favorite political program out of Ethiopia but I worry about the safety of the participants. They are good and fearless. I hope the 7th king won't send them to jail like Eskender by concocting some non existing crime.

Lovetarik
Member
Posts: 357
Joined: 10 Apr 2018, 00:39

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Lovetarik » 21 Jul 2020, 08:30

ይህ ደካማ ምክንያት ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ በአደባባይ ሲፈናቀል ደምጹን ማሰማቱ ጀግና ይስብለውል እንጂ አያስወቅሰውም። መወቀስ ያለበት ጭራውን በእግሮቹ ስር አድርጎ ለስልጣን የሚሮጠው የአዜማ አመራር ነው። እድሜ ለአስክንድር አንተም ዛሬ ለመተንፈስ በቃህ። እስክንድር ባይኖር ኖሮ ዛሬ አዲስ አበባ እንደሻሸመኔ ነበረች

quote=Guest1 post_id=1087407 time=1595332671 user_id=60]
የእስክንድር ችግር ያለ ኣቅሙ በመንጠራራቱ ብቻ ሳይሆን ዋናው አጄንዳ በማስቀየሩ እነ ኢዜማ ኣልተደሰቱም። በተለይ ከመንግስትና ከስም ኣይጠሬዎች ጋር ፊት ለፊት ግብግብ መፍጠሩ መስመር የሚያስለቅቅና የሚጎዳም ስለነበር በጣም አልፈለጉትም። ለምን ያለ ... ለማን ይተርፋል ይባላል።

በግሌ ከሁሉም ከሁሉም ኣስገራሚ ሆኖ ያገኘሁት ሲነገረው የማይሰማ ሰው መሆኑ ነው (የሃበሻ ባህሪይ ነው፤ አይደል?)።
[/quote]

Wedi
Member+
Posts: 8598
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Wedi » 21 Jul 2020, 09:20

ኢዜማ/ግንቦት 7 ኢትዮጵያ ከገባ ወዲህ ለአብይ ያደረገው ወዲህ የአብይን ስም ለማስጠፋት የቀድሞ የኢዜማ/ግ ን ቦት 7 አባልት የነበርቱን እና የባልደራስ አመራርን እና አባላትን ኢዜማ/ግንቦት 7 እንዲታሰሩ በማድረቅ እየተበቀላቸው ይገኛልል፡፡ ለምሳሌ አስቴ ስር ስዮም የተባለች ኢዜማን ለቃ ወደ ባልደራስ የተቀላቀለችን ወጣት ኢዜማ/ግንቦት 7 በሰሞኑ የሃጫሉን ግርግር ተከትሎ ኢዜማ/ግንቦት 7 እንድትታሰር አድርጓል፡፡

ኢዜማ/ግንቦት 7 በጣም አሳፋሪና ሴረኛ ድርጅት ነው፡፡

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Guest1 » 21 Jul 2020, 09:51

ስላማዊ ትግል ጭራ መቁላት ከሆነ እስክንድር ነጋም ስላማዊ ታጋይ ነበር። ታጥቆ ጫካ ኣልገባም አንድም ጥይት ኣልተኮሰም! ታስሯል። ጀብደኝነት ኣቅምን ኣለመገመት ነው።

‘’እድሜ ለአስክንድር አንተም ዛሬ ለመተንፈስ በቃህ። እስክንድር ባይኖር ኖሮ ዛሬ አዲስ አበባ እንደሻሸመኔ ነበረች።’’ ሃሰት! ኣዲስ ኣበባ ሻሻመኔ የምትሆነው ኣራት ኪሎ የፈረሰች እለት ብቻ ነው! እውነቱ እስክንድር ኣዲስ አበቤው እንዲጠቃ ምክንያት ሆኗል።

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by TGAA » 21 Jul 2020, 14:03

