በጉራጌ ሴቶች ሙየት (ሙዊየት) የሚባል ባህል አላቸው ። ይህ ባህል በመስከረምና መስቀል ሰሞን የሆነ መንፈስ የያዛቸው እናት ሴት ቀይ እባብ (መርዝ የላቸውም) ቅቤ እያበሉ በየቤቱ እየዞሩ ገንዘብ፣ ሽቶ፣ ሻሽ ምናምን ከሴቶቹ በተለይ ከልጅገረዶቹ እያስፈራሩ ይሰበስባሉ ። ይህ ባህል ወይም ልምድ በሳይስ ተመርምሮ የተገኘው መልስ ሴቶች በወንድ ጭቆና የታመቀውን ስሜትና ፍላጎታቸውን ሃይል አግኝተው የሚያሳዩበት ተግባር ክንዋኔ ነው የሚል ነው። እስማማለሁ ።
አሁን በኦርቶዶክስ ቤተስኪያን ሰፈር ያሉት እህተ ማሪያም ቀዳማዊት፣ እና ዳግማዊት የማያቸው ልክ እንደ ጉራጌ ሙየት ነው ። በጉራጌ መጀመሪያ ለጻነት የታገለች ሴት ነች፣ ወንድ አይደለም ። አሁን ህንድ ውስጥ ሴት ከባሏ ኋላ ኋል ነው ምትሄድ ። አረብ እንዲሁ።
በኢትዮጵያ ሴቶች ነግሰዋል ፣ ጦር መርተዋል፣ የእግዚአብሄር እናት ሆነው አምላክን ወልደዋል ። ይህን ሃይል ለማረጋገጥ ነው እነዚህ አዳዲስ ማሪያሞች ሚወለዱት ። እኔ ምንም ችግር ኣላይበትም ። ወንድ ሃያላን ናቸው አሁን የተደናገጡት ። ለሴቶች ሃልይ እንስጥ ወይም ለመከልከል አንሞክር ?? ይልቅስ ችግሩ ያለው ቴክኖሎጂና ሳይንስ ላይ መዋል ያለበት ወንድ ተብዬ ነጠላ ለብሶ እንደ ልጃገረድ በዲክታተሮች እየተገዛ ሲዘምር የሚውለው ወጣት ላይ ነው ። በሳይንስና ሃይማኖት መሃል ያለውን መመሳስለ ማየት የማይል ሳይንቲስትም ቄስም መሆን አይችልም ። ዝም ብሎ ብኩን ነው !!