Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum





Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 47525
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: "ጄኖሳይድ (GENOCIDE) ተፈፅሟል ሲባል..." [VIDEO]

Post by Halafi Mengedi » 19 Jul 2020, 21:26

If you had the same concern when Amharu went to Beneshangule and killed over 4300 women and kids then we could have understood your concern. Where were then to talk now about 800 people per your words, 4300>>>800 to talk about human right???
Last edited by Halafi Mengedi on 19 Jul 2020, 23:49, edited 1 time in total.



Wedi
Member+
Posts: 8600
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: "ጄኖሳይድ (GENOCIDE) ተፈፅሟል ሲባል..." [VIDEO]

Post by Wedi » 21 Jul 2020, 09:42

Please wait, video is loading...


Wedi
Member+
Posts: 8600
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: "ጄኖሳይድ (GENOCIDE) ተፈፅሟል ሲባል..." [VIDEO]

Post by Wedi » 23 Jul 2020, 14:16

:cry: :cry: :cry:

#Yonas_Abera
ሻሸመኔ
በቀደም ሃጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ከሰዓታት በኋላ ሌሊቱን ሙሉ እና በማግስቱ ሙሉ ቀን የዋለ የተቀናጀ አማራ እና ተዋህዶ አማኞች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከተደረጉባቸው ከተሞች አንዷ እና ግንባር ቀደሟ የሻሸመኔ ከተማ እና ዙሪያዋ ናቸው።

የዛን ቀን አረመኔው፥ ሰው በላው ቄሮ በሻሸመኔ ውስጥ እና በዙሪያው መንደር ለመንደር፥ ቤት ለቤት እየዞረ መታወቂያ እያየ በአማሮችና በጉራጌዎች ላይ ግድያን ጨምሮ የንግድ ቤትና የመኖሪያ ቤቶችን በሚያቃጥልበት በዚያ ሰዓት በሻሸመኔ ከተማ በ 02 ቀበሌ በአቦስቶ ክፍለ ከተማ ከውሀበ ክትፎ ቤት በላይ ከሉሲ አካዳሚ አቦስቶ ቅርንጫፍ በታች እንድ ቤተሰብ በመኖሪያ ግቢያቸው ውስጥ ተቀምጠው ከደጅ የሚያስገመግመውን "ነፍጠኛ ውጣ፣ የሚኒሊክ ሰፋሪ ካገራችን ውጣ፣ አማራ ውጣ!!" የሚል የመንጋው ቄሮ ድምፅ ሰፈሩን ቢያደበላልቀውም "ቢያንስ መንግስት አለ፤ መንግስት ይደርስልናል" ብለው ተስፋ አድርገው ነበር...

ባልዬው አቶ እንዳልካቸው ጥጋቡ (እንዳልክ) ይባላል፤ ባለቤቱ ሜሮን ተስፋዬ (ሚሚ) ትባላለች፤ የከተማው ነባር ኗሪ ናቸው። ሁለት ልጆች አሏቸው። ሸዋ በር አካባቢ የመኪና መለዋወጫ መሸጫ መደብር አላቸው።

ቄሮዎቹ የውጪውን በር ሰብረው ገቡ!! እጅግ መአት ናቸው!! ሁሉም ገጀራ ፣ መጥረቢያ፣ ሜጫና ሚስማር የተመታበት አጣና ተሸክመዋል። ቤተሰቡን አሸበሩት !! ቤቱ ውስጥ ገብተው ክፍል ለክፍል እየዞሩ ያገኙትን እቃ በሙሉ መሰባበር ጀመሩ!! ቴሌቪዥን፣ ሶፋ፣ ፍሪጅ፣ መስታወት፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ ..... የቀራቸው ነገር የለም፥ በያዙት መጥረቢያና ሜንጫ ፈለጡት !! በደቂቃዎች ውስጥ አመታት የተደከመበትን ቤት "ነፍጠኛ ቆማጣ" እያሉ በኦሮምኛ እየዘፈኑ እንዳልነበር አደረጉት፤ የቡና ጀበና አልቀረም!! ቪዲዮ እየቀረፁ፥ ሰልፊ እየተነሱ ቤቱን አወደሙት!! ማንም የደረሰ የለም!! መንግስት አልመጣም!! ጎሮቤት አልመጣም!!

ባልና ልጆች ተደበደቡ!! ህፃናቱ የሚገቡበት ጠፋ!! አፋቸው ደረቀ!! ለማልቀስም ቢሞክሩ እንባቸው ሁሉ ከየት ይምጣ?! ደርቀው ቀሩ!! አባታቸው እንዳልካቸው ላይና እናታቸው ሚሚ ላይ የሚደርሰውን ውክቢያና መገፈታተር በልጅነት አእምሯቸው እንደ ሆሮር ተመለከቱት!!

ሚስትየውን ሚሚን መሬት ላይ ገፍትረው ዘረሯት!! ያ ሁሉ መንጋ እላይዋ ላይ አጎንብሶ ገጀራቸውን፣ ሜጫቸውን፣ ጩቤያቸውንና መጥረቢያቸውን እያወዛወዙ ሆዷ ላይ ስለታቸውን እያፋጩ ዛቱባት "ሆድሽን ተርትረን ፅንሱን አውጥተን በጩቤ እንዘለዝልልሻለን!!" እያሉ አይናቸውን አፍጠው አጉረጠረጡባት !! ሜሮን የዘጠኝ ወር እርጉዝ ናት!! ሶስተኛ ልጅ!!