Gust1, talk is cheap. If you think wiggling your tail whichever side the wind goes is part of the peaceful struggling, you need to stop scrabbling and flip a book or two about peaceful struggle .Eskender has a back of Steele to be truffled by nobody,such as yourself. When looking up not let alone standing up to weyannes was a kiss of death, Eskender stood up for the principled his paying dearly now at the time of " so called reformist. He didn't not end up in prison to be satisfied by Chang of guard from Tigry Etho dectatorship to one of Oromo. Your conclusion that the only time Addis could turn in to shasemane is when Arat killo gets destroyed is dummy. If you wanted to destroy Addis or Ethipian that is where Ethiopian enemies will aim at, that is why weyan's send 300 armed military to palace , that is why jawar fought to bury Hachallu in Addis to gather his genocidal keeros and make Addis or your Arat killo into shasemane. What a dork? You don't have to think to know this.

Abere
Senior Member
Posts: 14738
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Abere » 21 Jul 2020, 14:43

የደረስንበት ዘመን በእውነት የሚያሳዝን ነው። ክፉ እና መልካም መለየት የማይችል ወይም ዋሽቶ አደር እርጉም ማህበረሰብ ማየታችን። በትንሹ መታመን ያልቻለ ህዝብ እንዴት በትልቅ ጉዳይ ሊታመን ይችላል። ምን ዓይነት ኅሌና ነው እስክንድርን ለመወንጄል የሚሞክር። ዐብይን መደገፍ ማለት ዐብይ መሥራት ያቃተውን ወይም አውቆ ተደብቆ የተወውን ትልቅ ኃላፊነት በጀግንነት የተወጣውን በድፍረት ለመዝለፍ የሀሰት ትንታግ መሆን አይደለም። ትንሽ ሰው ይታዘበናል አትሉም ካልሆነም አርፎ መቀመጥ እኮ እራሱ ዐብይን መደገፍ። እስኪ ምን ትልቅ ነገር ነው ዐብይ የቀየረው አስረዱን። ወያኔ መቀሌ ማገገሚያ ጣብያ እንድ ገባ ማድረጉ፣ አውሬን ኦነግ ከአሥመራ እና አሜሪክ አምጥቶ ለትንግርት ሰው ማሳረዱ፣ መቼም የታሰረ ፈታ ካልችሁ ያስቃል ወያኔ ሲሄድ እስረኛ ጠባቂ ስለሌለ ተፈቱ ነው የምለው እኔ፣ የአገሪቷ መበጥበጫ እና የሁከት አስማት የሆነው ኢ-ህገመንግሥት በሥራ ላይ ከመዋል ስለታገዴ፣ ወይስ የአምባሻው ባንዲራ ዐብይ በሄደበት ሁሉ ስለተውለበለበ ፣ እንዴ አሸን የጎሣ ፓርቲ እና አዳድስ የጎሳ ክልሎች ስላዋለዴ፣ ከተሞች ስለተደፈሩ፣ ወዘተ። ምን ለውጥ መጣ። በእርግጥ ለዐብይ ይኸ ሥራ እጅግ ይከብዳል - ግን ፊቱን እንጅ ልቡን መቼ ሰጠ። የዐብይ ልብ ያለው አልቆረጠም ከወያኔ የጎሳ መተት ጋር የተሳሰረ ነው። የጎሳ እትብት ተቆርጦ እስካል ወደቀ ገና አሥርት ዓመታት አዳሜ እየሞተ ሲያወራ ይኖራል። The people of Ethiopia, especially the so called elites, have a long way to differentiate right from wrong. Sorry for the generalization. Because the identifying the Ethiopian core problem is not a nuclear science. We have a self identified problem.

Horus
Senior Member+
Posts: 39769
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Horus » 21 Jul 2020, 15:20

እኔ የኦሮሞ አክራሪ አይደለሁም። እኔ የአማራ አክራሪ አይደለሁም ። እድሜ ልኬን የጎሳ ፖለቲካ የምቃወም የኢትዮጵያዊነት አማኝ ነኝ። በመሆኑም በፖለቲካ እምነቴ ከኢዜማ የሚቀርበኝ ሌላ ፓርቲ የለም ። በጭፍን ጥላቻ፣ ቂምና በቀል ከሚቃጠሉት ፈጣሪ ይጠብቀን ።

