Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 14 Jul 2020, 16:22


(1) የጎሳ ፓርቲዎች፣ ብልጽግናን ጨምሮ
(2) የጎሳው ሕገ መንግስት፣ ለዚህ የዎያኔ ኦነግ ወረቀት መኖር የሚታገሉትን ጨምሮ
(3) የጎሳው ፌዴሬሽን ፣ ለዚህ የጄኖሳይድ መሳሪያ መቀጠል የሚታገሉትን ጨምሮ
(4) የጎሳው መንግስት፣ ለዚህ የጎሳ ቀውስ ጥርቃሞ መቀጠል የሚታገሉትን ጨምሮ

ይህ ነው ሃቁ !

120 ሚሊዮን ሕዝብ በዕልፍ አዕላፍ ጋዜጣ፣ ቴሌቪዥን፣ ራዲዮ ፤ ሺ አዕላፍ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች፣ ሃሳቦች፣ ምናምኖች ተከፋፍለው ሺ ግዜ ለሺ አመት ሊፈላሰፉ ሊከራከሩ ሊነታረኩ፣ ሊጋደሉ ይችላሉ። ያ ሁሉ እውነትን የፈሩ፣ እውነትን የማይፈልጉ፣ አውቀው የደነዙ፣ ሳያቁ የደንዙ ሰዎች ታሪካዊ ብክነት ነው ።

የላይኞቹን 4 የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ አገር ፣ መንግስት ገዳይ ጠላቶችህ በስማቸው ጠርቶ እንዴት እንደ ሚወገዱ መፍትሄ የማይሻ ሁሉ ወይ አውቆ የተኛ መልቲ ወይ ሳያውቅ የተኛ ሞኝ ነው ።

የቀረው ዝም ብሎ ቃላት ፈለጣ ነው !
Last edited by Horus on 15 Jul 2020, 01:58, edited 1 time in total.

Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 47525
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች

Post by Halafi Mengedi » 14 Jul 2020, 16:35

Horus wrote:
14 Jul 2020, 16:22

(1) የጎሳ ፓርቲዎች፣ ብልጽግናን ጨምሮ
(2) የጎሳው ሕገ መንግስት፣ ለዚህ የዎያኔ ኦነግ ወረቀት መኖር የሚታገሉትን ጨምሮ -Amhara Amharic language
(3) የጎሳው ፌዴሬሽን ፣ ለዚህ የጄኖሳይድ መሳሪያ መቀጠል የሚታገሉትን ጨምሮ - Amhara culture
(4) የጎሳው መንግስት፣ ለዚህ የጎሳ ቀውስ ጥርቃሞ መቀጠል የሚታገሉትን ጨምሮ - Amhara control others

ይህ ነው ሃቁ !

120 ሚሊዮን ሕዝብ በዕልፍ አዕላፍ ጋዜጣ፣ ቴሌቪዥን፣ ራዲዮ ፤ ሺ አዕላፍ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች፣ ሃሳቦች፣ ምናምኖች ተከፋፍለው ሺ ግዜ ለሺ አመት ሊፈላሰፉ ሊከራከሩ ሊነታረኩ፣ ሊጋደሉ ይችላሉ። ያ ሁሉ እውነትን የፈሩ፣ እውነትን የማይፈልጉ፣ አውቀው የደነዙ፣ ሳያቁ የደንዙ ሰዎች ታሪካዊ ብክነት ነው ።

የላይኞቹን 4 የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ አገር ፣ መንግስት ገዳይ ጠላቶችህ በስማቸው ጠርቶ እንዴት እንደ ሚወገዱ መፍትሄ የማይሻ ሁሉ ወይ አውቆ የተኛ መልቲ ወይ ሳያውቅ የተኛ ሞኝ ነው ።

የቀረው ዝም ብሎ ቃላት ፈለጣ ነው !

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች

Post by Horus » 14 Jul 2020, 16:57

ለምሳሌ የእነዚህ መልቲና ሞኝች ፍጹም ጥፋትና ድክመት እንመልከት፤

ኢትዮጵያ በመሰረቱ ያሏት አራት አላማዎች ናቸው ።

አንድ፣ ኢትዮጵያ አንድነቷ የጸና፣ የተረጋጋችና ጠንካራ አገርና መንግስት ትሁን እንላለን ። የላየኞቹ 4 ጠላቶች እስካሉ ድረስ ይህ አላማ ቅዠት ሆኖ ይቀራል ።

ሁለት፣ ኢትዮጵያ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ ማህበረሰብ ትሁን እንላለን ። የላየኞቹ 4 ጠላቶች እስካሉ ድረስ ይህ አላማ ቅዠት ሆኖ ይቀራል ። የትላንትናው ጄኖሳይድ፣ ግፍና እልቂት ገና ገና ይደጋገማል፤ ሌላ ጊዜ፣ ሌላ ቦታ፣ በሌላ ጎሳ ።

ሶስት፣ የኢትዮጵያዊያን የበለጸጉ፣ የተማሩ፣ ጤነኛ ሕዝብ ይሁኑ እንላለን ። የላየኞቹ 4 ጠላቶች እስካሉ ድረስ ይህ አላማ ቅዠት ሆኖ ይቀራል ። ሰዎችም ወደ ስራ አይሄዱም። የሰሩትም በጎሳ ሽብር የደመሰሳል ፣ ትህምርትም የጎሳ መሃይምነት ፋብሪካ ሆኖ ህዝቡም ልክ እንደ ድሮው በደዌ ሲያልቅ ይኖራል ።

አራት፣ ኢትዮጵያ የፈጠራ፣ የክህሎት፣ የኢኮሎጂ ሚዛን ያለው፣ ባለመልካም ሰነምግባርና መንፈሳዊ ካልቸር ታብቅል እንላለን ። የላየኞቹ 4 ጠላቶች እስካሉ ድረስ ይህ አላማ ቅዠት ሆኖ ይቀራል ። የጎሳ ካልቸር የጥፋት የዲስትራክሽን ካልቸር ነው ። የጎሳ ካልቸር ምን ግዜም ሚዛናዊ የማይሆን፣ የስነ ምግባር ሳይሆን የመንጋ ፣ የመንፈሳዊ የፈሪሃ እግዚአብሄር ካልቸር ሳይሆን የስሜት፣ የግፍ፣ የአረመኔነት የጭለማ ካልቸር ነው ።

tlel
Member
Posts: 1559
Joined: 28 Dec 2019, 14:24

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች

Post by tlel » 14 Jul 2020, 19:07

ሆረስ ስትፈነጥዝ ኣልነበረም። ኣንዳንድ ጊዜ ውጭ ኣገር መኖር ኢትዮዽያውይንን ኣደንዝዞታል። የነሱ እውነታ ኢትዮዽያ ውስጥ እውነታ ይመስላቸዋል ወይም ትተው የሄዱት ኢትዮዽያ።

