* ስለ ህዳሴ ግድብ ምን አገባን።ይህ በግልፅ ግብፅን እሰከ መደገፍ ይደርሳል( መሐሪ ዮሃንስ)
*ኢትዮጵያ ጎረቤት ሃገር ነች።ይህ በግልፅ ኢትዮጵያና ኡጋንዳ መቐለ እግር ኳስ በተጫወቱ ግዜ ሁለቱ ጎረቤት ሃገሮች በመቐለ የእግር ኳስ ጨወታ አደረጉ እስከ ማለት በብዛት ፅፈዋል።በግልፅም ኡጋንዳ የደገፉ የህወሓት ደጋፊዎች ነበሩ።
*ማህበረ ቅዱሳን በትግራይ ላይ እጁን ያንሳ።ይህ እሰከ መላእክትን መካድ ይደርሳል።ለምሳሌ ተ/ሃይማኖት የኣማራ ሊሂቃን የፈጠሩት ነው መመለክ የለበትም፣ጭራሽ ተረት ተረት ነው ብለዋል የክፋትና ጥላቻ መምህሩ መምህር ገ/ኪዳን ደስታ።
*ትግራይ ሪፐብሊክ በግልፅ ማወጅ ካልሆነ ደግሞ ትግራይ ዲ ፋክቶ ስቴት መሆና ማወጅ።
*በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ የተከሰቱ መጥፎ ክስተቶች ልክ በምትጠላት በሌላ ሃገር እንደተፈፀሙ እንደወረደ መዘገብ፣ማሰራጨት ይባስ ብሎ መደሰት።ለምሳሌ በዪኒቨርስቲዎች ብጥብጥ ሲነሳ እሰይ፣ሴቶች ሲታገቱ ከማውገዝ ማበረታት፣ግጭት ሲነሳ የሰላም መፍትሔ ከማምጣት ለግጭት የሚያባብሱ ጨማምሮ መለጠፍና ማሰራጨት።
* የኢትዮጵያ መፃኢ በተደራጀ መልኩ ማጨለም፣ገፅታዋ ማበላሸት።ለምሳሌ ለመበታተን ተቃርባለች፣ሰላም የራቃት ሀገር ሆናለች፣በተፈናቃዮች ከአለም ደረጃ ያዘች-- ወዘተ እያሉ ወሬ መንዛት።
*ኢትዮጵያውያን በመልካም ዓለም ሲጠራቸውና የኢትዮጵያ ስም በመልካም ሲነሳ በተደራጀ መልኩ መልኩ መቃወም።ለምሳሌ የዶ/ር ዐቢይ የኖቤል ሽልማት መቃወም
በሁለት ዓመት ውስጥ ትግራይ እንጂ ኢትዮጵያ ሀገሬ ብሎ የዘፈነ አንድም የትግርኛ ዘፋኝ የለም።በብዛት የተዘፈኑ ዘፈኖች ደግሞ ጦርነት ቀስቃሽና ትግራይ ከኢ/ያ መሆንዋ በቁጭት የሚያወሱ ናቸው።
ግን ለምን እነዚህ በ27 ዓመት የህወሓት የስልጣን ዘመን አልተነሱም ነው ጥያቄው?
