ዶክተር ሊያ ባለፉት 2 ሳምንታት 81 የጤና ተቋም ሰራተኞች (የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮ) በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸውን አሳውቀዋል።
እስካሁን 97 የጤና ተቋም ሰራተኞች (የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮ) በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። ከነዚህ መካከል 55% የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
በቫይረሱ ከተያዙት 97 የጤና ተቋም ሰራተኞች መካከል ዘጠና አንዱ (91) ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው።
የምልክት ሁኔታቸው ሲታይ 86% የሚሆኑት ምልክት ያላሳዩ ሲሆኑ 14% የሚሆኑት ምልክት ያሳዩ ናቸው።
በተጨማሪ ባለፈው አንድ ወር ወደጤና ተቋማት ለሌላ ህክምና መጥተው ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ተቋማት ሰራተኞች 2,340 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 1,727 በመጋቢት ወር ነው ተጋላጭ መሆናቸው የተገለፀው።

