Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39884
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጉራጌ፣ አርጎቤ፣ አደሬ፣ ጋፋቴ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ አረርጌና አርሲ የቆረቆሩ እነሱ ናቸው ።

Post by Horus » 15 May 2020, 02:37

ታሪክና ምርምር ለምትወዱ ይህን እጅግ ጠቃሚ አመልካች ግኝት ይድረሳችሁ ። አደሬ የአረዴ ጉራማይሌ ነው። አረርጌ ማለትና አደሬ ማለት አንድ ቃል ነው ። አረጌ (አረዴ) የአርዴ ዘሮች አርጎባ፣ አደሬ፣ ጉራጌዎችና ጋፋቶችን ይጠቀልላል። ፋጣጋር ያርጎባ አገር ነበረች። በምስራቅ ኢትዮጵጵያ በኩል የነዚህ ሁሉ ግንድ ሃርሌ ወይም ሄራሌ የተባሉ ሕዝቦች ነበሩ ። ሃረር ብቻ ሳይሆን ሂርናን የቆረቆሩ ሄራሌ ወይም ሄራኖች ናቸው። ለምሳሌ አርሲ የሚባለው አገር ያቆሙ እነሱ ናቸው ። አርሲ ማለት አርዴ ማለት ነው። አሰላ የተሰኘው የከተማ ስም የአርሲ ጉራማይሌ ነው። ደራ የሚባለውን የአርሲ ክፍለ አገር የሰየሙ እነሱ ናቸው። በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ የሚገኙት ሁሉም አንድ የዘር ግንድ ያላቸው አርዴዎች የላቄ ዛዮች፣ ኡር ባረጌ (ኡር ባረዴ)፣ አዘረነት፣ ስልጤ፣ አረቴ፣ እያለ እስከ እንደ ጋኝ፣ እስከ ጋፋት ተበታተኑ። አርጎቤ (ቤ ማለት ቤት ማለት ነው ልክ እንዴ አደሬ) አረጌቤቶች ወደ ታች ወደ ደቡብ አርሲና ባሌ ድረስ ተበተኑ ። የቀሩት በየረር፣ በመናገሻ ፉሪ፣ በሰንዳፋ አሉ። ይህ እንግዲህ በደቡብ ወሎና በምስራቅ ሸው ካሉት ሌላ ማለት ነው። ለምሳሌ የሰሜን ጉራጌ ክስታኔ ቋንቋ ከአደሬ ጋር እጅግ ቅርብ ነበር ። ከ35% በላይ ቃላት ይጋራሉ። ቱርክ ሃረርን ይዞ ያደሬ ባህል ከመዳከም በፊት ። ይህ ሁሉ ወደ ፊት ሳይንሳዊ ጥናት ያረጋግጠዋል ። ዛሬ ጄኔቲክ ማፕ ቢሰራ ያርሲ ሕዝብ፣ የአደሬ ፣ የአርጎባ፣ የጉራጌ ደም ጋር ባብዛኛው ከ70 እስከ 80% አንድ ይሆናል ።

ሌላ ግዜ አርጎባ ማለት አደሬ ማለት፣ አረሬ ማለት፣ ሃርሌ ማለት፣ አርሲ ማለት፣ አሰላ ማለት ... ወዘተ ትርጉሙን ለሚሹ ይገለጻል ።

Horus
Senior Member+
Posts: 39884
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጉራጌ፣ አርጎቤ፣ አደሬ፣ ጋፋቴ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ አረርጌና አርሲ የቆረቆሩ እነሱ ናቸው ።

Post by Horus » 15 May 2020, 03:30

ዝዋይ፣ አድኣ፣ አዳዲ፣ መቂ፣ ወዘተ ዛሬም የዚያው የግዱን ምንነት እያረጋገጠ ነው፣ የስራ ስነ ምግባር !!! ከላይም ገላን እንዲሁ ነው ። ያዬም እንዲሁ ነው። ጂዳስ ቢሆን ዘሩን ቢክድ ያው የሚለማው በጂኑ ባገኘው ጸጋ ነው። ይህ ደሞ በጣም ደስ ይላል ፣ ሰው ነጻ የሚሆነው በስራ እንጂ መንገድ በመዝጋት ፣ ቴዲን እንዳይዘፍን በቆም አይደለም ። ቴዲ ስለሚኒልክ መዝፈን አላቆመም ። ሚኒልክን መሸጥ የገቡት ራሳችው ኦሮሞች ናቸው። ፍሬ ከግንዱ ርቆ አይወድቅም ይባል የለ !!

Post Reply