እኔ ዛሬ አሁን የማየው የኢዜማ ችግር ድርጅታዊ ፍዘት ወድቆበታል የሚል ነው ። የፖለቲካ ዳይናሚክስ ልክ እንደ ከረምቦላ ጠር ረጴዛ ላይ እንዳሉት ጠጠሮች ነው ። አንዱ ጠጠር ሲመታ ሁሉም ይነቃነቃሉ ። የኢዜማ ጠጠር ሲነቅነቅ አይታይም ። ለምሳሌ፣ የኢዜማ ማህበራዊ መሰረት (ሶሺያል ቤዝ) ከተማዎች፣ በኢትዮጵያዊነት አማኞች፣ ባብዛኛ የደቡብ ክልል ህዝቦች ናቸው ። የኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ ወዘተ ብሄረተኛ ኢዜማን አይወዱም። ያም ስለሆነ የዘር አጥፊዎች ከተሜንና ኢትዮጵያዊያንን ለማውደም ሲደራጁ፣ ሲዘጋጁ ቢያንስ ኢዜማ እንዴት መረጃ እንኳን ለተጠቂዎቹ በማድረስ እንዲጠነቀቁ አላደረገም? ዛዲያ የዚህ ፓርቲ ለዚያ የጄኖሳይድ ሰለባዎች ምናቸው ነው? ነገስ ቢሆን ለምን ይከተሉ? ለምን ይመኑት?

ሃጫሉ በተገደለ ማታ አሸባሪዎች ለሊቱን ሙሉ በመላ ኦሮሞ ሲደራጁና ሲቀናበሩ ኢዜማዎች ለሊቱን ሙሉ በየከተማ ህዝቡን ሲያስጠነቅቁ ቢያደሩ ነበር የዚያ ፓርቲ ፋይዳ በህዝቡ ዘንድ በተግባር ይታይ የነበረው ። ነገም ቢሆን ይህ ፓርቲ በህይወት መኖር ካሻው ራሱን ገምግሞ ከስህተቱ ይማርና ለሶሺያ ቤዙ ያለበትን ሃላፊነት ይወጣ ። የኦሮሞ ፖልቲከኞችን አታካች ድራማ ተመልካች ሆኖ እንዳይቀር ማለት ነው ።

tlel
Member
Posts: 1559
Joined: 28 Dec 2019, 14:24

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by tlel » 21 Jul 2020, 16:08

የሚመስለኝ የነበረው ቀስ በቀስ ወደ ዲሞክራሲ ሀገ መንግስቱን ለሁሉም ያሚሆን ተዘጋጅቶ የሚሄድ ነበር የሚመስለው። ግ፯ ውጪ እያለ ብዙ ሰው ኢትዮዽያን ብሎ ስለሚታገል ጥሩ ነበር ኣሁን በ ሻብያ ማታለልነ በ ዶር ኣብይ ምክን ያት ግ፯ቶች ኣፈረሱት ለምን ምን ማስተማመኛ ኖሯቸው ነው ግ፯ን ያዳከሙት በመጨረሻም ያፈረሱት? ህዋሃት ወደ ቀበሌ ሄደ ተብሎ ፪፯ ኣመት የተሰራው ሴራ ምን እንደሚያመጣ ተገንዝበዋል? ግላዊ መሆን የለበትም ኣብይና ለማ ኢትዮዽያ ስላሉ። እውነታው መሬት ላይና ወደፊቱ በመተንበይ በጭማሪም የውጭ ሃይሎች ኢትዮዽያ ላይ ያላቸው ኣስተያየት ኣላማ እውነት ኣጥንተው ነው የነበረባቸው። ልብዙ ኣመት እራሳቸው የታገሉት ቀላል ኣይደለም። የሚመስለኝ እስካሁን በኤርትራ ነፃውጪ መሪነት ኢሃፓ ስለነበር ከጉያቸው ክኢሳያስ እስካሁን ስር ናቸው።እነሱ የተማመኑት በኢትዮዽያም ህዝብም ኣይደለም በሻብይ ኢሳያስ ተማምነው ነው ለውጥ ኣስመጣላችሗለው በለው ነው። መጀመርያውኑ የኢሃፓ ኣባት ማን ሆነና ነው። ኤርትራው ውስጥ ኢትዮዽያ የሚል ቡድንን ተማምነው ይሆን ቂቂቂቂ። ኣለመብሰል ማለት ይህ ነው።

