ኤርትራና ኮሮና ቫይረስ (Part - One)
(By Elijah Eritrean - Facebook) - የኤርትራ የቻይና ቫይረስ ማሸነፈ ሚስጥሩ ምንድነው? እስከ አሁን ኤርትራን ጨምሮ ፣ 12 ሀገራት ከቫይረሱ ነጻ ሆነዋል። ኤርትራ እንያት እስቲ።
*
ኤርትራ ገና ቫይረሱ ኤርትራ ውስጥ ሳይገባ ነው መመርያዎች ማውጣት የጀመረችው። ይህ ማለት ቫይረሱ ከቻይና አልፎ በኢራን፣ ኮርያ ና ጣልያን ሰዎችን በብዛት እያጠቃመበት በነበረው በመጋቢት 11/2020 ማለት ነው። በዚህ ግዜ ከተወሰዱ ወሳኝ እርምጃዎች አንዱ ወደ ኤርትራ የሚመጡ መንገደኞች እንዲወሸቡ ማረግዋ ነበር።
*
ኤርትራ የመጀመርያ ታሚሚ ያገኘችው መጋቢት 21 ከኖርወይ የመጣ ኤርትራዊ ዜጋ ነበር። ከዚህ ብኋላ አዳዲስ መመርያዎችን አወጣች።
- ግዴታ ካልሆነ፣ ከሀገር ውስጥ መግባትና መውጣት ፣ እገዳ ጣለች።
- ከ10 ሰው በላይ መሰብሰብ ከለከለች
- የእምነት ቤቶች እንዲዘጉ ታወጀ እና ሌሎችም። እነዚህ ሁሉ ገና አንድ ሰው እንደተገኘ ነው።
መጋቢት 25፣ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ከውጪ ሀገር የመጡ፣ 3 አዲስ ታማሚ ሲገኙ፣ ከኤርትራም ወደ ኤርትራ የሚደረጉ All Commercial Flights ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ እንዲቋረጡ ትእዛዝ አስተላለፈች። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 4 ደረሰ። አሁን ቫይረሱ ሊገኝባቸው የሚችሉ ሰዎች፣ በረራ ከመታገዱ በፊት ቀድመው የገቡ ብቻ ናቸው ማለት፡ነው።
ኤርትራ ቀጥላ፣ ተጨማሪ መመርያዎች አወጀች
- ትምህርት ቤቶች ተዘጉ
- የታክሲ ማቆምያዎች ተዘጉ
- ምግቤትና ባሮች ሰዓት እላፊ ተጣላባቸው
- ፍርድ ቤቶች ተዘጋ። እስከዚህ ቀን total 6 ተይዘዋል።
መጋቢት 30 ውሸባ ውስጥ ካሉ፣ ተጨማሪ 9 ሰው ቫይረሱ ተገኘበት። tota 15 ደረሰ።
ኤርትራ፣ ተጨማሪ መመርያዎችን አወጀች፣ ከነዚህ መካከል
- ከሚያዝያ አንድ ጀምሮ ለ21 ቀናት የሚቆይ total lockdown all over the country አውጀች - stay at home.
- ከሁለት ሰው በላይ ከቤት እንዳወጣ
- ምግብ ቤት ባር ሆቴሎች እንዲዘጉ
- ባንክ ፣ ፋርማሲ፣ ስፑር ማርኬቶች ስራቸው እንዲቀጥሉ
- የገጠር እርሻ ባለበት ስራውን እንዲቀጥል እና ሌሎችም ጭምር እገዳ ጣለች።
አሁን አስመራ ብቻ ሳይሆን ኤርትራ ሙሉ በዝምታ ተሞላች። ጭር ማንም የለም።
ኤርትራ፣ እስከ ሚያዝያ 21፣ ተወሽበው ከነበሩ፣ ተጨማሪ 24 ታማሚ ስታገኝ፣ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 39 ደረሱ። ከነዚህ መካከል ደግሞ 6 አገግመው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቀሉ።
የ stay at home መመርያ የሚያበቃበት ግዜ በዚህ ቀን ነበር። ኤርትራ ግን፣ አዲስና ቆፍጠን ያለ መመርያ አወጣች እሱም እንዲህ ይላል።
ከዚህ በፊት የወጡ ሁሉም፡መመርያዎች ፣ ቫይረሱ ከኤርትራ ጠቅልሎ እስኪጠፋ ድረስ ፣ ባለበት ተግባራዊ እንዲሆን።
ይህም stay at home የሚለውን አዋጅ ፣ ላልተዋወቀ ግዜ አራዘመው።
*
እስከ ግንቦት 8 ድረስ ማለት ለ14 ተከታታይ ቀናት አዲስ ሰው ያልተያዘ ሲሆን፣ ማዳኑ ላይ ትኩረት በማድረግ፣ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 37 ደረሰ። ከዚህ ቀን ጀምሮ ኤርትራ ቀድመው የወጡ ትእዛዞችን ለቀቀ ማረግ ጀመረች። እንደ ሱቆች መከፈትና የተወስኑ እንቅስቃሴዎችን ፈቀደች።
ግንቦት 12፣ ደግሞ ያገገሙ 38 ደረሱ።
ግንቦት 15፣ ኤርትራ ከቫይረሱ ነጻ በመሆን፣ ከ39 ታማሚ፣ 39 ኙ ሲያገግሙ፣ በአፍሪካ ቫይረሱን በመቆጣጠር፣ ቀዳሚዋ ሀገር መሆንዋን አወጀች።