Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
AbebeB
- Member+
- Posts: 7694
- Joined: 15 Oct 2016, 10:31
Post
by AbebeB » 22 Jun 2020, 20:07
ወንዝ ለወንዝ መቀደስ፣ የተኛውን ሰይጣን መቀደስ ነው በማለት ያብራሩት የኢዜማ ተወካይ፤ አርቶዶክስ ተወሂዶ በሀይማኖት በዓላት በማሳበብና በሌሎችም ጊዜያት ወደ ወንዝ የሚዱበትን ዓላማ አጋልጠዋል፡፡ ነገር ግን የተዋሂዶ ቄሶች ሰይጣንን ሲቀሰቅሱ ከሚከተለው የደም መፍሰስ ምን ዓይነት ጥቅም ለማግኘት ከሰይጣን ጋር ውል እንደሚተባበሩ (እንደሚቀሰቅሱት) አልገለጹም፡፡ የደቡብ ሕዝቦችን ብሔራዊ ጥያቄ እያነሱ በተለይም የወላይታ ሕዝብ በወሳኝ ትግል ላይ እያለ ተወካዩ ይህን አስጸያፊ ቃል መጠቀማቸው ኢዜማ ለደቡብ ሕዝቦች በጠቅላላው እና ለወላይታ ብሔር ደግሞ በተለይ ያለውን ጥላቻ አመላካች ነው፡፡
ሌላው የኦፌኮ ተወካይ ደግሞ ዛሬ ላይ በመቀሌና አዲስ አበባ መካከል የሚመላለሱት የሀይማኖት አባት ተብዬዎች በ2008 በኦሮሚያ ውስጥ ተጋግሎ የነበረውን አመጽ ለማስቆም እንዲተባበሩ በደብዳቤ ተጠይቀው ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸውን አጋልጠዋል፡፡
ታዲያ ዛሬ ላይ የሀይማኖት አባቶችን እንቅልፍ ያሳጣቸው መኖ ሳስቶባቸው መንግስት ለቀቅ እንዲያረግላቸው መሆኑን አመላካችነቱ ያጠራጥራል?