Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
ENTEL KORACH
Member
Posts: 272
Joined: 18 May 2013, 09:45

The evil weyanes horrendous crime.

Post by ENTEL KORACH » 22 Apr 2020, 01:34

April 20 at 1:30 PM ·

ሀጂ ነጋሽ ሰዕድ እባላለሁ የመቶ አመት የዕድሜ ባለ ፀጋ አላህ ለጉድ ያስቀመጠኝ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ነዋሪ ነበርኩ በወጣትነት ዘመኔ አረብ ሀገር ሄጄ ያፈራሁት ሀብትና ንብረት /ቪላ ቤትና የንግድ ድርጅት/ ጭምር በስድስት መቶ ሺህ ብር በሀራጅ ገዝቸዋለሁ የሚል አንድም ቀን ያለየሁት ችሎት ቀርቦ ያልተከራከረኝ ሰው ቤቱንና የንግድ ድርጅት ጭምር በሀራጅ ገዝቷል ተብሎ ለቡዙ ዓመት በፍርድ ቤት ሲያንከራትተኝ ቆይቶ በመጨረሻ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የተከራከረኝ የተጭበረበራ ሰነድ ነው ተብሎ ቤቱን እንዲረከብ የተወሰነልኝ የፍርድ ውሳኔ ሳይፈፀምልኝ።አቤት ብል የሚሰማኝ አጥቼ እያለሁ ሌላ ተጋይ ነኝ የሚል ሰው አርብ ለጁምዓ ሷላት ወደ መስጂድ ስሄድ ''ቤትህ ውስጥ ቦንብ ተደብቋል " አክራሪ ነህ ተብለህ በእስር ከምትማቅቅ ከአካባቢው ዞር በል አለኝ። የህዋሃት ታጋይ ነኝ የሚል ይሄው ሰው ወቅቱ አስፈሪ ስለነበር በመቶ አመት ዕድሜዬ የማላስበውና የተባሉትን ነገሮች በእጄ ይዤ የማላውቅ ሰው በልሰራሁት ወንጀል እንዳያስሩኝ ብዬ ለጥቂት ቀናት ከመንገድ ዞር አልኩ ሲመለስ ልጆቼን ድርጅቴን የተካራዩ ሰዎችን ከቤት አስወጥቶ አባሮ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ታጋዩ ቤቴ ውስጥ ገብቶ እስከ አሁን አልወጣም አለኝ። ይህ ታጋይ ነኝ ባይ በፍርድ ቤት ተካሰን አናውቅም ውልም አልፈፀምንም ። ይሄው ታጋይ ነኝ ባይ ማፊያ ቡድን አዘጋጅቶ በላዳ ታክሲ ውስጥ አስገብተውኝ መድሃኒት በግድ አጠጡኝ ራሴን ሳትኩ ከገርጂ ጎሮ ድልድይ ወደ ገደል ሊጥሉኝ ሲሉ ሰው አይቶአቸው እዛው ጥለውኝ ሄዱ ከሳምንት በኋላ ሽንት መሽናት ከለከለኝ ወደ ህክምና ሄጄ ከሆስፒታል በተደረገልኝ የሽንት ማስወገጃ ፕላስቲክ ቱቦ አንጠልጥዬ ተከራከርኩ።የኔን ጉዳይ የሚያይ ደኛ የለም ብመጣም ቀጠሮ ብቻ ለምን? የልደታ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮ ቤተሰብ የሆኑት ታጋዩ ቤቴን በነፃ ሰጥቷቸው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይኖሩበታል ይነግዱበታል። ከቤቴ በሚገኘው ገንዘብ ነው ፍትህን እያዛባ ነውያለው። ሌላው አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሽሮ እኔ በማላውቀው ሁኔታ በሚስጥር " የቤቱን ካርታ አምክኑት" ብሎ ለቦሌ መሬት አስተዳደር የፃፈውን ትዕዛዝ በእጃቸው ይዘው አሳይተውናል።ፍትህ አጣሁ በማለት በብሶት ይናገራሉ። በእውነት የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 25 ለማነው የሚሰራው? እውነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህግ ፊት እኩል ነው? እስኪያሰኘን ድረስ ጉዳዩ ገረመን። እሳቸው እንደሚሉት አማርኛ መናገር አለመቻሌ ነው፡ ለዚህ ሁሉ የዳረገኝ ይላሉ። እኛም በጉዳዩ ተገርመን ከለውጡ በኋላ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አለመለከቱም? ብለን ጠየቅናቸው።እሳቸውም ሲመልሱ ልጄ በር ላይ ስደርስ እንደ ውሻ ያበርሩኛል ሃላፊዎቹን መግኘት አልቻልኩም ይላሉ። አሁን የት ይኖራሉ? ሰው ለምኜ ፈጣሪን የሚፈራ ያሳድረኛል። ምን ይበላሉ ? ከገኘሁ በላለሁ ካጣሁም እንደዚያው ይላሉ። ለሀገር እንጂ ለእኔ ለውጥ የለም ይላሉ።ሙሉ ታሪኩን በቅርብ ቀን ይጠብቁ።
እውነቱን ተገንዝቦ ለፈጣሪ ብሎ ቤቴንና ድርጅቴን የሚየስመልስልኝ ሃለፊ በኢትዮጵያ ካለ በስልክ ቁጥር 0912426789 ይደውልልኝ። ለምታደርጉልኝ ድጋፍ ሁሉ አላህ ጀዛችሁን ይመልስላችሁ። ሀጂ ነጋሽ ሰዕድ ሚያዚያ 06 ቀን 2012 ዓ.ም. share በማድረግ ለአዘኙ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አድርሱልኝ ይላሉ። ፈረንጆች እንዲህ ይላሉ justice is prerequisite for peace, peace is prerequisite for development.ለደገፋችሁኝ ሁሉ ሀሳቤን የተጋራችሁ ሁሉ አላህ በችግር ጊዜ ከጎናችሁ ይቁም በማለት ለሁላችሁም መልዕክት አስተላልፈዋል።



( ͡° ͜ʖ ͡°)
Member
Posts: 2312
Joined: 11 Jan 2020, 21:22

Re: The evil weyanes horrendous crime.

Post by ( ͡° ͜ʖ ͡°) » 22 Apr 2020, 02:51

So sad! Agame are evil creatures. :x :x :x

Post Reply