ባሁኑ እውነታ ከላይ ብቻ የጠቀስከው ኣይደለም ሌሎችም ኣይዲዎሎጃቸውን ያልረሱ ህልም ያላቸው ኣሉ።ኢትዮዽያን ካላፈረሱ የነሱ ኢትዮዽያ ሚኒሊክ ህ፨ስላሴ የሌለበትን ኢትዮዽያ ነው የሚፈልጉት። ኣሁን ያለውም መንግስት ቢሆን። ዋና ይህን መንግስት ከሗላ የሚቆጣጠረው ሻብያ ነው። ሻብያ በውጭ ትዛዝና በኢሃፓ ቀሚስ ዘለል ብላ ገባች። ህዋህት ደሞ ቀስ ብላ በሻብይ ቀሚስ ውስጥ እየኖረ ነፍስ ይዘራል። ችግሩ የነሱን ኢትዮጅያ ታሪክ የሌላት ኢትዮዽያ ነው የሚመጡት፣ በንጉሳችን ቂም በቀል ነው የሚመጡት። ያንን ነው ኢትዮዽያ የሚሉት። ኣዎ ኣንተም ነግረኸናል ኢሃፓ ውስጥ መኖርህ። ኣሁንም ይህ ሶሻሊስት ኮሚኒስት ፅንሰ ሃሳብ መልኩን ቀይሮ ነው የሚመጣው። ብልፅግናስ ፓርቲ ብትል ደሞ፣ ሻብያ በ ብልፅግናም ፓርቲ ሰተት ባላ ኣገሩን ይዛለች። ኣሁን ደሞ ትሪከ ቢስ፣ የሌላ ባዶ የሆነ ቂም በቀል ኣስተዳደር መሆኑን ይቀጥላል።

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች

Post by Horus » 14 Jul 2020, 21:28

tlel,

እኔ ስለ አይዲኦሎጂ ወይም ስለ ታሪክ አይደለም የምተቸው፤ ስለ አሁን ያለው እውነታና ሁኔታ ነው ። ይህ ከኛ ወጭ ያለው ፍጥረት የኛ ሪያሊቲ አይደለም ። የሰው ልጅ ኮንስትራክቲቪስት ነው ፤ እኛ የራሳችንን ሪያሊቲ እኛው ራስችን ነን የምንፈጥረው ። ዛሬ ያለው የኛ ሪያሊቲ ወይ ሃይለ ስላሴ ወይ ደርግ የሰራው ሪያሊት አይደለም። እነኢአፓን ከዚህ እናውጣቸው ፤ እነሱ አቁመቅት የሄዱ ሪያሊቲ የለም፣ እናም እነሱን መክሰስ ሽሽት ነው።

የጎሳ አይዲኦሎጂ ለ20 አመት ጫካ ወስጥ ተሰርቶ ለ30 አመት በተግባር ላይ ወሎ ወጤቱን በግልጽ እያየን ነው ። ያ ነው አሁን ያለው ጭብት የሚታይ። የሚሸተት፣ የሚዳሰስ ኢምፒሪካል ሪያሊቲ ። በአንድ ቃል በጎሳ አይዲኦሎጂ ና ቲኦሪ አማካይነት ኮንስትራክተድ የሆነው ሰርዓት ከሽፏል፣ አይሰራም፣ ሽባ ነው፣ ዲፌክቲቭ ነው።

ሰዎች በአንድ በተወሰነ ቦታ፣ ግዜና የግንዛቤ (ኢንተለጀንስ) ልክ የሰሩት ሪያሊቲ ሲከሽፍ ያንን ትተው ሌላ የሻለ ሞዴል የትሻለ ዲዛይን የተሻለ ካርታ መሞከር ግድ ይላቸዋል፣ አለዚያ ስለሚጠፉ፣ ስለሚራቡ፣ ስለሚሞቱ ወዘተ ።

ዛሬ የጎሳ ፓርቲ ሲስተም ውድቅ ነው፣ አይሰራ፣ የጎሳ ኮንስቲቱዩሽን ዋጋ የለሽ ውድቅ ሃሳብ ነው ። በዚያ ላይ የቆመው ፌዴሬሽን ቀውስ ነው ። ማስተዳሪያ ሳይሆን ህዝቦችን ማጋደያ፣ ኢኮኖሚ ማውደሚያ የግጭትና ጦርነት መፈልፈያ ቀፎ ነው ። ዛሬ መንግስት ሆነው ሌት ተቀን መጨበጫ የሌለው ቀውስ ውስጥ ሚባክኑት እነአቢይ መንግስት አይደሉም፣ እሳት አደጋ ተከላካዮች ናቸው።

ይህን የመረረ ሪያሊቲ አንድም ሰው አንስቶ አያወራውም ፣ እንደ ሰጎን ሁሉም አንገቱን አሸዋ ውስጥ ደብቆ ያሰመስላል ። ዛሬ ሻሸሜን የሆነ አለምንም ጥርጥር በሌላ ግዜ ይደገማል። ያን የሚያመጣው ሲስተሙ ነው ፣ የጎሳ ሲስተም ስራው ያ ስለሆነ ።

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች

Post by Horus » 15 Jul 2020, 00:38


Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች

Post by Horus » 15 Jul 2020, 00:50

አናርኪዝም ማለት መንግስት አልባነት ማለት ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች

Post by Horus » 15 Jul 2020, 01:12


Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 15 Jul 2020, 02:03

ኤርሚያስ ለገሰ አንደበተ እርቱዕ፣ እውነት ተናጋሪ፣ የተናገረው ጠብ የማይል የኢትዮጵያዊነት ንቅናቄ መሪ !!! ነገር ግን አንድ ነገር መገንዘብ አለበት ። የኢትዮጵያዊነት ንቅናቄ አንገቱን ከፍ ባደረገ ቁጥር ያማራ አክራሪዎች እኛ ብቻ ካልመራነው እያሉ በተደጋጋሚ ግዜ ትግሉን ማዳከማቸውን አውጥቶ መገሰጽ አለበት ።

tlel
Member
Posts: 1559
Joined: 28 Dec 2019, 14:24

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች

Post by tlel » 15 Jul 2020, 02:24

በኦሮምያ ባዕድ ነገር የኦሮሞ ማህበረሰብ ተዋውቋል። የኦሮሞ ወጣት ማንነታቸውና ፍላጎታቸው ባልታወቀ ፖለቲከኞች ባዕድ በሆነ ነገር የኦሮሞ ወጣትን ማንነቱን እያወናበዱት ነው።

ገና የዛሬ ሁለት ኣመት፣ ከውንድሞቹ ጋር ከፋኖ ከዘርማ ጋር ኣብሮ ህዋሃትን ኣስወግዶ፣ ዛሬ ከውንድሞቹ ከፋኖ ዘርማ ጋር እንዲለያይ ሲደረግ ይህ ለውጥ ማለት ሰላምነት ሳይሆን መከፋፈልን ነው ያመጣው። ኣሁንም ምስጢራዊ የሆነ ነገር እየተሰራ ነው።ሆን ተብሎ በዚህ መንግስት ተደርጏል። የዚህ መንግስት ኣመጣጡም ከህዋሃት ተፎካክሮ ህዋሃትን የመጣል እንጂ ኣላማው በዘር ያልሆነ ሚዛናዊ ኣገዛዝን ሊያመጣ ኣልቻለም። ህዝብን የበለጠ እየከፋፈለ ነው።ለማንኛውም የሆነ ሃይል እንዳለ ነው የሚያስረዳው ኣክራሪዎችንና ከፋፋዮችን ኣገር ውስጥ እንዲገቡ ማስደረግ።

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 15 Jul 2020, 02:52

tlel

እኔ አንተ ክምን ጎሳ እንደ ሆንክ፣ የፖለቲካ መለካከትህ ምን እንደ ሆነ አላቅም ። ስለዚህ ዝም ብዬ በአክብሮት መልስ እሰጥሃለሁ ። ስለ ቄሮም ሆነ ስለ ኦሮሞ ፖለቲከኞች አላማ ያልከው ስህተት ነው። ያልከው ነገር ስለ ኦሮሞ የ50 አመት እቮሉሽን ወይ አውቀህ ወይ ሳታቅ የምትስተው ነገር አለ ። የኦሮሞ የማንነትና ሌላው አጀንዳ በጣም ውስብስብ በጣም ሽፍንፍን እንደ አሜባ የሚንሸራተት ሃሳብ ነው። እኔ ኦነግ ሲፈጠር የነበርኩ ሰው ነኝ፣ በጣም፣ በጣም አድርጌ አቃቸዋለሁ ።