ከንቱ መሆን ነው ያ ሁሉ ትግል በራሳቸው በዘር ያሰማሩትን የኢትዮዽያን ህዝብ እነ ሻብያ ስር መሾገጥ። ውጪ ታግሎ ነፃ እስከሚወጣ ድረስ በዘረኞች መታገል ተመራጭ ነው። ወይም ኣንድ እግርን ኣገር ውስጥ ሌላውን እግር ውጭ ኣስቀምጦ መታገል ነበረባቸው። ምን ሆነ፣ ዘረኞች ኦነግ ገብተው ኣገሩን ተቆጣጠሩ፣ ዜገኞች ተሸንፈው ተመልካች ሆነዋል። ልክ የህዋሃት ጊዜ እጣ ፋንታ ነው ኢዜማ የደረሰው። በህዋሃት ጊዜ እንዲሁ ተስፋ በማድረግ፣ ለሚዲያ ህዋሃት ይጫወትባቸው ነበር ለፈረንጆቹ ይኸው ዲሞክራሲ ኣገራችን ኣለ ተቃዋሚ ፕርቲዎችን እቋቋማለሁ እያለ፣ እንደነ ይልቃል ኣይነቶቹ፣ እንደ በየነ ጴጥሮስ ኣይነቶቹ፣ ይኸው ስንት ኣመት ሲጠብቁ፣ ምን እነደሚጠብቁም እግዜር ይወቀው ይህን ሁሉ ኣመት። ግን በግላዊነት ጥሩ ህዋሃት በሚፈቅደው ሁኔታ ተቃውመው ትንሽ ድጎማ ይሰጣቸዋል ደህና እንዲኖሩ። ኣለበለዚይ እነዚህ ግለስቦች ምንም ለህዝብ ኣልጠቀሙም ካለ ወሬ በስተቀር። ኢዜማም ያን እጣ ፋንታ ነው የሚደርሰው። ያም ሆነ ይህ፣ በኢትዮዽያ የተደራጀ ውስጥም ውጭም ያስፈልጋል፣ ኣንዱ ሲጠቃ ኣንዱ እንዲተካ። ኢዜማን እኮ መጠበቅ ህዝብ የለበትም በራሱ ተነስቶ መድረግ ያለበትን ማድረግ ኣለበት። ባሁኑ ግዜ ምንም ያሚያስተማምን ነገር የለም።
Last edited by tlel on 21 Jul 2020, 16:43, edited 1 time in total.

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by sun » 21 Jul 2020, 16:11

Bashu wrote:
21 Jul 2020, 08:25
What do you expect from a party headed by Qes Mogesse. Awdma is my favorite political program out of Ethiopia but I worry about the safety of the participants. They are good and fearless. I hope the 7th king won't send them to jail like Eskender by concocting some non existing crime.

There is not even the slightest need or motivation for concocting non existing crimes since even existing and documented repeat crimes are so much abundant
:P

tlel
Member
Posts: 1559
Joined: 28 Dec 2019, 14:24

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by tlel » 21 Jul 2020, 16:20

