Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40154
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ወራፎ፣ ኢዘዲን ካሚል በወጣቱ አይምሮ ውስጥ የነፋው ማንቂያ !!

Post by Horus » 21 Apr 2020, 01:05

ይህ የዘመናችን ልሂቅ ብላቴና ለኮሮና መተንፈሻ የፈለሰውን ቴክኖሎጂ 'ወራፎ' የሚል ስም ስጥቶታል ። ወራፎ ማለት የብረታ ብረት ጠቢባን ብረት ለማለስለስ እና ብረት ለማቅለጥ የሚነፉበር ሃይድሮሊክ ሲሊቻ ነው። እጹብ ድንቅ የሆነ ስያሜ ነው።

ወራፎ በሰባት ቤት፣ ወላፎ በክስታኔ መንፊያ ማለት ሲሆን የቃሉ ስር ግዕዝ ንፋት ፣ ነፍስ፣ መተንፈስ ማለት ነው ። ከዚህ የተሻለና የበለጠ ስም የለም ፤ ሬስፕሬቶሪ ማዚን ለማለት !!

እኔ ግምት፣ ይህ ልሂቅ ብላቴና የመላውን ወጣት ትውልድ አንጎል ያነቃነቀ ፣ ያነቃቃ ብላቴና ነው ።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ልጅ ሳቢያ ያለም ካርታ ላይ እንደ ሚበሩ ጥርጥር የለኝም !!!