ቄሮ ለኢትዮጵያ ነጻነትና እድገት ታገለ ከሚለው የላቀ ተረት ባለም ላይ ሊኖር አይችልም ። ቄሮ ትላንትም ዛሬም ወደፊትም ለኦሮሞ ሄጂሞኒ ያ ካልሆነ ለፎሌ ለወረራ ወደ ፊትም የሚሰለፍ ሃይል ነው። ዛሬ የተለያዩት የኦሮሞ ልሂቃን ኢትዮጵያን እንዴት እንቆጣጥር በሚለው እስትራተጂና ታክቲክ ላይ ይለያያሉ። ግን በአላማ ሁሉም አንድ ናቸው።

አንድም የኦሮሞ ንቅናቄ፣ አንድም የኦሮሞ ድርጅት በኢትዮጵያዊነት ወይም ኢትዮጵያን ለማግነን የሚሰራ የኦሮሞ ድርጅት የለም ። ጥቀስና ርታኝ !!!


EthioRedSea
Member
Posts: 4089
Joined: 31 Aug 2019, 11:55

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by EthioRedSea » 15 Jul 2020, 10:11

Horus wrote:
14 Jul 2020, 16:22

(1) የጎሳ ፓርቲዎች፣ ብልጽግናን ጨምሮ
(2) የጎሳው ሕገ መንግስት፣ ለዚህ የዎያኔ ኦነግ ወረቀት መኖር የሚታገሉትን ጨምሮ
(3) የጎሳው ፌዴሬሽን ፣ ለዚህ የጄኖሳይድ መሳሪያ መቀጠል የሚታገሉትን ጨምሮ
(4) የጎሳው መንግስት፣ ለዚህ የጎሳ ቀውስ ጥርቃሞ መቀጠል የሚታገሉትን ጨምሮ

ይህ ነው ሃቁ !

120 ሚሊዮን ሕዝብ በዕልፍ አዕላፍ ጋዜጣ፣ ቴሌቪዥን፣ ራዲዮ ፤ ሺ አዕላፍ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች፣ ሃሳቦች፣ ምናምኖች ተከፋፍለው ሺ ግዜ ለሺ አመት ሊፈላሰፉ ሊከራከሩ ሊነታረኩ፣ ሊጋደሉ ይችላሉ። ያ ሁሉ እውነትን የፈሩ፣ እውነትን የማይፈልጉ፣ አውቀው የደነዙ፣ ሳያቁ የደንዙ ሰዎች ታሪካዊ ብክነት ነው ።

የላይኞቹን 4 የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ አገር ፣ መንግስት ገዳይ ጠላቶችህ በስማቸው ጠርቶ እንዴት እንደ ሚወገዱ መፍትሄ የማይሻ ሁሉ ወይ አውቆ የተኛ መልቲ ወይ ሳያውቅ የተኛ ሞኝ ነው ።

የቀረው ዝም ብሎ ቃላት ፈለጣ ነው !
That is right. I support such plans. Though I sometimes side with the ethnic groups who are fighting for equality. We need to democratize Ethiopia without the formation of ethnic federalism or ethnic based political partys.

Horus! Yow were supporting Guraghe domination of Ethiopia. There should not be domination of any ethnic group. We need to promote equal rights to all citizens. Amharic should not be the only working language. We need to add Tigrigna and Geez. Oromo cannot be a working language as it has no base in Ethiopia's ancient history. The Oromo should choose between Tigrigna and Amharic or English, which will be the working language for all.

We need to disband all Ethnic group based organisation. There should be only about 4 political partys in the whole country.

It is quite disturbing that some muslims are abusing the system. Forming religious based banks should not be allowed. Names of banks should be neutral. We need to mdel the country according to western democracy: UK, German, France, USA, china, Russia etc

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 15 Jul 2020, 14:01

ethioredsea

ዎያኔ ከወደቀ በኋልም ቢሆን መጨረሻ ላይ የጎሳ ፖለቲካን አስከፊነት ለማየት መቻልህ ጥሩ ነው ። እኔ ይህን የዘር ፖለቲካ ለ45 አመት ተቃውሜዋልሁ ። ታውቀኛለህ ። ጉራጌ ኢትዮጵያን ዶሚኔት የሚያደግ ብዛትምም አላማም የለውም ያልኩት ጉራጌ በባህሉ። በሳይኮሎጂው፣ በኢትዮጵያ ወዳድነቱ በስራ ስነ ምግባሩ የኢትዮጵያ ምሳሌ ነው ፣ ነው ያልኩት ። ይህን ደሞ አሁንም እደግመዋለሁ ።

አሁን ወደ ዋናው ነገር እንመለስ ። ጎሳ የሚለው ጽንሰ ነገር፣ ዘር የሚለው ጽንሰ ነገር የካልቸር ጽንስ ነው፣ በቃ ። በጎሳ ህሳቤ ፖለቲካ፣ መንግስት፣ ሕግ፣ ኢኮኖሚ፣ ቴክኖሎጂ ወይ ሳይንስ ወይ ምንም አይነት ስልጣኔ ማቆም አይችልም ። እንዲያም ልክ ዛሬ ኦሮሚያ እንደሚታየው አብሪካ፣ እርሻ፣ ኢንዱስትሪ፣ ህንጽ፣ መክና። ቴክኖሎጂ ማንኛውም የስልጣኔ ውጤት በአንድ ቀን ማንደድ የሚችል የአረመነኔ፣ የባርባሪያን ህሳቤ ነው የጎሳ ስርዐት ።

ይህ ማለት ደሞ ኦሮሞ ብቻ አይደለም፣ ሁሉም የጎሳ ሰርአቶች ፍጻሜአቸው ወድመት ነው። ይህ ብቻ አይደለም ፤

ለምሳሌ የኦሮሞ ክልል ፕሪዚዳንት እስከ ዛሬ ኦሮሞን በእግሩ አልነካም፤ ምክኛቱም እዚያ መንግስት ስለሌለ ሴኩሪቲ ስለሌለ ። በአንድ ቃል እሱ ኦሮሞን እየገዛ አይደለም። ግዛት የሌለው ፕሬዚዳንት ነው። ያ የጎሳ አይዲኦሎጂ ውጤት ነው ። ይህ ደሞ ለሕወሃትም። አማራም ሌላም ተመሳሳይ ነው።

ገና መቀሌ ውስት ሽብር እና እሳት ይነሳል። ይህ የጎሳ ሲስተም ሕግ ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 15 Jul 2020, 16:24

ሃብታሙን ስሙት ?