Genesis wrote:
21 Jul 2020, 04:00
Hello Horus,

I hope you remember me. Thank god you come to your senses
You didn’t like it when I told you ginbot 7 was a sell out and it’s leader Birhanu was a hired spy working for the west. But you didn’t listen. Ginbot 7 the now ezema was an opportunist organization then and still is. Forget the request for intelligence, Birhanu has no principle at all. Who was massacred now in Oromo land, Amara and Gurage mostly. Let alone Ethiopia, can Birhanu speak for his relatives the hard working gurages when they are killed? Not at all. This is what happened when you support charlatans like Birhanu, he disappointed you. Better late than never now you understand. The only solution for all of this is when the Gurage, Amaras and other Ethiopian victims stand up together and defend themselves. I was visiting the Amara region a few months ago, I have seen too many Gurages living and as usual working hard running their business. When I talk to them they are happy and feel at home in Amara provinces. My advice to you is never ever support people like Birhanu as they call him bir amtu Nega. You thought then I was insulting him because he is from Gurage ethnic but you were wrong. He is a different breed very shrewd man who can sell his mom for a dime like he did to Ethiopia. Stay focused one day judgment will be served for people like him. Sorry if I am harsh on you and I am glad you are back to the fold. I know you are wise but sometimes standing for a kin is normal and sometimes it is better to investigate when others stand against your kin. This is how truth guides all of us. You stand for Birhanu before when most people are against him because of his opportunist behavior and now you realize the truth on his stand. That makes you wiser, welcome to the club.
Mr Genesis,

You exaggerate and those who insult dr berhanu based on bogus accusation, yes, it is about ethnic insult when you tallk about money, economy, I know your types, I used to live in diverse sefer in Lideta, I know certain Gonderes come to AA insulting the gurages, it is ethnic insult and I know it. It is one thing to oppose dr berhanu based on his political stance it is another thing when targeting his ethnicity. It is not new. That being said, you also have no evidence whether he works for outside. Your description sounds you are somehow afraid of him, I wonder why. I hope you say that saying sell out fully to Lidetu as well. That being said, my opposition is completely different whereas you have your agenda. I would like to see your types over thowing Tplf instead of barking on small tree. Better yet, I would like to see your bravado freeing Welkait, Afar, Raya and Nile from stangle of Tplf. That is when I see yes, you are better than Berhanu/G7/Ezema. Show us! It is possible maybe something good can come out while remaining patient, yet nothing is guarnateed. My worry is the make and brake comes from Shabia.
Last edited by tlel on 21 Jul 2020, 16:26, edited 1 time in total.

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by sun » 21 Jul 2020, 16:23

Horus wrote:
21 Jul 2020, 15:20
እኔ የኦሮሞ አክራሪ አይደለሁም። እኔ የአማራ አክራሪ አይደለሁም ። እድሜ ልኬን የጎሳ ፖለቲካ የምቃወም የኢትዮጵያዊነት አማኝ ነኝ። በመሆኑም በፖለቲካ እምነቴ ከኢዜማ የሚቀርበኝ ሌላ ፓርቲ የለም ። በጭፍን ጥላቻ፣ ቂምና በቀል ከሚቃጠሉት ፈጣሪ ይጠብቀን ።

እኔ ዛሬ አሁን የማየው የኢዜማ ችግር ድርጅታዊ ፍዘት ወድቆበታል የሚል ነው ። የፖለቲካ ዳይናሚክስ ልክ እንደ ከረምቦላ ጠር ረጴዛ ላይ እንዳሉት ጠጠሮች ነው ። አንዱ ጠጠር ሲመታ ሁሉም ይነቃነቃሉ ። የኢዜማ ጠጠር ሲነቅነቅ አይታይም ። ለምሳሌ፣ የኢዜማ ማህበራዊ መሰረት (ሶሺያል ቤዝ) ከተማዎች፣ በኢትዮጵያዊነት አማኞች፣ ባብዛኛ የደቡብ ክልል ህዝቦች ናቸው ። የኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ ወዘተ ብሄረተኛ ኢዜማን አይወዱም። ያም ስለሆነ የዘር አጥፊዎች ከተሜንና ኢትዮጵያዊያንን ለማውደም ሲደራጁ፣ ሲዘጋጁ ቢያንስ ኢዜማ እንዴት መረጃ እንኳን ለተጠቂዎቹ በማድረስ እንዲጠነቀቁ አላደረገም? ዛዲያ የዚህ ፓርቲ ለዚያ የጄኖሳይድ ሰለባዎች ምናቸው ነው? ነገስ ቢሆን ለምን ይከተሉ? ለምን ይመኑት?

