የቁስል አሻራ!( በጋዜጤኛ አርአያ ተ/ማርያም)
በየአመቱ ይህ ወቅት ላይ የግራ እጄ ነርቭ ህመም ይነሳል። ባለፉት ሳምንታት የስቃይ ቀናትና ምሽት አሳለፍኩ። የስቃዬ አሻራ የቀድሞ የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ነው። ከእስር መፈታቱን ሰማሁ። ይበልጥ ያሳመመኝ ከእስር የተፈታበት መንገድ ነው፤ 10 አመት ተፈርዶበት ከዛ ወደ 7 ወርዶ እንደገና 4 አመት ይበቃል ተብሎ መፈታቱ ነው። ተመስገን ደሳለኝ ፊቴ ላይ ድቅን አለ። በሚያስፍር ሁኔታ አመክሮ መብት ተከልክሎ ነው የተፈታው። ከስሞኑ ሀኪም ያዘዘልኝ ከባድ መድሃኒት ስቃዬን ያስወገድልኝ ቢሆንም ዛሬ ይበልጥ ቁስሌ አመረቀዘ። እኔ..ስል ወ/ስላሴ ያሰቃያቸውን፣ ያስገደላቸውን...ጭምር አካትቼ ነው። ስቃይና ቁስላቸውን እጋራለሁ። በጣም የሚያሳዝን አንድ መረጃ ልጠቁም። ቦሌ ሩዋንዳ በቀኝ በኩል ገባ ብሎ በተንጣለለ ቪላ ይኖር የነበረው ወ/ስላሴ ማታ ሰክሮ ሲገባ በቤቱ በር ደጃፍ በእግሩ ይጓዝ የነበረ ምስኪን ወጣት ላይ አከታትሎ በመተኮስ ከገደለው በኋላ ሬሳውን ጎትቶ ግቢው አስገባው። ስልክ ደውሎ ሬሳውን አስወሰደ። ...ወ/ስላሴ የሚመራው ራሱን የቻለ መንግስት በአገሪቱ ትልቅ መረብ ዘርግቶ ነበር። ከመለስ ሞት በኋላ አዜብ መስፍን የፓርቲው መሪና ወደ ጠ/ሚ/ር ስልጣን ለማምጣት ያቀዱበትንና የከሸፈው እቅድና.ሌሎች መረጃዎችን በሚቀጥሉት ቀናት እመለስባቸዋለሁ።
(በፎቶው..ረቡእ መስከረም 20 ቀን 1996ዓ.ም ወ/ስላሴ ያሰማራቸው ፖሊሶች ያደረሱብኝ ድብደባ)