ኢትዮጵያዊያን እንደ ገና ሰልፍ መውጣት ጀምረናል? ለምን? በአንድ ቃል ከዛሬ ጀምሮ የትግላችን አላማ የኢትዮጵያ አጀንዳ መሆን አለበት።

አጀንዳውም ይህ ነው ።

ኢትዮጵያ በመሰረቱ ያሏት አራት አላማዎች ናቸው ።

አንድ፣ ኢትዮጵያ አንድነቷ የጸና፣ የተረጋጋችና ጠንካራ አገርና መንግስት ትሁን እንላለን ።

ሁለት፣ ኢትዮጵያ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ ማህበረሰብ ትሁን እንላለን ።

ሶስት፣ የኢትዮጵያዊያን የበለጸጉ፣ የተማሩ፣ ጤነኛ ሕዝብ ይሁኑ እንላለን ።

አራት፣ ኢትዮጵያ የፈጠራ፣ የክህሎት፣ የኢኮሎጂ ሚዛን ያለው፣ ባለመልካም ሰነምግባርና መንፈሳዊ ካልቸር ታብቅል እንላለን ።


Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 16 Jul 2020, 01:15

የኢትዮጵያ ቀውስ መነሾ፡

(ይህ ሃተታ በ9/2/1995 ለER መጽሄት ልልከው ከጻፍኩት በኋላ ተረስቶ ዛሬ እንዳጋጣሚ ሳነበው አሁንም ያለውን ሁኔታ ስለሚያሳይ ምንም ሳልቀይር እነሆ ከ24 አመታት በኋላ። ሃተታው ረጅም ስለሆነ ለመደምደምያው ታገሱ ። እዚህ ፎረም ላይ ልክ የዛሬ አመት ለጥፌው ነበር ። ዛሬ ደግሞ ከታች ያያዝኩትን ያኢትዮ360 ውይይት ከሰማሁ በኋላ እንሆ ከ25 አመት በሁላ)

የጽሁፉ መቋጫ የቀድሞ ኢትዮጵያም የቀድሞ ጎሳዎችም ወደ ዘመናዊነት በሚደረገው አድካሚ ጉዞ ይለወጣሉ፤ አሁን የምናየው ሁሉ ግዜያዊ ነው። በዚህ የሽግግር ውጥንቅጥ መሪና አሸናፊዎቹ እጅግ አዲስና ያልታየ መፍትሄ ማመንጨት የሚችሉት ፈላስፎች፣ ነዳፊዎች፣ ሃሳቢዎችና የኪነት ፈጣሪዎች ናቸው ።

ኢትዮጵያ መሰረታዊ የውድመትና የድቀት አደጋ አለባት እላለሁ ። ይህን ስል ምን ማለቴ ነው?

አንደኛ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአካል አይወድሙም፤ አይጠፉም። እንዲያውም በሚቀጥሉት ሰላሳ አምስት አመታት ወስጥ የሕዝባችን ቁጥር ከ55 ሚሊዮን ወደ 140 ሚሊዮን ያድጋል። የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ ስርዓታት ተሽካሚዎችና አንቀሳቃሾች ይህ ሕዝብ ነው። ሆኖም አሁን ካለው ሕዝብ የተወሰኑት በሽግግሩ ወቅት ይጠፋሉ። ሽግግር ስል ግዙፉን ወደ ዘመናዊነት የሚደረገው አስቸጋሪና ዝብርቅርቅ ሽግግር ማለቴ ነው ። በሽሽግሩ የሚወድሙት ግን ከፊሉ ብቻ ናቸው።

በኢትዮጵያ ካሉት ብዙ ጎሳዎች አኳያ ወደ ዘመናዊነት በሚደረገው ሽግግር ወቅት የሚወድሙት ማህበረ ሰቦች የተኞቹ ናቸው? ከወድመት የሚድኑት ከመጥፋት የሚተርፉት በምን በምን ምክንያቶች ነው? በመሰረለቱ ከውድመት የሚድኑት ሕዝብ ሆኑ ጎሳዎች አሁን ከሚያምኑበት የጥፋትና የቀውስ ባህል እየከዱ ወደ አዲስ አስተሳሰብና ባህል የሚዞሩት ናችደው። ይህን መሰል እውቀትና ችሎታ የሌላቸው ግለሰቦች፣ ጎሳዎችና ቡድኖች ወዳሚዎች ናቸው። ስለዚህ የዘመኑ ቀውስና ብሶት የሚጠይቀውን ለውጥ ለማድረግ ችሎታ ያላቸው ክፍሎች ግዙፉን ሽግግር ያልፋሉ፤ ያልቻሉት ይወድማሉ። አሁን ያለው ሞራሉ የላሸቀው ሰው አዲስ ነገር አይፈጥርም።

ሁለተኛ፣ ስለ ኢትዮጵያ ወድመት በሚጠቀስበት ወቅት ሌላው ግልጽ ነገር ኢትዮጵያዊያን እስከ ዛሬ የፈጠሯቸው ቁሳዊ ባህላት፣ ቁሳዊ ግንባታዎች ሁሉ አይደመሰሱም። የፈጠሩት ሳይንስ ሆነ ቴክኒክ ሁሉ አይወድምም። ሆኖም ከቁሳዊ ባህላችን፣ ከልማት ውጤቶች ከፊሉ በሽግግሩ ጦርነት፣ አብዮት፣ አናርኪና ሁከት ይወድማሉ። ከውድመት የሚድኑት ቁሳዊ (ለምሳሌ ቤቶች፣ መንገዶች፣ መኪናዎች) ከእሴታዊ ምንነት ጋር ብዙም የተቋለፉ አይደሉም። ለምሳሌ ለዘውድ አገዛዝ የታነጸው ቤተ መንግስት ለኮሚኒስት ፓርቲና ለወያኔ መሰብሰቢያ ያገለግላል። ፈንጂ ለጥፋትም ለማእድንም ያገለግላል። ስለዚህ ቀደም ሲል ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ የተፈጠሩት ቁሳዊ ባህላት ሆነ ተቋማት አሁን ለጎሳ ስርዓት ግንባታ መገልገያ ተደርገዋል።
ምንነትና እሴት እና የነሱ ተሸካሚ የሆነው ቁሳዊ መሳሪያ ያላቸው አንድነት እጅግ የላላ ነው። ቴሌቪዝን ሃይማኖትም ሌብነትም የሰበክበታል። እነዚህ ቁሳዊ መሳሪያዎች የአዲሱ ስርወ እሴት አገልጋይ ይሆናሉ።

ሶስተኛ፣ ከዚህ ቀደም በፌውዳሉ ስርዓት ስር ተዋቅሮ የነበረው የነበረው የመላ ኢትዮጵያ ስርወ እሴት መዝቀጥና መፍረስ የሁሉም ባህልና ማህበራዊነት መፍረስ ወይም መበታተን አይደለም። ቀድሞ ያልተዋሃደ ነገር ሊበተን አይችልም። ስለዚህ የዘመኑ የጎሳ ስርወ እሴት ድሮ የነበረውን የጎሳዎች ልዩነት አጽድቋል፣ አጠናክሯል፤ እስከ ተወሰነ ድረስ እያደጉ የነበሩ የመላ ኢትዮጵያ እሴቶችን ሰባብሯል። ሆኖም ተጽዕኖው የተወሰነ እንጂ ጠቅላላ መበታተንና ዝቅጠት ሊሆን አይችልም። ጠበብ ብሎ በሴምና ባማራው ዙሪያ ያደገው ባህል ስሜታዊ ሆነ ሳይንሳዊ እስከ ተወሰነ ድረስ ተለውጦ ስፋት እያገኘ ነው። ግን ይህ ምን አይነት ባህል ነው?