ሃጫሉ በተገደለ ማታ አሸባሪዎች ለሊቱን ሙሉ በመላ ኦሮሞ ሲደራጁና ሲቀናበሩ ኢዜማዎች ለሊቱን ሙሉ በየከተማ ህዝቡን ሲያስጠነቅቁ ቢያደሩ ነበር የዚያ ፓርቲ ፋይዳ በህዝቡ ዘንድ በተግባር ይታይ የነበረው ። ነገም ቢሆን ይህ ፓርቲ በህይወት መኖር ካሻው ራሱን ገምግሞ ከስህተቱ ይማርና ለሶሺያ ቤዙ ያለበትን ሃላፊነት ይወጣ ። የኦሮሞ ፖልቲከኞችን አታካች ድራማ ተመልካች ሆኖ እንዳይቀር ማለት ነው ።
Obbo Horus,

May I say that action speaks louder than words. :P

As a matter of fact you are one of the most racist and divisive vagabond characters on this forum. And the cumulative counter actions may slowly but surely come to reflect on the ordinary innocent common citizens while you are sitting in your protected ivory tower munching your cheesy cheeseburger and passing judgements as your cumulative agitation propaganda puts the poor against the poor citizens. Only fools may believe your cvnning fox deceptions and fake swearing to the effect that you are neither an Oromo nor an Amhara extremist which in fact is utter lie.
:P

Abere
Senior Member
Posts: 14738
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በኦሮሞ የኢትዮጵያዊያን ጄኖሳይድና የኢዜማ ፓርቲ ፋይዳቢስነት

Post by Abere » 21 Jul 2020, 16:43

ምን ዓይነት ተለዋጭ ስም ይሰጠው ይሆን? ዳቦ ተቆርሶ ሳይሆን ደም ፈሶ ከአንዴም ሦስት አራት ጊዜ በጅምላ በኦሮሞ ፅንፈኞች የዘር ዕልቂት ተፈፅሟል ይኸ ኦሮሞ ጄኖሳይድ በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ ይባላል። በእርግጥ በጄኖሳይድ ላይ በየትም ቦታ ሁሉ ይሳተፋል ማለት አይደለ - ፅንፈኛ ልክፍተኞች ያደርጉታል። አታላይ እና አስመሳይ ኦነጎች ደግሞ sexy name የቁልምጫ ስያሜ ይጠቀማሉ እርሱም የእርስ በእርስ ግጭት። እንዴት ብሎ የእርስ በእርስ ግጭት እንዴ ሚሆን እነርሱ ብቻ ያውቃሉ። በሰላም አሳድረኝ ብሎ በሩን ዘግቶ የተኛ ማህበረሰብ፣የስም ዝርዝር ከነሙሉ ትጥቅ በር እየሰበረ ቤት እያቃጠለ በስም እየለዬ የሚገድል ከማን ጋር ነው የተጋጨው?- ከተኛ ሰው ጋር። እኔ ኦነጎች የጅል ብልጥ ሊሆኑ ሲሞክሩ የበለጠ ዝፍጥ መሆናቸውን እንዴሚይስረግጥ እንኳን አያውቁም። ጅሃር ሰው ገድሎ እንዴ ገና አስከሬን ሲሰርቅ - እስክንድር ይታሰራል። ምን አገናኜው - ጅሃር በግ ገዝቶ አርዶ ቆዳ መልስ ስላደረገ እስክንድር አብሮ ማጀብ አለበት? ይህን ያህል ነው የኦነግ እና የኦነግ ቅርንጫፎች የሚያስቡት - በእነርሱ ቤት ህዝብ አያውቅም። አዎን ፣ ኦሮሞ በሌሎች ኢትዮጵያን ላይ ያደረገው ጀኖሳይድ ነው። ህመሙን የደበቀ መድሃኒት አይገኝለትም። ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ቆመናል የሚሉ አብረው ከእስክንድር ጋር አለመቆማቸው እና አደጋው እንዳይደርስ አለመተባበራቸው በእርግጥ ያሳዝናል- ያስተዛዝባል።

Post Reply