ባልን ሌላ ክፍል ውስጥ ከልጆቹ ጋር ይዘው በተመሳሳይ ቴረር ለቀቁባቸው!! ልመና አይሰሙም!! የፈጣሪ ስም ሲነሳ ይብስባቸዋል!!

የሚዘርፉትን ዘረፉ!! ከካዝና ውስጥ ብቻ 400 ሺህ ብር ዘርፈው እዛው ተከፋፈሉ!! በፈጣሪ ተአምር የቤተሰቡ ህይወት ተረፈ!! ቄሮዎቹ ወደ ሌላ ቤት፥ ወደ ሌላ ግዳይ ወጥተው ሄዱ። ወደ እነ እንዳልክ ቤት ከመምጣታቸው ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በትንሽ ርቀት ላይ የሚገኘውን "ወሃበ ስጋ መሸጫና ሬስቶራንት" ን እንዳልነበረ አድርገው አውድመውታል።

መንጋው ከሄደ በኋላ እንዳልክና ሚስቱን የሰፈር ሰው መጥቶ ሲያናግራቸው ምን እንደተፈፀመ አእምሯቸው ገና አልተረዳውም ነበር!! ሁሉም ኮንፊውዝድ ሆነዋል!! ከፍተኛ ድንጋጤ!! ልጆቻቸው ያለቅሳሉ!!

ሚሚ ለህክምና ወደ ሃዋሳ ተወሰደች፤ ሆስፒታል ተኝታ ህክምና እየተደረገላት "ገደሉኝ፣ ልጆቼን ሊያርዱብኝ ነው፣ ሆዴን በጩቤ ተርትረው ፅንሴን አውጥተው ሊያርዱብኝ ነው!!" እያለች እየጮኸች ሰነበተች!! ሐኪሞች አዘኑ፣ ነርሶች አለቀሱ.....

ሚሚ ያለፈው እሁድ በእለተ ሰንበት እዚያው ሆስፒታል ውስጥ አረፈች!! አስክሬኗ ሻሸመኔ መጥቶ እጅግ ብዙ የሻሸመኔ ከተማ ህዝብ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ በተገኘበት የበቀደሙ ሰኞ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተቀበረች......
"ፅንሴን፣ ፅንሴን፣ ፅንሴን፣ ሊያርዱኝ ነው፣ ልጆቼን አደራ..." እንዳለች፥ እንቅልፍ ባይኗ ሳይዞር ቀን ከሌሊት እንደባነነች ከነፅንሷ ሞታ ተቀበረች.....
ሜሮን ተስፋዬ ከባለቤቷ ጋር የቤተክርስቲያን ግንባታ ኮሚቴ ውስጥ ተሳትፈው፣ ገንዘብ አዋጥተው ባስገነቡት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ የሻሸመኔ ህዝብ በእንባ ተራጭቶ ቀበራት.....
በብሔራቸው፣ በተዋህዶነታቸው ብቻ ይሄ ሁሉ መዓት ወረደባቸው !!! እግዚዮ !!!

የሚሚን ነብስ ሃያሉ እግዚያብሄር ይማርልን...
ባለቤቷን እንዳልክንና እነዚያን ለነብስ የምትወዳቸውን ህፃናት ልጆቿን እግዚያብሔር ያፅና....
ዘመድ አዝማዷን፣ የሻሸመኔን ህዝብ እግዚአብሔር ያፅና....

PS: መረጃውን ከሻሸመኔ ደውሎ አጣርቶ በስልክ ለረጅም ሰዓታት ተርኮ ላወራኝ ከአመታት በፊት በሻሸመኔ ከተማ ስሰራ የተዋወቅሁት ወዳጄ ስሙ እንዲጠቀስ ስላልፈለገ ስሙን እዚህ አልጠቅስም። ወዳጄ ለእነ እንዳልክና ሚሚ ቤተሰብ የረጅም ጊዜ ቅርበት እንዳለው ነግሮኛል። ተባረክልኝ።

NB: የቤተሰቡ ሃዘን ትንሽ ሰከን ቢል ብዬ እና የሟች ሰልስቷ እስኪወጣ ይሄንን ታሪክና ፎቷቸውን ላለማውጣት ሶስት ቀን መታገስ ነበረብኝ።
ከሻሸመኔ ትንሽ ርቀት ላይ የምትገኘው ኮፈሌ የተባለችው ከተማ ላይ የተፈፀመን አሰቃቂ ግድያ አንድ በዚያ ከተማ ከሚኖር ድሮ የስራ ባልደረባዬ ከነበረ ወዳጄ ዘንድ ደውዬ የሰበሰብኳቸው እጅግ አሰቃቂ ግድያዎችን የሚተርኩ መረጃዎች አሉኝ። ተጨማሪ ማጣራቶች ካደረኩባቸው በኋላ እፖስታቸዋለሁ።
ሰላም።





Wedi
Member+
Posts: 8600
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: "ጄኖሳይድ (GENOCIDE) ተፈፅሟል ሲባል..." [VIDEO]

Post by Wedi » 23 Jul 2020, 14:26

"ጄኖሳይድ (GENOCIDE) ተፈፅሟል ሲባል..."
Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "ጄኖሳይድ (GENOCIDE) ተፈፅሟል ሲባል..." [VIDEO]

Post by Revelations » 23 Jul 2020, 15:40

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "ጄኖሳይድ (GENOCIDE) ተፈፅሟል ሲባል..." [VIDEO]

Post by Revelations » 24 Jul 2020, 07:13

Please wait, video is loading...

Post Reply