አራተኛ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እሴትና ምንነት ወይም ማንነት በጎሳ እሴትና ማንነት እየተተካ ሲሄድ ወይም መሄድ ማህበረሰባዊና ባህላዊ ፈጠራን ማለትም ስልጣኔን ቀጥ አቁሟል፤ ያቆማልም። የተፈጥሮ ስይንቲስቶች እና ቁሳዊ ፈጣሪዎች የሚሰሩለት አገራዊ ፋይዳ ሆነ ትርጉም ከጠፋ ወዲህ ስራ አቁመዋል። በመንቀሳቀስ ላይ ያለው የጎሳ ባህል፣ ተረት፣ ታሪክና አፈታሪክ የሚቆፍረው ጠባቡ የሶሻል ሳይንስ ምሁር ብቻ ነው። በአንጻሩም ለኢትዮጵያዊነት የሚሟገተው የሶሻል ሳይንስ ምሁር ፖለቲካዊና ታሪካዊ ክርክር ያደርጋል። ክዚህ ውጭ የጎሳ ሳይንስ ወይም ቴክኖሎጂ የሚባል ነገር ስለሌለ ሳይንሳዊ ፈጠራ ከእሴትና ምንነት እጦት የተነሳ ወድቋል። ይህ መቼም ትልቁ ቀውስ ነው። ይህም ሆኖ በተፈጥሮ ሳይንስ ዙሪያ እያቆጠቆጠ የነበረው ምሁር ሲበተን ጠንካራ ብሄራዊ ምሁራን በሃይማኖት፣ በፍልስፍና በስነ ፖለቲካ ዙሪያ ተነስተው ብሄራዊ ፈጠራ ሊያደርጉ አልቻሉም።

ይህ ሁለገብ ዝቅጠት እጅግ አሳሳቢው ቀውስ ነው። በኢትዮጵያ ወስጥ ለብዙ ግዜ ብሄራዊ ሳይንሳዊ የፈጠራ እንቅስቃሴ ሊኖር አይችልም፤ አገራዊ እሴትና አለኝታ ጠፍቷልና። በማህበራዊ ፍልስፍና መስክም ተመሳሳይ ቀጥ የማለት አደጋ አለ ። በአጠቃላይ አገራዊ የሆኑት የፍልስፍና መሰረቶች ማለትም የግለሰቡ ሰብአዊነት፣ እና መደባዊ ህብርዊነት በዘር ጽንስ ስለተሻሩ ጎሳ በተሰኘው የቡድን ጽንስ ዙሪያ አንድም የረባ ፍልስፍና ሊነሳ አይችልም ። የጎሳ ጽንስ ቅድመ ፍልስፍና ስለሆነ፣ ቅድመ ሰብአዊነት ስለሆነ። ስለሆነም ሶሺያ ፊሎሶፊም ከፍተኛ ዝቅጠት ወስጥ ይግኛል። ሌላው ቀርቶ መንፈሳዊ ፍልስፍና እንኳን ሊያቆጠቁጥ አልቻለም።

አምስተኛ፣ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሳይንስ ቀውስ አለ። የጎሳ ጽንሰ ሃሳብም ሆነ የጎሳ እንቅስቃሴ ማህበራዊ ወይም ሶሺያል ሳይንስ የለውም። ይህ አዲስ ተብዬ ፖለቲካም በጭለማ ውስጥ የሚደረግ ሙከራ ነው። ጠባብ የፖለቲካ መሃንዲሶች የሚያጨማልቁት ሙከራ ነው። ብሄራዊ ሶሺያል ሳይንሱ ስረው መሰረቱን በደንብ ለውጦና ግልጽ አድርጎ የፈጠራ ንቅናቄ ማድረግ ተስኖት ቆሟል። የሶሺያ ሳይንስ ቀውሱ የጀመረው በሃይለ ስላሴ ዘመን ነበር። የዘውድ አገዛዝን ዘመናዊ ለማድረግና ለምዕራብ ተቀባይነት ለመስጠት ሲሞከር የተፈጠረ ውዥንብር ነበር። ስለዚህ በዘውድ አስተሳሰብና በሊብራል ዴሞክራሲ መካከል የተነሳው ቀውስና ውዥንብር እልባት ሳያገኝ የአብዮቱ ዘመን መጥቶ ሁለቱም (የመለኮታዊም ሆነ የሕዝባዊ ሃይል አስተሳሰብ) ከመድረክ አስወገዳቸው።

ሶሺያሊዝም እየተባለ ይታወቅ የነበረው የተሳሳተ ወታደራዊ አገዛዝ በአንድ ቃል የፖለቲካ ሃተታ ወይም ትንተና ከህብረተሰቡ እንዲጠፋ አደረገ። ወታደራዊ የቡድን አገዛዝ ከሶሻሊዝም ጋር እንደ ተምታታ ሁሉ ዛሬ ደግሞ የጎሳ አስተሳሰብና ርዕዮት ከዴሞክራሲ ጋር እየተምታታ ቀርቧል። ስለሆነም በጎሳ አስተሳሰብ መግነን ሳቢያ አዲሱ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ትልቅ ቀውስ እንዲወድቅ ተደርጓል። ዘመናዊ ዴሞክራሲና ጎሰኝነት እስካልተለያዩና ዴሞክራሲ ከጎሰኘነት እስካልጸዳ ድረስ በኢትዮጵያ የሶሺያል ሳይንስ ቀውስ አያበቃም።

ሌላው ትልቁ የኢትዮጵያ ቀውስ የስነ ጥበብ ውድቀት ነው። እነሱም ስዕል፣ ጠረባ፣ ሙዚቃ፣ ስነጽሁፍ፣ ውዝዋዜ፣ ቲያትር፣ ሲኒማ፣ ዚቅ፣ አርኪቴክቸር ወዘተ ። ቀደም ሲል የነበሩት ጠቢባን እያለቁ ነው። አዲስ የሚፈጠሩት አብዛኞቹ ዋጋ ቢስ ናቸው፤ ጥልቀትና ንቃት የላቸውም። ብሄራዊ ራዕይና ስረው እሴት ላይ የተመሰረተ ፈጠራ ሳይሆን ከዚህም ከዚያ የተለቃቀመ፣ ከምዕራብ የተገለበተ የተቀዳ ስራ ነው ።

የቀረው ከጎሳዎች ግላዊ ባህል፣ ሙዚቃ ወዘተ ጋር የተያያዘ ነው ። የኪነትና የስነት መስክ በውራጅ ፈጠራ ተጥለቅልቋል ። እዚህ ላይ ተደጋግሞ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ኪነትና የኢትዮጵያ ስነ ጥበብ የሚባል ነገር አለ ወይ የሚለው ነው? ወይስ የ90 ብሄረ ሰቦች ስብስብ ጥርቅም ስነ ጥበብ? ይህ ያልተመለሰውና አወዛጋቢው ጥያቄ ነው።

ሌላው ትልቁ የኢትዮጵያ ቀውስ ሕግና ስነምግባር (ኤቲክስ) የተመለከተ ነው። በአንደኛ ደረጃ ዘመናዊ ወይም በተዋሃደ መልኩ የኢትዮጵያን ሕግና ስነምግባር የምንላቸው በምዕራቡ ግፊት የገባው እጅግ አለማዊና አምባገነን ባህል ሳቢያ ለብዙ አመታት የተከሰተ ኢሕጋዊነት ወይም የሕገወጥነት ክስተት አለ። ይህ የሕገወጥነትና የስነ ምግባር (ሞራል) ብልሹነት በአገሪቱ ለዴሞክራሲ አለመኖር ብቻ ሳይሆን በታሪክ ውስጥ በብሄረሰቦች መካከል የነበረውን ግንኙነት የመነጨም ነው። በተለይ ስነምግባር በተመለከተ የ90ቹ ጎሳዎች ግላዊ ኤቲክስ አለመዋሃዱና አንድ ብሄራዊ የኢትዮጵያ ስነምግባር አለመፈጠሩን ያመለክታል።

በዚህ መስክ ያለው ቀውስ እጅግ አሳሳቢ የሚሆነው የተለያዩ የብሄረ ሰብ ሴራዎችና ስነምግባራት መኖራቸው ብቻ አይደለም። የሕግ አለመከበር፣ የሃይል መግነን፣ በስልጣን መባለግና ፍርደገምድልነት፣ እኔባይነት ሌሎችን ማፈን በሃይል ሌሎችህን ማንበርከክ የዛሬን ጥቅም ባይነት ብቻ (ሄደኒዝም) እና አፍራሽነት የደምሳሽነት አመለካከት (ኒሂሊዝም) የመሳሰሉት የሁሉንም ብሄረሰብ አኗኗር ስለሚያቃውሱ አደገኛነታቸው ህብረባህል ከመሆን የባሰ ነው።

ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ቀውሶችን እናስተውላለን። አንደኛው የመላ ኢትዮጵያ አንድ ወጥ ስርዓት፣ እሴት፣ ባህል፣ ለማስተባበር ለማዋሃድ የሚሞክረው አዝማሚያ ነው። ይህ አዝማሚያ የተበተነና አቅጣጫ የለሽ መሆኑ ነው። ሁለትኛው የእያንዳንዱ ጎሳ እሴትና ባህል ቁንጽል ብቸኛ መሆንና በሌሎች ተቀባይነትን ማጣት እንዲሁም በዘመናዊነት መመታቱ ነው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ እሴት የላትም፤ ያለውም በምዕራብ ዘመናዊነት ተቃውሷል። የጎሳው እሴት አንዱም ለብሄራዊነት ብቃት ማጣቱ ብቻ ሳይሆን እሱም በዘመናዊነት ተቃውሷል። በሶስተኛ ድረጃ በኢትዮጵያ እሴትና (ካለ ማለት ነው) በጎሳው እሴት መሃል ያልተቋለጠ ግጭት ይካሄዳል። እነዚህ ሶስት ክስተቶች ሕግን፣ ስነምግባርን፣ ዴሞክራሲን፣ አስተዳደርን፣ አደረጃጀትን፣ ወዘተ ሁሉ ያካልላሉ። ለዚህ ደግሞ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ የለንም።

በሌላ ደረጃ እየተከሰተ ያለ መሰረታዊ ችግር አለ። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ ብሔራዊ እሴትና ባህል አለመፍጠሯ፣ በ90 ብሄረሰብ ባህሎችና በብዙ ሃይማኖቶች መከፋፈሏ ብቻ ሳይበቃ በተለይ ከምዕራቡ ዘመናዊነት ጋር የተቃመሱት የጎሳ ባህላትም የስሜታዊነት ጥራዝነጠቅነት ብልሽት ደርሶባቸዋል። ያጭር ግዜ ድል፣ ደስታ፣ ተንኮልና አፍራሽነት በሁሉም ባህላት ዘንድ እሴቶች ሆነዋል። ስለዚህ ስርወ እሴት ያጣው የኢትዮጵያዊነት ባህል (ካልቸር) ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ጎሳም ተመሳሳይ ቀውስ አጋጥሞታል። ከዚህ ሁለገብ የሆነ ቀውስ ለመውጣት ሰዎች ግዙፍ የሆኑ የእምነት፣ የአንድነት፣ የትብብር፣ የፍቅር እሴቶችን ከመሻት ይልቅ በግላዊና ቡድናዊ የታሪክና የህላዌ ምርምር ወይም ቁፋሮ ላይ ስለተጠመዱ እጅግ ቅጥ ያጣ የአመለካከት ጥበትና ውዥንብር በህብረተሰቡ ሰፍኗል። ስለሆነም ኢትዮጵያ የረዥም ግዜና መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችላት ብሩህ አመለካከት፣ ብሩህ ራዕይ የላትም፤ በምሁሮችዋ ማለት ነው።

ስለዚህ ግዙፉ የኢትዮጵያ ሽግግር ከየት ወዴት የሚሄድ ሽግግር ነው? የሚለው በፍጹም ግልጽ አይደለም። ከአንድነት ወደ መበተን ወይስ ከመበተን ወደ አንድነት? ወደ አለማዊነት ወይስ ወደ መንፈሳዊነት? ከእምነት ወደ ሳይንስ ወይስ ከሳይንስ ወደ እምነት? ከጎሳዊነት ወደ ዜግነት ወይስ ወደ ባሰ ዘረኝነት? ከኢሰባዊነት ወደ ሰባዊነት ወይስ ሌላ?

ይህን ግዙፍ ሽግግር ለምፍጠር በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፊሎሶፊ፣ በሶሺያል ሳይንስ በተለይ በፕለቲካ ሳይንስ፣ በስነ ጥበብ፣ በሕግና ስነምግባር መስኮች ሊመሩ የሚችሉ የሃይማኖት፣ የሳይንስ፣ የስነት፣ የስነ ህብረተሰብ መሪዎች ኢትዮጵያ የሏትም። መፈጠር ያለበትና ሊፈጠር የሚታሰበው እምነትና ንድፈ ሃሳብ መብላላት አልጀመረም፤ ሲብላላ አይታይም።

ከላይ የቀረበው ሃተታ የሚያመለክተው ጉዳይ ቀደም ሲል በትንሹም ቢሆን በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትና በአማርኛ ቋንቋ ዙሪያ ተገንብቶ የነበረው የባህልና እሴት መለኪያ (ደረጃው) እጅግ መዝቀጡን ነው። የብሄረሰቦች ፉክክር ከሰፈነ ወዲህ አገሪቱ ባህላዊና እሴታዊ ህብረተሰብ መሆኗ ጠፍቶ የምዕራብና የምስራቅ ሸቀጣ ሸቀጣዊ ባህል በገፍ የሚራገፍባት ገበያ ሆናለች። በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እንጂ አገር መሪዎች የሉም። የዜጋዎች ደህንነት ባገር አቀፍ ድህነት ማለትም የእምነት ድህነት፣ የፍልስፍና ድህነት፣ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና የፈጠራ ድህነት፣ የሶሻልና ፖለተካ ሳይንስ ድህነት፣ ተዉጧል። በስነ ጥበብ ማለትም በስዕል፣ ጠረባ፣ ሙዚቃ፣ ስነጽሁፍ፣ ቲያትር፣ ውዝዋዜ፣ ስነሲኒማ፣ ስነፎቶ ሁሉ ድህነት፤ በሕግና ስነምግባር ድህነት ጭምር የታጠረ ሁኖዋል። ህብረተሰቡ በጥቂት ያልተማሩ ሃብታሞችና በብዙሃን ያልተማሩ ድሆች ተከፋፍሏል። ከላይ የተዘረዘሩትን መስኮች ሊፈጥር የሚችለው ምሁር ወይም ተሰዷል፣ አለያም ፈጽሞ የለም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን በአይምሮዋቸው የሚሰሩ ሕዝቦች ሳይሆኑ መደባዊ ክፍፍሉ በሚበሉና በሚራቡ ሰዋዊ እንስሶች መካከል ነው። ይህ ሰቆቃ (ትራጀዲ) እንጂ ሽግግር አይደለም።

ከዚህ መቀመቅ እንዴት እንደሚውጣ የሚያሳይ ብርሃን አለን? ለኢትዮጵያ ወድቀትና ወድመት ምክንያት አገሩ ቀውስ መሆኑ ብቻ ኣይደለም። ከፍተኛ ያስተሳሰብና የመመራመር ድርቀት አለ። ከፍተኛ የፈጠራ አልባነት ጭለማ ሰፍኗል። ትልቁ ችግር የድንቁርና መስፈን ነው። በዚህ ጭለማ ወስጥ ከምዕራብ በሚመጣ ውራጅ ሸቀጥና ባህል አንድም ፋይዳ ለመፈየድ አይቻልም።
ስለሆነም አዲስ ቅድመ መርህ (አዲስ ፓራዳይም) አዲስ መርሃ እሴት (ቫልዩ ፕሪንሲፕል) መፈልሰፍ አለበት ። ይህን መሰል የሃሳብና የፈጠራ ብርሃን በኢትዮጵያ ምሁራን ሁሉ ይሞከራል ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ነው። የጎሳ ፖለቲካ የምሁራንን አንድነት አፍርሷል። ተያይዞም ብሄራዊ (አገራዊ) የሃሳብ አንድነት ፈርሷል። በመሆኑም ሙሉ ባህል ወይም አሞሌ ካልቸር፣ የኢትዮጵያ ምልአተ ባህል ሊፈጥሩ አይችሉም፤ እንዳይፈጠር አድርገዋል። የኢትዮጵያ እጅግ መሰረታዊና ወሳኝ ቀውስ (ችግር) መከፋፈል፣ መበታተን ነው። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ብትንና የቅውስ (ኬዎስ) ስርዓት ነው። ከሃይማኖት እስከ ተራ ሕይወት ሁሉም ብትን ስርዓት ነው።

ኢትዮጵያ ብትን ስርዓት እስከ ሆነች ድረስ ምልአተ ባህል፣ እሴተ ተዋህዶ ያለው ብሄራዊ ሴራ መፍጠር አለመቻል ብቻ ሳይሆን የተበታተኑት ክፍሎች እርስበርሳቸው ይጋጫሉ፣ ይጣላሉ፣ ይወድማሉ። ከላይ የተዘረዘሩት የባልና የፈጠራ መስኮች የሚንቀሳቀሱት በሰዎች፣ በቡድኖች፣ በሕዝብ ነው። እነዚህ የባህል ተሸካሚዎች እስከተበጣበጡ ድረስ አንድ ወጥ ነገር ለመፍጠር አለመቻል ብቻ ሳይሆን ምንም ነገር ሊፈጥሩ አይችሉም፤ አንዱ ሌላውን ስለሚያፈርሰው። ኢትዮጵያ ብትን ስርዓት ብቻ ሳትሆን የግጭት ስርዓት ነች ። የእርስበርስ መጠፋፋት፣ መዋደም፣ የእልቂት ስርዓት ንች ። ይህን መሰል ህብረተሰብ ወደ ታች እንጂ ወደ ላይ አይሸጋገርም። ለዚህ ሁሉ መሰረቱ ኢትዮጵያዊያን ማንም ይሁኑ ከየትም ይወለዱ፣ በአንድ ፈጣሪ የሚያምን፣ በሰው ልጅ ሰባዊነትና ልዕልና የሚያምን፣ በኢዮጵያዊያን ሁሉ ወንድማማችነት የሚያምን አንድ ሕዝብ አለመሆናቸው ነው። ይህን መሰረት፣ ይህን ቅድመ መርህ፣ ይህን ፓራዳይም እውን የሚያደርገው ትውልድ ገና የለም።

ያልኳቸውን ነገሮች በትንሹ ለመድገም፣ ኢትዮጵያ በማንኛውም መስክ ብትለካ ማለትም በሃይማኖት፣ በፍልስፊና፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሶሺያል ሳይንስ፣ በስነ ጥበብ፣ በሕግና በስነ ምግባር በሁሉም መስክ ቁርጭራጭ ስርዓት ነው። እነዚህ እጅግ ብዙ ቁርጭራጮች በግለ ህልውናቸው ፋይዳቢስ ሲሆኑ በህብረ ህልውናቸው ተጻራሪ፣ ተዋዳሚ፣ ተፋላሚና የግጭት መነሾዎች ናቸው። ስለዚህ ለየብቻም በህበረትም ዋጋቢሶች ናቸው። በግል ለድህነትና ለድንቁርና ተጋልጠዋል፤ ከተባበሩ ይተላለቃሉ ። መውጫ የለሽ ዙሪያ ጥምትም ማለት ነው።

ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች በኢትዮጵያ ግለሰቦች እና ቡድኖች አይምሮ ላይ ወይም አስተሳሰብ ዘንድ የሚያስከትሉት ተጽዕኖዎች አሉ። የግለሰቦች፣ ብሄረሰቦችና ቡድኖችን የማንነት ትርጉም ለውጠዋል፣ አናግተዋል። እነዚህ የምንነትና የማንነት ትርጉሞች ተበታትነዋል፣ ተፍረክርከዋል፣ ተቃውሰዋል፣ ተዘባርቀዋልም። ተያይዞም እነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች ያሏቸው፣ የነበራቸው እሴቶች ወይም ሰርዓተ እሴቶች፣ አስተሳሰብ፣ መርሆችና እምነቶች ተበታትነዋል፣ ተፍረክርከዋል፣ ተቃውሰዋል። የሞራል ስነስርዓታቸው ላሽቋል፣ ወድቋል። ማለትም ደግና ክፉ፣ ጥሩና መጥፎ፣ ትክክልና ስህተት፣ ፍትህና ግፍ፣ ጠቃሚና ጎጂ፣ ገምቢና አፍራሽ፣ እድገትና ወድቀት፣ ልማትና ወድመት፣ ነጻነትና ባርነት፣ ትልቅነትና ትንሽነት፣ ክብርና ውርደት፣ ራዕይና መታወር፣ ብርሃንና ጭለማ፣ ፍቅርና ጥላቻ፣ የሰላምና ሽብር፣ ስርዓትና ቀውስ በአንድ ቃል ደህንነትና ድህነትን የሚለይ የግምትና የህሊና ተቋማቸው ወይም ችሎታቸው ተቃውሷል።

ከላይ የተጠቀሰው መበታተንና መጋጨት የግለሰቦችን አስተሳሰብና ሰነምግባር በመበታተን ላይምሮና የሞራል አናርኪ ዳርጓቸዋል። ማሀበራዊ አናርኪና ያስተሳሰብ ምስቅልቅልነት አይነጣጠሉም። አንዱ ሌላውን ይወልዳል፤ እንዲያውም ያስተሳሰብና የሞራል ስርዓት ሳይኖር ማህበራዊ ስርዓት ሊኖር አይችልም። ብትን ሃይማኖት፣ ብትን ፍልስፍና፣ ብትን እሴት፣ ብትን ፖለቲካ፣ ብትን ስነት፣ ወዘተ የሚፈጥሩት ብትን ህብረተሰብን ነው።

ያስተሳሰብ፣ የህሊናና የሞራል ቀውስ ወይም አናርኪ ውጤቱ የተፋፋመ ቅራኔ ፣ ግጭት፣ ሁከትና ጦርነት ነው። በኢትዮጵያ የሃይልና የጉልበተኝነት ሚና እየገነነ ይሄዳል። ጦርነት፣ አብዮት፣ አመጽ፣ ወንጀል፣ ሕግ አልባነት በአገሪቱ ይስፋፋሉ። በሰው ሕይወት ላይ እልቂት ይከተላል። የሕዝቦች ቁሳዊ መደላደል (አኗኗር) ይፈርሳል። ያገሪቱ ቁሳዊ ሃብት ይወድማል። ይህ የመጨረሻ ወድመትና ጥፋት ከሚከተሉ ሶስት አዝማሚያዎች አንዱን ሊወድ ይችላል።

አንደኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በብትንትንነቱና በቀውሱ ለረጅም ዘመን ሊቀጥል ይችላል። ይህም ማለት አገሪቱ ምንም አይነት መሰረታዊ መፍትሄ ሳታገኝ በሞትና በህይወት መካከል አሳዛኝ የሆነው ህልውናዋ እንደ ተንጠለጠለ ሊቀጥል ይችላል።

ሁለተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በተወሰኑ ሰፋፊ መሬቶች ፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ግዛቶች፣ ተከፋፍሎ በአዲስ ፌዴራላዊ ወይም ኮንፌዴራላዊ ስብስብ ሊቀጥሉ ይችላሉ። ኢትዮጵያ በብዙ አገሮች የምትከፋፈለቅ ይህ አዝማሚያ እውን ከሆነ ነው።

ሶስተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ መሰረታዊ ያስተሳሰብና የእስትራተጂ ለውጥ አድርጎ ስርወ እሴታችን የአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ የሰው ልጅ ልዕልናና የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ሆኖ አገሪቱ ከውድቀት ልትድን ትችላለች ።

ከነዚህ ሶስት አዝማሚያዎች የትኛው እውን እንደሚሆን የሚወሰነው በኢትዮጵያ ምሁራን መካከል ባለው የሃይል ሚዛንና የማሰብ ችሎታ ነው። ለምሳሌ ያንድነትም ሆነ የብሄረሰብ ምሁራን ከደከሙና አዲስ መፍትሄ ማቅረብ ካልቻሉ ወይም አንዱ ከለላው በልጦ ማሸነፍ ካልቻለ አንደኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

የብሄረሰብ ምሁራን የበላይነት ይዘው የጎሳ ክፍፍል አሁን ባለው ቀጥሎ ካደገና ካሸነፈ ሁለተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል። የኢትዮጵያ አንድነት ምሁራን ከጠነክሩ ሶስተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

ለምሳሌ ሶስተኛው አዝማሚያ ሃይማኖትን በተመለከተ የኢትዮጵያዊያን እምነት ሆነ አምልኮ መሆን ያለበት እግዚአብሄር፣ ክርስቶስ፣ አላህ፣ ያዌ፣ ጂሆቫ፣ ዋቃ፣ ሌላም ሌላም በሚል መናቆር ሳይሆን በአንድ ፈጣሪ ማመን ነው። ቤተ እምነት ሆነ ቤተ አምልኮ ሁሉ የአንድ ፈጣሪ ቤተመቅደስ ሆኖ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የአንድ እምነት አማኝ አንድ ሕዝብ መሆናቸውን መቀብለና ያንን ማስተማር አለበት ። የኢትዮጵያ ብሄረሰብ ግለሰቦች ሁሉ ማለትም ኢትዮጵያዊ ሰው ሁሉ የአንድ ፈጣሪ ፍጡራን እንደ ሆኑ። እነሱም አንድ ኢትዮጵያዊ ብሄር እንደሆኑ ተቀብሎ የኢትዮጵያ ጎሳ እንደሆኑ ማመንና ማስተማር አለበት ። በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አንድ ቤተሰብ ፣ ወንድማማች እንደሆኑ ማመንና ማስተማር አለበት ።

በእነዚህ ሶስት ስረወ እሴቶች መሰረት የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣ የፍልስፍና፣ የስነ ጥበብ፣ የማህበራዊ ሳይንስ፣ የሕግና የስነ ምግባር ውህደቶችን የሚያንጸባርቅ ባህል፣ ፈጠራ፣ ንድፈ ሃሳብ መቀመር ግድ ይላል። የኢትዮጵያ አንድነት ምሁራን ይህን ማድረግ ካልቻሉ የጎሳ ምሁራን አሁን በጀመሩት አጀንዳ ቀጥለው ሕዝቡን በብዙ አማልክጥ በብዙ ጎሳዎች፣ በብዙ ቋንቋዎች፣ በብዙ ባህሎች በመከፋፈል ይህም ውሎ አድሮ ወይ ኢትዮጵያ መከፋፈል ወይም ወደ ኢትዮጵያ ወድመት ማምራቱ አይቀሬ ነው።

ይህን ያልኩት የዛሬ 25 አመት ነበር ።

አንድ ጽንሰ ነገር ተቀርጾ፣ ተተክሎ፣ ለምቶ እስኪያብብ በድጋሚ በድጋሚ እንክብካቤ ይሻል። ስለ ኢትዮጵያ ማህበረ ሰብ፣ ስለ ኢትዮጵያ ፍጥረ ግብር ወይም ካልቸር ስናስብ ያለው ሃቅ ተመሳሳይ ነው።

እንደ ገና ልድገመው፤ ሁላችንም የምታኮራ፣ ተወዳጅ ኢትዮጵያ ላይ ለመስማማት ሶስት ስርወ እሴቶች ወይም ኮር ቢሊፍስ ላይ እንስማማ።

ሁላችንም በአንድ ፈጣሪ እንመን ። ያ አንድ ፈጣሪ በተለያዩ ስሞች መጥራታችንን ተቀብለን በስም ልዩ በይዘት አንድ እምነት እንዳለን እንቀበል። ከዚያም ይህ አንድ ፈጣሪ የፈጠረውን የሰው ልጅ ማለትም አንድ ግለ ሰብ ፍጹም ልኡል፣ ፍጹም ነጻ የሆነ ሰብአዊነቱም ከፈጣሪው ያገኘው መሆኑ ላይ እንስማማ። ይህም ስለሆነ ኢትዮጵያዊያን ሰው በመሆናቸው ብቻ ወድማማች በመሆናቸው እንስማማ።

ይህ ነው ያንድ ትልቅ ካልቸር ወይም ፍጥረ ግብር መሰረቱ። በዚህ መሰረት አንድ ኢትዮጵያዊ ካልቸር (ፍጥረ ግብር) ይፋፋል። ከዚያ በኋላ በኢትዮጵያ አጀንዳ ላይ መጣላታችን ያበቃል።

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 16 Jul 2020, 15:20

ከሰኔ 2012ቱ የቄሮ ፎሌ ወረር ወዲህ ጥግን የጎሳ ሰርዓት ለመቀጠል የሚሞክረው ክፍልና (ያቢይ ካምፕ) እና ኢጎሳዊ ሰርዓት እንዲመጣ የሚሞክረው ካምፕ በግልጽ እየተለያዩ ነው ። ስለዚህ አሁን የኢትዮጵያ ሃይሎች አሰላለፍ በአገር አፍራሽ አክራሪ ጎሰኞች፣ በጠጋኝ የጎሳ ሲስተም አማኞች፣ እና በኢጎሳዊ ኢትዮጵያዊነት ካምፖች የተከፈል ሆኖዋል።

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 16 Jul 2020, 18:18

ይህን ድንቅ ውይይት ተከታተሉ ።

የጎሳ ፖለቲካም ሆነ አይዲዮሎጂ በፍጹም መልስ አያገኝም ፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ኦሮሞ ነው ውይስ አይደለም የሚለው ጥያቄ በፍጹም ሊመለስ አይቻልም ። የጎሳ ወይ የዘር ጽንሰ ሃሳብ ምንም ሌላ ቁሳዊ መሰረት የሌለው መናብ ወይም ሃሳብ ነው። ይህ የኦሮሞነት ንትርክ የሚቆመው ኦሮሞ የሚለው ሃሳብ ሰው በሚል ቃል ሲተካ ብቻ ነው።


Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 17 Jul 2020, 21:12

በሰሞኑ ሽብርና ጄኖሳይድ ውስት ያሉት ድብቅ በረከቶች ብዙ ናቸው ፤ እመለስባቸዋለሁ ።

Horus
Senior Member+
Posts: 40301
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 4ቱ የኢትዮጵያ ገጋይ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 20 Jul 2020, 23:46

ያቢይ መጀመሪያ እርምጃ ሕገ መንግስት ትብዪውን መግታት ነው ።

Post Reply